የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተመረቀ

Home Forums Semonegna Stories የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተመረቀ

Viewing 2 posts - 1 through 2 (of 2 total)
  • Author
    Posts
  • #7932
    Semonegna
    Keymaster

    የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያስገነባው የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የግንባታ ሥራው የተጀመረው በጥቅምት ወር 2009 ዓ.ም ሲሆን የቻይናው ግዙፍ ኩባንያ ቻይና ሲቪል እንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ግንባታውን ሲያከናውን ነበር።

    አዳማ (Semonegna) – በኦሮሚያ ክልል፣ አዳማ ከተማ የተገነባው የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በዛሬው ዕለት (መስከረም 27 ቀን 2011 ዓ.ም.) ተመርቋል። በምርቃቱ ስነ ስርዓት ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ለማ መገርሳ፣ የአማራ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የእንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ እና የኮርፖሬሽኑዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ት ሌሊሴ ነሜ እንዲሁም ሌሎች የክልልና የፌደራል ባለስልጣናት ከፍተኛ ተገኝተዋል።

    የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያስገነባው የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የግንባታ ሥራው የተጀመረው በጥቅምት ወር 2009 ዓ.ም ሲሆን የቻይናው ግዙፍ ኩባንያ ቻይና ሲቪል እንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን (China Civil Engineering Construction Corporation/ CCCC) ግንባታውን ሲያከናውን ነበር።

    ከአዲስ አበበ ከተማ 99 ኪሎ ሜትሮች ርቆ የሚገኘው የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተለያየ ዘርፍ ለሚሰማሩ አምራች ኩባንያዎች የሚያገለግሉ በአጠቃላይ 19 (በዝርዝር፦ ስድስት 11 ሺህ ካሬ ሜትር፣ ዘጠኝ 5 ሺህ 500 ካሬ ሜትር፣ አራቱ ደግሞ በ3 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፉ) የመሥሪያ ጠለላዎች ወይም የመሥሪያ ቦታዎችን (shades) የያዘ ነው። የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በአጠቃላይ ሊለማ ከታቀደው 2 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ በመጀመሪያው ዙር ልማት 354 ሄክታር መሬት የሚይዝ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ለምቶ ለዛሬ ምረቃ የበቃው በ100 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባው ክፍል መሆኑን፣ ይህም ግንባታ 4.1 ቢልዮን ብር መፍጀቱን፣ እንዲሁም ፓርኩ በመጀመሪያው ምዕራፍ በሙሉ አቅም ወደ ምርት ሲገባ እስከ 25 ሺህ ለሚደርሱ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ወ/ት ሌሊሴ ነሜ በምረቃው ንግግራቸው ላይ አስታውቀዋል።

    ◌ RELATED: A visit to Hawassa Industrial Park by Dire Dawa Industrial Park & City’s Administration people

    የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተመርቆ ሥራ መጀመር በሀገሪቱ ወደማምረት የገቡ የኢንዱስትሪ ፓርክኮች ቁጥር ወደ አምስት የሚያሳድገው ሲሆን፥ ከሌሎቹ አራቱ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለየት የሚያደርገው ፓርኩ ያለበት ከተማ (አዳማ) በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ አስተዋጽዖ ያመጣል ተብሎ የታመነበተና አምና ሥራ የጀመረው የአዲስ አበባ-ጅቡቲ የባቡር መስመር በሚያልፍባት የአዳማ ከተማ መገኘቱ ነው። ይህ የባቡር መስመርና የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ እርስ በርሳቸው ጉልህ የሆነ የጥቅም ግንኙነት ይኖራቸዋል ተብሎ ይታመናል። ከዚህ በተጨማሪ የኢንዱስትሪ ፓሩኩ በከተማ ከሚገኘው የአዳማ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ጋር በማምረት ዘርፍ እና በመማር፣ ማስተማርና ምርምር ዘርፎች መካከል ቁልፍ የሆነ ግንኙነት ይፈጥራሉ ይጠበቃል።

    የሀገሪቱ የማኑፋክቸሪንግ ሴክተር (manufacturing sector) ከኢትዮጵያ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) መጠን አራት ነጥብ አምስት በመቶ (4.5%) ድርሻ ብቻ የሚሸፍን ሲሆን፥ መንግስት እስከ 2022 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ይህን አናሳ ድርሻ ወደ ሀያሁለት በመቶ (22%) ለማሳደግ አቅዳለች። ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ እስከ 2025 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) አሁን ያሏትን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ቁጥር ከአምስት ወደ ሀያ አምስት የማሳደግ ዕቅድ አላት። በያዝነው ዓመት ስድስት የኢንዱስትሪ ፓርኮች (ድሬ ዳዋ፣ ቂሊንጦ II፣ ቦሌ ለሚ II፣ ጅማ፣ ባህር ዳር እና ደብረ ብርሃን) ግንባታቸው ተጠናቆ ወደምርት ተግባር እንደሚገቡ ዶክተር አርከበ ዕቁባይ አስታውቀዋል። 

    ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

    የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ

    #10014
    Semonegna
    Keymaster

    የደብረብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድና በኬንያው ፕሬዝዳንት ዑሁሩ ኬንያታ ተመረቀ
    —–

    የደብረብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድና በኬንያው ፕሬዝዳንት ዑሁሩ ኬንያታ ተመረቀ። የኢንዱስትሪ ፓርኩ ግንባታው በ2009ዓ.ም ነበር በ75 ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጭ የተጀመረው፡፡ የኢንዱስትሪ ፓርኩ 8 ሼዶች ያሉት ሆኖ በ75 ሄክታር መሬት ላይ አርፏል።

    የኢንዱስትሪ ፓርኩ ከደብረ ብርሃን ከተማ 6 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።

    ምንጭ፦ የአማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት

Viewing 2 posts - 1 through 2 (of 2 total)
  • You must be logged in to reply to this topic.