Home › Forums › Semonegna Stories › ራይድ የተባለዉ የታክሲ አገልግሎት ድርጅት የስም ማጥፋት ዘመቻ እና ጥቃት ደርሶብኛል በማለት ወቀሰ
- This topic has 1 reply, 1 voice, and was last updated 6 years, 1 month ago by Semonegna.
-
AuthorPosts
-
November 13, 2018 at 9:47 pm #8506SemonegnaKeymaster
ራይድ የተባለዉ የታክሲ አገልግሎት ድርጅት የስም ማጥፋት ዘመቻ እና ጥቃት ደርሶብኛል በማለት ወቀሰ። የመለያ ቁጥር 3 ባለንብረቶች ሕጋዊ ባልሆነ ደረሰኝ በትራፊክ ፖሊሶች እየተቀጣን ነው ሲሉም ተናገሩ።
“ዛይቴክ አይቲ ሶሉዊሽን” በተባለ የግል ኩባንያ ለአገልግሎት የበቃው የራይድ የሞባይል አፕልኬሽን፤ ዓላማዉ ተሳፋሪን እና አሽከርካሪን ማገናኘት እንደሆነ አስታዉቋል። ሥራውን የጀመረዉ ከሁለት ዓመት ከስድስት ወር በፊት ነው። ኩባንያው እንደሚለዉ ግቡ በሚንቀሳቀስ የጥሪ ማዕከል አማካኝነት የታክሲ አገልግሎት በተመጣጣኝ ክፍያ መስጠት ነበር። ኩባንያው በስሩ በርካታ አሽከርካሪዎችን አቅፎ እየሠራ ቢቆይም በቅርብ ጊዜ ግን እንቅፋት ገጥሞኛል ባይ ነዉ።
የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ ታደሰ እንደሚሉት በድርጅታቸዉ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ፤ በሚያስማራቸዉ አሽከርካሪዎች ላይ ደግሞ ቅጣት ደርሶባቸዋል። አቶ ሐብታሙ ለዘመቻዉ እና ለጥቃቱ የአዲስ አበባን ትራንስፖርት ባለስልጣንን ይወቅሳሉ።
አቶ ሐብታሙ አክለዉ እንዳሉት ድርጅታቸዉ ከንግድ ሚንስቴር ሕጋዊ ፈቃድ አዉጥቷል። “የስምሪት ሥራ እየሠራችሁ ነው” የሚባለው የአሠራራችን ሁኔታ አለማወቅ ነው ይላሉ። የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ባለስልጣን በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን ጠቅሶ ሕጋዊ እንዳልሆኑ በመገናኛ ብዙሃን ሁሉንም በጥቅል መናገሩ ስም ማጥፋት እንደሆነ ይናገራሉ።
◌ RIDE, Ethiopia’s version of Uber, is opening up for women in male-dominated taxi business
ራይድ የጥሪና የአፕልኬሽን የትራንስፖርት አገልግሎት ኮድ 1 የታክሲ ባለንብረቶች ጋር በጋራ ይሠራል። 540 ኮድ 1 መኪኖችን ለአገልግሎት ያሰማራል። ሆኖም የራይድ አገልግሎትን የሚያመለክቱ ስቲከሮችን የለጠፉ ተሽከርካሪዎች ለቅጣት እየተዳረጉና እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ አቶ ሐብታሙ አስታዉቀዋል። ሕጋዊ ባልሆነ ደረሰኝ እየተቀጣን ነው ይላሉም።
በሌላ በኩል ኮድ 1 ታክሲ ባለንብረቶች በብድር የገዛነውን መኪና ዕዳ መክፈል አልቻልንም ሲሉ አንድ ያነጋገርኳቸው የታክሲ ባለንብረት ዶይቸ ቬለ ራድዮ የአማርኛ ዝግጅት ክፍል ገልጸዋል። ስምሪቱ በቶሎ አይደርሰንም ሲሉ ያማርራሉ። በዚህ አገልግሎት መስጠት ያለባቸው ኮድ አንድ ብቻ መሆን እንዳለባቸውም ይገልጻሉ።
በሌላ በኩል ኮድ 3 የኪራይ መኪናዎች ሕግን ተከትለው በዚሁ ዘርፍ እየሠሩ ቢሆንም እንዳይሠሩ ተጽዕኖ እየተፈጠረብን ነው ይላሉ።
በትራንስፖርቱ ዘርፍ ፍቃድ የሌላቸው ተቋማት አገልግሎት መስጠት እንደሌለባቸው የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ዳዊት ዘለቀ ባለፈዉ ሳምንት ለሀገር ዉስጥ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል። እውቅና ሳይኖራቸው አገልግሎት ሲሰጡ የተገኙ ተቋማት መኖራቸውንም ዋና ሥራ አስኪያጁ ቢናገሩም የተቋማቱን ስም ግን አልጠቀሱም። በስልክ ያነጋገርናቸዉ የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ባለሥልጣናት ኃላፊዎች ለጥያቄያችን መልስ ለመስጠት ፈቃደኞች አይደሉም። የዶይቸ ቬለ ራድዮ የአማርኛ ዝግጅት ክፍል ጋዜጠኞች የአዲስ ትራፊክ ፖሊስ ጽህፈት ቤትን ኃላፊዎችን ለማነጋገር በተደጋጋሚ ስልክ ቢደውሉም መልስ የሚሰጣቸው አላገኙም።
የ“ዛይቴክ አይቲ ሶሉዊሽን” ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ ታደሰ ከዶይቸ ቬለ ራድዮ ጋር ያደረገውን አጭር ቃለ ምልልስ እዚህ ጋር ያዳምጡ።
ምንጭ፦ ዶይቸ ቬለ ራድዮ | Semonegna Business
November 14, 2018 at 5:33 am #8520SemonegnaKeymasterምክትል ከንቲባው የራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቀጥል የመፍትሔ አማራጭ አስቀመጡ
—–
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ከራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ከወ/ሪት ሳምራዊት ፍቅሩ ጋር በመወያየት፣ ራይድ የጀመረው ዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠናክሮ መቀጠል በሚችልበት አማራጭ መፍትሔ ዙሪያ መከሩ።
ሪፖርተር: https://www.ethiopianreporter.com/article/13863 -
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.