Search Results for 'ባሕር ዳር'

Home Forums Search Search Results for 'ባሕር ዳር'

Viewing 31 results (of 31 total)
  • Author
    Search Results
  • Semonegna
    Keymaster

    የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሠራ ነው

    ባሕር ዳር፦ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ የምርምር ሥራ ለመሥራት የሚሆን 54.8 ሄክታር መሬት ከመንግስት በስጦታ አግኝቶ ምርምር በማካሄድ ላይ ይገኛል። ለምርምር የሚሆነው ስፍራ በመርዓዊ ከተማ (ከባህር ዳር ከተማ በደቡባዊ አቅጣጫ 30 ኪሎ ሜትሮችን ርቃ የምትገኝ ከተማ) ዙሪያ በሚገኙ አራት ቦታዎች ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ለሙከራ የሚሆን ከዚህ ቀደም በአካባቢው በአርሶ አደሮች ያልተሞከሩ የጤፍ ዘር፣ የስንዴ ዘርና እንዲሁም የበቆሎ ዘር ተዘርቶ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝና ጥሩ ምርትም እንደሚገኝበት በመስክ ጉብኝቱ የተገኙ ባለሙያዎች አስተያየታቸውን ሰጥተውበታል።

    የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሰለሞን አዲሱ በአራቱም ቦታዎች ላይ የተሠሩ የምርምር ሙከራዎችን ለተጋባዥ እንግዶች ሲያስጎበኙ እንዳሉት የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ቦታውን ከተቀበለ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተግባር ለማስገባት ሲባል የመኪና መንገድ፣ ድንበር ማስወሰን፣ ዘርና ማዳበሪያ ግዥ የመሳሰሉ ሂደቶችን አልፈው ያልተሞከሩ የዘር አይነቶችን ለመሞከር ለአርሶ አደሩ በተሻለ መልኩ አምርቶ ለማሳየት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው ማህበረሰቡ ከዚህ ልማት በዘር አቅርቦት፣ በጉልበት እንዲሁም በመሳሰሉት መንገዶች የሚጠቀምበትን መንገድ እናመቻቻለን ብለዋል።

    ተመሳሳይ ዜና፦ Addis Ababa University receives over USD3.5 million award for Health Professional Education Partnership Initiative (HEPI) through the US government fund

    የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃኑ ገድፍ በጉብኝቱ የተገኙ ሲሆን ይህ የምርምር ሥራ ከምርታማነት አንጻር ከአርሶ አደሩ በተለየ ሁኔታ ለውጥ ማምጣት አለበት፣ ተመራማሪዎቻችን የሚመራመሩበት፣ አዲስ የዘር ዝርያ /variety/ የሚወጣበት እንዲሁም የተለያዩ ተማሪዎች የምርምር ሥራቸውን በተግባር የሚሰሩበት የልህቀት ማዕከል /center of excellence/ መሆን ይገባዋል ብለዋል።

    አጠቃላይ 54.8 ሄክታር ከሚደርሰው መሬት ውስጥ በአራት የተለያዩ ቦታዎች ላይ ከተዘሩት የተለያዩ አዝዕርት ዘር የተዘራ ሲሆን ከዚህ ቦታ በተጨማሪ ያልተዘራበት ስምንት ሄክታር በመተው ተመራማሪዎች የምርምር ሥራቸውን እያካሄዱበት ይገኛሉ። በጉብኝቱ ወቅት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞች፣ የግብርና ባለሙያዎችና የዩኒቨርሲቲው አመራሮች የተገኙ ሲሆን የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተሰጠውን መሬት ወሰን በማስከበር እንዲሁም ዘላቂ እቅድ በማቀድ ከዚህ የምርምር ሥራ ማኅበረሰቡ የሚጠቀምበትን መንገድ ማመቻቸት አለበት ተብሏል።

    (በትዕግስት ዳዊት)
    ምንጭ፦ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

    የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፎቶ ምንጭ፦ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

Viewing 31 results (of 31 total)