Home › Forums › Semonegna Stories › በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ከ56 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው ሆስፒታል ተመረቀ
Tagged: መደ ወላቡ, አቤ ደንጎሮ ሆስፒታል, ኦሮሚያ ክልል, ደረጃ ዱጉማ, ጠይባ ሀሰን
- This topic has 1 reply, 2 voices, and was last updated 5 years, 6 months ago by Anonymous.
-
AuthorPosts
-
March 18, 2019 at 10:07 am #10300SemonegnaKeymaster
ተመርቆ ለአገልግሎት የበቃው አቤ ደንጎሮ ሆስፒታል የተመላላሽ፣ የአስተኝቶ ማከም፣ የወሊድ አገልግሎት፣ የቀዶ ሕክምና፣ የድንገተኛ ሕክምና፣ የራጅ፣ የላቦራቶሪና ሌሎች የአገልግሎት መስጫ ክፍሎች አሉት።
ነቀምት (ኢዜአ) – ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤ ደንጎሮ ወረዳ ከ56 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው አቤ ደንጎሮ ሆስፒታል መጋቢት 8 ቀን 2011 ዓ.ም. ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። ሆስፒታሉ ተገንብቶ ለአገልግሎት መብቃቱ እንዳስደሰታቸው አንዳንድ የወረዳው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ደረጃ ዱጉማ በምርቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት፥ ተመርቆ ለአገልግሎት የበቃው አቤ ደንጎሮ ሆስፒታል የተመላላሽ፣ የአስተኝቶ ማከም፣ የወሊድ አገልግሎት፣ የቀዶ ሕክምና፣ የድንገተኛ ሕክምና፣ የራጅ፣ የላቦራቶሪና ሌሎች የአገልግሎት መስጫ ክፍሎች አሉት።
ሆስፒታሉ በአቤ ደንጎሮ ወረዳና በአካባቢው በሚገኙ ተጎራባች ወረዳዎች ለሚገኙ ከ400 ሺህ ለሚበልጡ ነዋሪዎች አገልግሎት እንደሚሰጥ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ሆስፒታሉ የሕክምና መሳሪያዎችና የሰው ኃይል የተሟላለት መሆኑንም አመልክተዋል።
የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንትና የማኅበራዊ ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪ ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን በበኩላቸው ሆስፒታሉ የህዝቡን የረጅም ጊዜ ጥያቄ የመለሰና የሕዝቡን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የሚፈታ መሆኑን ገልጸዋል። ህብረተሰቡ ሆስፒታሉ የራሱ ሀብትና ንብረት መሆኑን ተረድቶ እንደ ዓይኑ ብሌን ሊጠብቀው እንደሚገባ አሳስበዋል።
ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች በበኩላቸው ሆስፒታሉ ተገንብቶ ለአገልግሎት በመብቃቱ መደሰታቸውን ተናግረዋል።
ከወረዳው ነዋሪዎች መካከል የቱሉ ዋዩ ከተማ ነዋሪ ወ/ሮ እቴነሽ ደገፉ በሰጡት አስተያየት በአካባቢያቸው ለበርካታ ዓመታት የጤና ተቋማት ባለመኖሩ በተለይ በእናቶችና ህጻናት ህይወት ላይ አደጋ ይደርስ እንደነበር አስታውሰዋል። የወረዳው ህዝብ ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ሻምቡና ነቀምቴ ሆስፒታሎች በመጓዝ ለወጪና እንግሊት ሲጋለጥ መቆየቱንም ጠቁመዋል። በአካባቢያችን ደረጃውን የተጠበቀ ሆስፒታል መገንባቱ ወጪና እንግልትን ከማስቀረቱም በላይ የእናቶችና የህጻናትን ሞት ለመቀነስ እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
ሌላው የከተማው ነዋሪ አቶ ደቻሣ ገለታ ወረዳው ከነቀምቴና ሻምቡ ሆስፒታሎች በብዙ ኪሎሜትሮች ርቀት ላይ ስለሚገኝ በተለይ በወሊድ ጊዜ የበርካታ እናቶችና ህፃናት ህይወት ሲያልፍ መቆየቱን አመልክተዋል። የሆስፒታል መገንባት የአካባቢውን ሕዝብ የረጅም ጊዜ ጥያቄ የመለሰና የህብረተሰቡን የጤና ችግር የሚፈታ በመሆኑ ተገንብቶ ለአገልግሎት በመብቃቱ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
——
ተመሳሳይ ዜናዎች፦- የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ባለስልጣናት በተገኙበት በይፋ ተመረቀ
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ ያስገነባው ዘመናዊ የህክምና ማዕከል ተመረቀ
- የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተቀናጀ የግብርና ምርምር ፕሮጀክት ተመረቀ
- የዱባይ ግብረ ሰናይ ድርጅት አዲስ አበባ ውስጥ ያስገነባው ትምህርት ቤት ተመረቀ
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ ያስገነባው ዘመናዊ የህክምና ማዕከል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ሌሎችች ባለስልጣናት በተገኙበት ተመረቀ
June 16, 2019 at 12:33 am #11102AnonymousInactiveበ60 ሚሊዮን ብር የተገነባው የመደ ወላቡ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በይፋ ተመረቀ
—–በባሌ ዞን በመደ ወላቡ ወረዳ በ60 ሚሊዮን ብር የተገነባው የመደ ወላቡ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ባሳለፍነው ሳምንት በይፋ ተመርቋል።
ሆስፒታሉን በይፋ የመረቁት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ናቸው፡፡ኤክስ ሬይን ጀምሮ በርካታ የህክምና ቁሳቁሶችን ያሟላው ሆስፒታል ለ150 ሺህ የአካባቢው ነዋሪዎች አገልግሎት መስጠት ይችላል ሲል የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።
በ2005 ዓ.ም. ግንባታው የተጀመረው ሆስፒታሉ በ2009 ዓ.ም. በከፊል ተጠናቆ ሥራ እንደጀመረ በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ ተገልጿል።ምንጭ፦የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.