Home › Forums › Semonegna Stories › የአርሲ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ4ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 388 የህክምናና የጤና ተማሪዎች አስመረቀ
Tagged: አርሲ ዩኒቨርስቲ
- This topic has 0 replies, 1 voice, and was last updated 5 years, 9 months ago by Semonegna.
-
AuthorPosts
-
January 15, 2019 at 7:23 pm #9217SemonegnaKeymaster
የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ካስመረቃቸው መካከል 86ቱ የህክምና ዶክተሮች መሆናቸውንና፣ ቀሪዎቹ በጤና መኮንን፣ ክሊኒካል ነርሲንግ፣ ሚድዋይፈሪና በሜዲካል ላቦራቶሪ ሳይንስ መስክ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ መሰልጠናቸው ተጠቁሟል።
አሰላ (ሰሞነኛ) – የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በህክምና ዶክትሬት፣ በጤና መኮንንና ሌሎች የጤና ትምህርት መስኮች ለ4ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 388 የህክምና እና የጤና ተማሪዎች አስመረቀ።
የህክምና ሙያ ምሩቃን መከላከል በሚቻል በሽታ (preventable diseases) መሞት እንዲበቃ ጠንክረው በመሥራት ጤንነቱ የተጠበቀ ማኅበረሰብ ለመፍጠር ሊረባረቡ እንደሚገባ የሣይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ዶ/ር ሂሩት ወልደማርያም ለተመራቂዎች ባስተላለፉት መልዕክት አሳስበዋል።
በጤና አገልግሎትና አጠባበቅ ረገድ በሚታየው ውስንነት መዳን በሚቻልባቸው በሽታዎች ሰዎች እንደሚሞቱና ታክሞ መከላከል በሚቻል ሁኔታም የአልጋ ቁራኛ እንደሚሆኑ ያብራሩት ዶ/ር ሂሩት፥ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሥራው ዓለም የሚፈልገውን ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ ከማፍራት አንፃር ትኩረት የሚሹ ቀሪ ሥራዎችን ለመፈጸም መሠራት እንዳለበት አሳስበዋል።
◌ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በህክምና እና በነርስነት ይስተማራቸውን 220 ተማሪዎች አስመረቀ
የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ኑዋማ ቢፋ ኮሌጁ ካስመረቃቸው መካከል 86ቱ የህክምና ዶክተሮች መሆናቸውንና፣ ቀሪዎቹ በጤና መኮንን፣ ክሊኒካል ነርሲንግ፣ ሚድዋይፈሪና በሜዲካል ላቦራቶሪ ሳይንስ መስክ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ መሰልጠናቸውን ጠቁመዋል። በጤናው መስክ ሀገሪቱ ያለባትን የባለሙያ እጥረት ለማቃለል ዩኒቨርሲቲው ድርሻውን እየተወጣ መሆኑንም ዶ/ር ኑዋማ አመልክተዋል።
የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዱጉማ አዱኛ ተመራቂዎቹ በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የቀሰሙትን ዕውቀት ከህይወት ተሞክሯቸው ጋር በማዋሃድ በተሰማሩበት መስክ ኃላፊነታውን መወጣት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
ከተመራቂዎች መካከል በህክምና ዶክትሬት ዲግሪ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ ዶ/ር አዲሱ ነዲ በሰጠው አስተያየት፥ በሽታን አስቀድሞ መከላከል ላይ መሠረት ያደረገውን የጤና ፖሊሲ ውጤታማ እንዲሆን የሚጠበቅበትን ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
ከሴቶች ተማሪዎች በከፍተኛ ውጤት በማምጣት የተመረቀችው ዶ/ር አያንቱ ሆርዶፋ በበኩሏ በዩኒቨርሲቲው የቀሰመችውን ዕውቀት ወደ ተግባር በመለወጥ ለውጥ ለማምጣት እንደምትጥር ተናግራለች።
የህክምና ትምህርት የተግባር ትምህርት እንደመሆኑ እርስ በእርስ የነበረ የመማማር ሂደት አሁን ለደረሰችበት ስኬት እንደረዳት ገልጻለች።
ምንጭ፦ የሣይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር / ኢዜአ / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
——
ተመሳሳይ ዜናዎች፦- የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ዶክተሮችን ለስድስተኛ ጊዜ አስመረቀ
- በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥናት ትምህርት ቤት በይፋ ተመርቆ ሥራ ጀመረ
- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገነባው የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል ግንባታ በተያዘለት የጊዜ ገደብ አይጠናቀቅም
- ኬር ኢትዮጵያ በ7 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ወጭ ያስገነባውን የምርምርና የስልጠና ማዕከል ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ አስረከበ
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ ያስገነባው ዘመናዊ የህክምና ማዕከል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ሌሎችች ባለስልጣናት በተገኙበት ተመረቀ
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.