Search Results for 'ኢትዮጵያ'

Home Forums Search Search Results for 'ኢትዮጵያ'

Viewing 15 results - 541 through 555 (of 730 total)
  • Author
    Search Results
  • Anonymous
    Inactive

    ተማሪዎች እና መምህራን 123ኛውን የአድዋን ድል እየዘከሩ ነው
    —–

    ‹‹3ቱ የካቲቶች›› የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ እስከ የካቲት 30 ይቆያል

    የ‹መለከት አፀደ ሕጻናትና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት› ተማሪዎች በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ሥር በሚገኘው በብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል በመገኘት 123ኛውን የአድዋን ድል እየዘከሩ ነው፡፡

    የአድዋን ድል በማስመልከትም ያዘጋጁትን ቴአትር አቅርበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የልጆች ክፍል አዘጋጆች በቦታው ተገኝተው የተማሪዎቹን ጉብኝትና ቴአትር ቀረጻ አድርገዋል፡፡

    ሕጻናቱ ባቀረቡት ቴአትር ላይ አገር ስለመውደድ፣ ስለፍቅር እና የፆታ እኩልነትን አስመልክተው አስተማሪ ጭብጦችን አንስተዋል፡፡

    ‹‹3ቱ የካቲቶች›› የተሰኘው የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ እስከ የካቲት 30 ስለሚቆይ ሁላችሁም እንድትጎበኙት ተጋብዛችኋል፡፡

    —————————-
    አድራሻች፡- የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ፣ ከፒያሳ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ፣ ሆስፒታሉ አካባቢ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍን አልፎ በሚገኘው ቅያስ 500 ሜትር ገባ ብሎ፡፡

    ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

    Semonegna
    Keymaster

    አዲስ አበባ (ሰሞነኛ)– የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰቡን ዘርፈ ብዙ የጤና ችግሮች ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ባለድርሻ አካላት በመናበብ እና አቅማቸውን ይበልጥ አጠናክረው መሥራት እንዳለባቸው ተገለጸ።

    የኢንስቲትዩቱ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ማዕከል የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ከየካቲት 18 እስከ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. በኢንስቲትዩቱ አዳራሽ ተካሂዷል።

    የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማው ዋና ዓላማ በሃገር አቀፍ ደረጃ የሕብረተሰብ ጤናን ከማስጠበቅ አንጻር የተሠሩትን በርካታ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ከዕቅድ አኳያ ምን ያክሉን ማሳካት እንደተቻለ፥ በመቀጠልም የታዩ ክፍተቶችን በመለየት በቀጣይ የተሻሉ ዘዴዎችን በመቀየስ ችግሮቹን ለማስወገድ ታስቦ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ነበር።

    የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ወቅት እንደገለጹት አጠቃላይ የሕብረተሰቡን ጤና አደጋዎች ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይቻል ዘንድ ከፌዴራል ጀምሮ እስከ ታችኛው የሕብረተሰብ ክፍል ያለው አስተዳደራዊ መዋቅር ሰንሰለቱን ጠብቆ ጠንካራ የሆነ መስተጋብር ሊፈጥር ይገባል፤ በመሆኑም የክልል ጤና ቢሮዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በጤናው ዘርፍ በቅንጅት እየሠሩ የሚገኙ ሲሆን፥ ይህ መድረክ በዚህ የግማሽ ዓመት የሕብረተሰቡን ጤና ችግሮች ከመፍታት አንጻር የታዩ ጠንካራ ሥራዎች እና ድክመቶችን በመለየት በቀጣይ ለሚሠሩ ተግባራት ላይ የጋራ መግባባት የሚደረስበት በመድረክ ነው ብለዋል።

    ዶ/ር በየነ ሞገስ የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው እንደሀገር ከሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር አንጻር እየሠራን ነው፣ ምን ላይስ እንገኛለን፣ በዚህ ግማሽ ዓመት ምን ዋና ዋና ውጤቶች ተመዝግበዋል የሚሉትን በመፈተሽ በቀጣይ ችግር ፈቺ የሆኑ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የጋራ መግባባት የሚደረስበት መድረክ ነው የተዘጋጀው ሲሉ ተናግረዋል።

    የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ማዕከል ከዕቅድ አንጻር በግማሽ ዓመቱ ያከናወናቸውን ተግባራት፣ በመቶ ቀናት ውስጥ የታቀዱ ተግባራት፣ የነበሩ ጠንካራና አፈፃፀሞችና የነበሩ ክፍተቶች እንዲሁም የነበሩ ስጋቶች፣ ተይዞ የነበረው የበጀት አፈጻጸም፣ ዓለም አቀፍና አገር አቀፍ በሽታዎች ከዕቅድ አንጻር ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ፣ ሀገራዊ የጤና ደህንነት እቅድ፣ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ስጋቶች፣ ተጋላጭነትና ምላሽ ዳሰሳ ጥናት በግምገማ መድረኩ ላይ በዝርዝርና በስፋት ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

