አዳማ ከተማ ውስጥ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው እና ጥቅም ላይ የማይውሉ መድኃኒቶችን ማስወገጃ ማዕከል ተገነባ

Home Forums Semonegna Stories አዳማ ከተማ ውስጥ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው እና ጥቅም ላይ የማይውሉ መድኃኒቶችን ማስወገጃ ማዕከል ተገነባ

Viewing 2 posts - 1 through 2 (of 2 total)
  • Author
    Posts
  • #9450
    Anonymous
    Inactive

    በአዲስ አበባ በ2.5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የጤና ከተማ ሊገነባ ነው (ሪፖርተር ጋዜጣ)

    ቪዥን አፍሪካ ሆስፒታል የተባለው የግል ኩባንያ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በ2.5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የጤና ከተማ ሆስፒታል በአዲስ አበባ ሊገነባ ነው፡፡

    በሚቀጥለው ዓመት (ጥር 2012 ዓ.ም.) ይጀመራል የተባለው ይኸው የግንባታ ፕሮጀክት፣ በቦሌ ለሚ አይሲቲ ፓርክ በአንድ ሚሊዮን ስኩዌር መሬት ላይ የሚያርፍ ሲሆን፣ ለግንባታ የሚውለው ገንዘብ ከዓለም አቀፉ አበዳሪዎችም የሚገኝ መሆኑን የቪዥን አፍሪካ ሆስፒታል ኩባንያ ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ታደሰ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

    እ.ኤ.አ. በ2028 ይጠናቀቃል የተባለው ይኸው ፕሮጀክት፣ ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ ቅድመ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝና በዚህ ጊዜም በጣሊያን ዲዛይን ኩባንያ የተሠራው የሆስፒታሉ ሥነ ሕንፃ ዲዛይን መጠናቀቁንም ተናግረዋል፡፡

    የጤና ከተማ ሆስፒታሉ አምስት ሺሕ አልጋዎች ያሉትና በቀን እስከ ሰባት ሺሕ ተኝተውና በተመላላሽ ለማከም የሚያስችል ሆስፒታል፣ ሦስት ሺሕ ተማሪዎችን በአዳሪነት መያዝ የሚችል የሕክምና ትምህርት ቤት፣ የአፍሪካ የባህል ማዕከልና ሙዚየም፣ ለኤምባሲዎችና ለዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የሚያገለግሉ ቢሮዎች፣ ምግብ ማደራጃዎች፣ የገንዘብ ተቋማት፣ ባለአምስት ኮከብ ሆቴል፣ የስፖርትና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዕከል፣ ቤተ መጻሕፍት፣ የገበያ ማዕከል፣ ተጨማሪ የጤና ማዕከላትና ማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ይኖሩታል፡፡

    ሙሉውን ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ያንብቡ

    #9451
    Anonymous
    Inactive

    የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ፋብሪካ በኢትዮጵያ ሊነባ ነው (አዲስ አድማስ ጋዜጣ)

    ተቀማጭነቱን በቻይና አድርጐ፣ በህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ምርትና ሽያጭ፣ በህክምና ዘርፍ ምርምሮች አለም አቀፍ እውቅና ያለው ዋንፎ ካምፓኒ፤ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካውን በኢትዮጵያ ሊያቋቁም ነው፡፡ ፋብሪካው በቂሊንጦ ፋርማሲ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ውስጥ የሚሰራ ሲሆን እ.ኤ.አ አቆጣጠር በ2020 ግንባታው ተጠናቆ ወደ ምርት እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

    ቻይናዊው ዋንፎ ካምፓኒ ዴልታ ኢንስትሩመንት ቴክኖሎጂ፣ EZM እና RE4 ኢምፖርት ኤክስፖርት ከተባሉ አገር በቀል አጋሮቹ ጋር በትብብር ለሚያቋቋመው ለዚሁ ፋብሪካ ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ በጀት መመደቡንና የፋብሪካው ስራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ስራ በሚጀምርበት ወቅት ምርቶቹን ወደተለያዩ የአፍሪካ አገራት በብዛት ለማዳረስ እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡

    ኢትዮጵያን የህክምና መሳሪያዎች ማኑፋክቸሪንግ እምብርት ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንደሆነ የገለፀው ዋንፎ ካምፓኒ፤ ይህም ለአገሪቱ የስራ ዕድል ፈጠራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሏል፡፡

    ትናንት በሸራተን አዲስ ሆቴል በተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተነገረው፤ ዋንፎ ካምፓኒ ከሶስቱ አገር በቀል አጋሮቹ ጋር በመሆን በአፍሪካ እጅግ ተፈላጊ የሆነውን የወባ፣ የኤችአይቪ ኤድስ እና የእርግዝና ምርመራ ማድረጊያ የህክምና መሳሪያዎችን ሌሎች መገልገያ ቁሳቁሶችን ለማምረት የሚያስችለውን ፋብሪካ በአገራችን ያቋቁማል፡፡ ፋብሪካው በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ግንባታው ተጠናቆ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ እንደሚባና ለፋብሪካ ማቋቋሚያው ከተያዘው በጀት 3 ሚሊየን ዶላር የሚሆነው ለፋብሪካ ግንባታው እንደሚውል ተገልጿል፡፡

    አዲስ አድማስ ጋዜጣ

Viewing 2 posts - 1 through 2 (of 2 total)
  • You must be logged in to reply to this topic.