Home › Forums › Semonegna Stories › የካንሰር ህክምና አገልግሎት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል
Tagged: ካንሰር, የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል
- This topic has 0 replies, 1 voice, and was last updated 6 years, 2 months ago by Semonegna.
-
AuthorPosts
-
November 8, 2018 at 1:34 pm #8456SemonegnaKeymaster
ኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን ድረስ የካንሰር ህክምና አገልግሎት በብቸኝነት ሲሰጥ የነበረው የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንደነበረና የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ይህን አገልግሎት መጀመሩ ለታካሚዎች ትልቅ አስተዋጽዖ ይኖረዋል።
አዲስ አባባ (ዋልታ/ ሰሞነኛ) – የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ከመስከረም 2 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ የካንሰር ህክምና አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ አስታውቋል። ሆስፒታሉ ህክምናውን ከጀመረበት ቀን አንስቶ እስካሁን ድረስ ከ300 በላይ የካንሰር ታማሚዎችን በተመላላሽ ማከሙንም ገልጿል።
በሆስፒታሉ የካንሰር ህክምና ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር አብዲ አደም የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ይህንን ህክምና መጀመሩ ከዚህ በፊት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በቦታ ጥበት ምክንያት በወረፋ ለሚንገላቱ ታካሚዎች መፍትሔ ይዞ መምጣቱን ገልጸዋል።
እስካሁን በተመላላሽ ህክምና ለታካሚዎች አገልግሎት ሲሠጥ መቆየቱን የገለጹት ዶ/ር አብዲ በቅርቡ አስተኝቶ ማከም የሚያስችል ወደ 350 የሚጠጋ አልጋ እየተዘጋጀ መሆኑን አስታውቀዋል።
ዋልታ ያነጋገራቸው በሆስፒታሉ የካንሰር ታካሚዎች እንደገለጹት ከዚህ በፊት ህክምናውን ለማግኘት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እስከ ስድስት ወር እንደሚወስድ ገልጸው አሁን ግን በቅዱስ ጳውሎስ አገልግሎት መጀመሩ ያለምንም ወረፋ ህክምናን ለማግኘት እንዳስቻላቸው ተናግረዋል።
◌ Ethiopia: Are Ethiopian hospitals constructed in environment-suitable and climate-friendly way?
በኢትዮጵያ የተደራጀ የጥናት ውጤት ባይኖርም በግምት በዓመት ከ160 ሺህ በላይ የካንሰር ተጠቂዎች እንደሚኖሩ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። እ.ኤ.አ በ2012 በተደረገ ጥናት ኢትዮጵያ ውስጥ በዓመት ውስጥ ከሚሞቱ ሰዎች ውስጥ 5.8 በመቶ የሚሆኑት በካንሰር ምክንያት እንደሚሞቱ ይጠቁማል። በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ስር የብሔራዊ የካንሰር ቁጥጥር ፕላን ባወጣው በዚህ ጥናት ምንም እንኳን ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ አጠቃላይ የሕዝብ ቆጠራን ተገን ያደረገ አሀዝ (population-based data) ባይኖርም ኢትዮጵያ ውስጥ በየዓመቱ 60,960 ሰዎች በተለያዩ ዓይነት የካንሰር በሽታዎች እንደሚጠቁና 44,000 ሰዎች ደግሞ በካንሰር ምክንያት እንደሚሞቱ ያትታል። በዚህም የካንሰር በሽታ በከፍተኛ ቁጥር ሰዎችን ከሚያጠቁ አራት ተለላፊ ካልሆኑ በሽታዎች [non-communicable diseases] ውስጥ ከልብ በሽታ ቀጥሎ ሁለተኛው ነው። (እነዚህ አራቱ ተለላፊ ከሆኑ በሽታዎች የልብ በሽታ፣ ካንሰር፣ የስኳር በሽታ እና የሳንባ በሽታ ሲሆኑ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎ ከሚሞቱት ሰዎች ቁጥር 80 በመቶ የሚሆነው ከእነዚህ በሽታዎች በአንዱ ምክንያት የሚሞት ነው።) ኢትዮጵያ ውስጥ ወንዶች ላይ የደምየ አንጀት ካንሰሮች፣ ሴቶች ላይ ደግሞ የጡት ካንሰር በከፍተኛ መጠን እንደሚታይ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ሪፖርት ያሳያል።
የዓለም ጤና ድርጅት ለአንድ ሚሊዮን ሰዎች አንድ የካንሰር ህክምና ተቋም ሊኖር እንደሚገባ ቢመክርም በኢትዮጵያ ግን ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በብቸኝነት የህክምናውን አገልግሎት ይሰጥ እንደነበርና እ. ኤ.አ በ2017 በወጣ አሃዝ ከ6,000 በላይ የካንሰር ታካሚዎችን እያከመ እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የስዊዘርላንዱ መድኃኒት አምራች ግዙፍ ኩባንያ ኖቫትሪስ (Novartis) እ.ኤ.አ በ2017 ባወጣው ዘገባ ከ100 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ኢትዮጵያ በቁጥር ስምንት ኦንኮሎጂስቶች (የካንሰር ሀኪሞች) ብቻ እንዳላት አስታውቋል። ሌላ ተመሳስይ ጥናት ደግሞ ብቸኛው የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ካሉት 627 ነርሶች ውስጥ 26ቱ ብቻ የካንሰር ህክምና ነርሶች እንደሆነ ይጠቁማል።
ዋልታ | ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.