Home › Forums › Semonegna Stories › የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት እና ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር አብሮ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ
Tagged: መለሰ ማርዮ, ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ, የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት, ገናናው ጎንፌ
- This topic has 0 replies, 1 voice, and was last updated 6 years ago by
Semonegna.
-
AuthorPosts
-
February 6, 2019 at 7:47 am #9524
Semonegna
Keymasterየኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት በቅርቡ ዋና ካምፓሱን በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፍቼ ከተማ በምድረግ ከተመሠረተው ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር አብሮ ለመሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።
አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መለሰ ማርዮ እና የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገናናው ጎንፌ ጥር 8 ቀን 2011 ዓ.ም. በኢንስቲትዩቱ አዳራሽ እውቀትን ለማሸጋገር፣ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን በጋራ ለማከናወን የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መለሰ ማርዮ በስምምነት ፊርማው ላይ ባደረጉት ንግግር እንዳስታወቁት የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና የምርምር ተቋማት ጋር አብሮ ሊያሠራው የሚችል ስምምነቶችን በመፈራረም የተለያዩ ተግባራትን ለማከናወን መቻሉን ገልጸዋል። ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በዱረም ስንዴ ላይ በተሠራው ሥራ ከፍተኛ ምርት የሚሰጥና ድርቅን መቋቋም የሚችል ውጤት መገኝቱን፤ ከጎንደር ዩኒቨረሲቲ ጋር በመተባበር በደን ልማት ላይ እየተሠራ መሆኑን እና ከዲላ ዩኒቨረሲቲ ጋርም በመተባበር ለምርምርና ለቱሪስት መስህብ የሚውል የቦታኒክ ጋርደን ግንባታ ሥራ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
◌ VIDEO: Ethiopia: After mandatory preparations, Selale University accepts incoming students
የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገናናው ጎንፌ በበኩላቸው ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በቅርብ ጊዜ ሥራ የጀመረ፣ እየሰፋ የሚሂድና ለግብርና እና የአካባቢ ጥበቃ ልዩ ትኩረት የሚሰጥ ነው። የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ካለው መልካአ ምድራዊ አቀማመጡ ጋር በተያያዘም በእንስሳት ዝርያ አጠባበቅ በተለይም የተለያዩ ዝርያዎችን በማዳቀል ለአዲስ አበባ ከተማ 50 በመቶ የሆነውን የወተት ምርት የሚያቀርበው የሰላሌ አርሶ አደርን ተጠቃሚ ለማድረግ ከኢንስቲትዩቱ ጋር አብረው ለመሥራት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
ዶ/ር ገናናው አክለውም ስምምነቱ የወረቀት ላይ ስምምነት ብቻ እንዳይሆን ለማድረግና የብዝሀ ሕይወት ጥበቃ ሥራዎችን ለሕብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ከመማር ማስተማር ሥራው ጎን ለጎን የአካባቢውን ማሕበረሰብ ተጠቃሚ የማድረግ ሥራ ለማከናወን ዩኒቨርሲቲው መዘጋጀቱን ገለጸዋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
——
ሌሎች ዜናዎች፦- ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የኮምፒዩተር ድጋፍ አደረገ
- የአርሲ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ4ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 388 የህክምናና የጤና ተማሪዎች አስመረቀ
- ኬር ኢትዮጵያ በ7 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ወጭ ያስገነባውን የምርምርና የስልጠና ማዕከል ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ አስረከበ
- የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለቀረቡላቸው አማራጮች ፈንታ በከተማው ውስጥ ሁከት በመፍጠራቸው ከባህር ዳር እንዲወጡ ተጠየቀ
- ጃፓን የትምህርትና ጤና ዘርፎችን ለመደገፍና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚገኘውን የራስ መኰንን አዳራሽ የገንዘብ እርዳታ አደረገች
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.