የታሸጉ ውሃዎችና ተግዳሮቶቻቸው
—–
የታሸገ ውሃ (ቦትልድ ዋተር) ለመጀመርያ ጊዜ የተመረተው በእንግሊዝ እ.ኤ.አ. በ1621 ነው፡፡ በ17ኛው ክፍለ ዘመን በአሜሪካና በአውሮፓ አገሮች እየተስፋፉ የመጡበት ሁኔታ መኖሩ፣ የታሸገ ውሃ እንደ ፀበል በሽታን ይፈውሳል የሚል እምነት አሳድሮም ነበር፡፡ በኢትዮጵያ የታሸገ ውሃ መጠቀም ከተጀመረ ወደ ሁለት አሠርታት ቢሆንም በፍጥነት እያደገ የመጣ ዘርፍ ነው፡፡
አቶ ደሴ አበጀ የምግብ፣ መጠጥና ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የፓኬጂንግ ዳይሬክተር እንደተናገሩት፣ በ2006 ዓ.ም. 33 የነበሩት የውሃ ፋብሪካዎች አሁን ላይ 80 ደርሰዋል፡፡ በሥራ ዕድል ፈጠራው፣ በቴክኖሎጂ ሽግግሩና ኅብረተሰቡን በማርካት ደረጃ ሲታዩ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጠቀሜታም አስገኝተዋል፡፡
በቴክኖሎጂ ሽግግር ረገድ በ1993 ዓ.ም. በትንሽ መሣሪያ ይገለገሉ የነበሩ ፋብሪካዎች፣ በአሁኑ ሰዓት እጅግ ትልልቅና በጣም ውስብስብ የሆኑ የውሃ ማምረቻ መሣሪያዎችን መጠቀም ጀምረዋል፡፡ እንዲህ ዓይነት ፋብሪካዎችም በብዛት ተገንብተው በሥራ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ ባለፈው ዓመት ከተወሰደው መረጃ ለማወቅ እንደተቻለው፣ ከ100 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ባለበት አገር ውስጥ በቀን ለአንድ ሰው በአማካይ 100 ሚሊ ሊትር የታሸገ ውሃ ይመረታል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ 3.5 ቢሊዮን ጠርሙስ ውሃ እንደሚመረት ይገመታል፡፡ ይህም ፍላጎትን እንደማያሟላ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
የውሃ አምራች ተቋማት እያደጉና እየተስፋፉ ቢመጡም፣ በርካታ ችግሮች እንዳሉባቸው ይነገራል፡፡ ከችግሮቹም መካከል ደረጃ ባለማሟላታቸው የተነሳ የመታሸግ፣ ከተቆጣጣሪ አካላት በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ መሰጠት፣ የብሔራዊ ደረጃን ምልክት ሳይለጥፉ ማምረትና መሸጥ ተጠቃሾ ናቸው፡፡
የማምረቻ ቦታና አካባቢ ንፅህና ደረጃ አናሳ መሆን፣ የታሸገን ውሃ የምርት ደኅንትና ጥራት ሊያጓድሉ ከሚችሉ ነገር ጋር ተቀላቅሎ ማከማቸትና ማጓጓዝ፣ በየሱቁ በታሸጉ ውሃዎች ላይ ኬሚካልና የፍሳሽ ሳሙና ተደርድረው መታየት፣ በሐሩራማና በጣም ከባድ በሆነ ፀሐይ አካባቢ የታሸጉ ውሃዎችን ማከማቸት እየተለመደ መምጣቱ፣ የውሃና የማሸጊያ ማምረቻዎችን በአንድ የሥራ ክፍል ውስጥ ማምረቱ ችግሮች ናቸው፡፡
ሙሉውን ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ማንበብዎን ይቀጥሉ