Search Results for 'ህወሓት'

Home Forums Search Search Results for 'ህወሓት'

Viewing 61 results (of 61 total)
  • Author
    Search Results
  • Anonymous
    Inactive

    “በአሁኑ ጊዜ የህወሓት አመራሮችና አባላት በመሆናቸው ብቻ ከፌዴራል መንግሥትና ከአዲስ አበባ አስተዳደር የኃላፊነት ቦታዎች እንዲነሱ እየተደረገ ነው። ይህ ተግባር በፍፁም ተቀባይነት የለውም።”

    የህወሓት ማዕከላይ ኮሚቴ መግለጫ

    መቐለ (ህወሓት ማዕከላይ ኮሚቴ) – ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ውስጥ የተፈጠረው የሃሳብና የመስመር ልዩነት እየሰፋ መጥቶ አሁን ኢህአዴግ በያዘው መስመርና ከነበረው የግንባሩ አደረጃጀት ሥርዓት እና አሠራር ውጭ ጨርሶ እንዲፈርስ በማድረግ በይዘቱ አዲስ ፓርቲ እንዲመሠረት ተደርጓል። ህወሓት ይህ ሕገ-ወጥና ፀረ-ዴሞክራሲ አካሄድ በተደጋጋሚ እንዲታረም፣ የሀገራችንን ህልውና አደጋ ውስጥ በገባበት ወቅት ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ሊታዩ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ እንድናተኩር በፓርቲው ውስጥም ሆነ ለመላው የሃገራችን ሕዝብ በተደጋጋሚ ስንገልፅ ቆይተናል።

    ይሁን እንጂ ይህንን ሊቀበል ወይም ሊሰማ ዝግጁ ያልሆነው አመራር ኢህአዴግን በፀረ- ዴሞክራሲያዊ መንገድ እንዲፈርስ እና ሕዝብ ያልመረጠው አዲስ ፓርቲ ስልጣን ይዞ እንዲቀጥል አድርጓል። ከዚህ በኋላ እንደ ድርጅት የነበረን ብቸኛው አማራጭ በጉዳዩ ላይ ሕዝባችን በተወካዮቹ በኩል ተወያይቶ እንዲወስን፤ ይህንን ተከትሎም በመጀመሪያው አስቸኳይ ጉባዔያችን ላይ ሂደቱንና ሁኔታዎችን በዝርዝር እንዲወስን ማድረግ ነበር። በዚሁ መሠረት ከተፈጠረው አዲስ ፓርቲ ጋር እንደማንወሃድ መወሰኑ ይታወቃል።

    በፓርቲ ደረጃ በያዝነው መስመር እንለያይ እንጂ በሕገ-መንግሥታችን የተቀመጠውን የፌደራል እና የክልል መንግሥት ግዴታና መብት አክብረን እንደምንሄድ በግልፅ አስታውቀናል። በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢህአዴግን በያዘው ዓላማና ፕሮግራም እስከ ቀጣይ ምርጫ የሰጠውን ኃላፊነት በጥብቅ ሊከበር ይገባል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የኢህአዴግ ድርጅቶችን ነው የመረጠው። መንግሥት እንዲመሠርቱም፣ እንዲመሩም ስልጣን የተሰጣቸው እነዚህ ድርጅቶች ናቸው። ከዚህ ውጭ በማን አለብኝነት ሕዝብ ያልመረጠው ሌላ አዲስ ድርጅት ስልጣን እንዲይዝም ሆነ አገር እንዲመራም ማድረግ የሕዝቡን ስልጣን መቀማትና ሕገ-መንግሥቱን መርገጥ ነው። ሀገር እንዲመራ በጋራ ለተሰጠን ኃላፊነት በተወሰኑ ኃይሎች ፍላጎት ሕጋዊ እና ዴሞክራሲያዊ ያልሆኑ ውሳኔዎች ሊወሰኑና ሊተገበሩ አይገባም።

    በአሁኑ ጊዜ የህወሓት አመራሮችና አባላት በመሆናቸው ብቻ ከፌዴራል መንግሥትና ከአዲስ አበባ አስተዳደር የኃላፊነት ቦታዎች እንዲነሱ እየተደረገ ነው። ይህ ተግባር በፍፁም ተቀባይነት የለውም። በመሆኑም ይህ ሆነ ተብሎ እየተፈፀመ ያለው እና ከዚህ ቀደም የተፈፀመ መረን የለቀቀ ተግባር ሊታረም ይገባል። ካልሆነ ግን ይህንን ተከትሎ ለሚፈጠር ሁኔታ ኃላፊነት የሚወስደው ይህ ሕገ-ወጥ ተግባር እየፈፀመ ያለው አካል መሆኑን ግልፅ ሊሆን ይገባል።

    የህወሓት ማዕከላይ ኮሚቴ
    መቐለ

    የህወሓት ማዕከላይ ኮሚቴ


Viewing 61 results (of 61 total)