    የጤና ሚኒስቴር እና በስሩ የሚገኙ መሥሪያ ቤቶች፣ የኢንስቲትዩቱ የበላይ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች፣ የክልል ጤና ቢሮዎች፣ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር የሥራ ሂደት ኃላፊዎች፣ የዕቅድ ክትትል እና ምዘና ኃላፊዎች እንዲሁም የእናቶችና ህፃናት ቡድን መሪዎች በውይይትና ግምገማ መድረኩ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል።

    ምንጭ፦ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት / ሰሞነኛ ኢትዮጵ

    የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት


    Semonegna
    Keymaster

    የአድዋ ድል ለኢትዮጵያ ነጻነትና ኩራትን፣ በዓለም ዙሪያ በተለይ በአሜሪካዎቹ ሰፋፊ እርሻዎች ለ500 አመታት በባርነት ለተጋዙ ጥቁር ሕዝቦች ደግሞ፥ የማንነት ማረጋገጫ፣ የዘመናት ጭቆናና የስነ-ልቦና ቁስልን አውልቆ የመጣያ የተስፋ ትንሳኤ ሆኖ ነበር።

    ሰለሞን ተሰራ (ኢዜአ)

    በርሊን ከተማ ውስጥ የጀርመን ግዛት አስተዳዳሪ (ቻንስለር)በነበረው ኦቶ ቫን ቢስማርክ (Otto von Bismarck) መኖርያ ሳሎን ፌሽታ በፌሽታ ሆኗል። እለቱ እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር (እ.አ.አ) የካቲት 16 ቀን 1885 ሶስት ወር ሙሉ አሰልቺ ውይይት የተደረገበትና ዋና ዋናዎቹ የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች ተሰብስበው ”አንተ ይሄን ያዝ አንተ ያንን ያዝ” ተባብለው ከወታደራዊ ዘመቻ በፊት አፍሪካን የተቃረጡት።

    በስብሰባው ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነውን የአፍሪካ መሬት የሃሳብ መስመር እያሰመሩ ያለከልካይ ተከፋፈሉት። ከሦስት ወራት በላይ (እ.አ.አ ከኅዳር 15 ቀን 1884 እስከ የካቲት 26 ቀን 1885) ሲካሄድ የነበረው የበርሊን ጉባዔ (Berlin Conference) መደምደሚያ የነበረው ‘የበርሊን ጉባዔ ጠቅላላ ግብአተ ሰንድ’ (በእንግሊዝኛው፥ General Act of Berlin conference) በታሪክ አጥኚዎችና ፖለቲካ ተመራማሪዎች ዘንድ በ አብዛኛው “አፍሪካን የመቀራመት ጉባዔ” (“The Division of Africa” ወይም “Scramble of Africa”) ተብሎ ይታወቃል። በጉባዔው ላይ የጀርመን፣ ኦስትሮ-ሀንጋሪ፣ ቤልጅየም፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ፣ ብሪታንያ፣ ጣልያን፣ ኔዘርላንድስና ፖርቱጋል ተወካዮች ተገኝተዋል።

    አውሮፓውያን አፍሪካን ለመቀራመት በበርሊን ስምምነት ሲያደርጉ፤ አፍሪካዊያን ደግሞ የውጭ ወራሪዎችን ለመከላከል ከዚህ አለፍ ሲልም እርስ-በርሳቸው መተነኳኮስ የጀመሩበት ጊዜ እንደነበር ታሪክ ያስረዳል። ወቅቱ በአራቱም የአህጉሪቷ አቅጣጫዎች የሚገኙ ነገስታት እና የጭፍራ አለቆች በተናጠል ከአውሮፓውያኑ ጋር በገጠሟቸው ውጊያዎች ትርጉም ያለው ስኬት ሳያገኙ፤ አፍሪካውያን በቅኝ ግዛት መውደቅ የጀመሩበት ነው።

    ይህን ተከትሎ ጣልያንም ኢትዮጵያን በቁጥጥሯ ስር ለማድረግ ብትነሳም እምቢተኛው ጥቁር ሕዝብ ማንነቱንና ክብሩን አሳልፎ ላለመስጠት በመወሰኑ ያልተመጣጠነ ውጊያ ቢገጥሙም አሳፍሮ መልሷታል። ዘመናዊ የጦር መሣሪያ የታጠቀው የጣልያን ጦር የቅኝ ግዛት ተልእኮውን እውን ለማድረግ የተመመው በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ በአግባቡ የሰለጠኑ ወታደሮችን ይዞ ነው። ነገሩ እንደታቀደው ሳይሆን ቀርቶ የጣልያን ጦር በአድዋ ድል ተነሳ። ታሪክም ይህን ጦርነት <የአድዋ ጦርነት> (The Battle of Adwa) በማለት፣ ለጥቁር ሕዝቦች ታላቅ መነቃቃትና ተስፋ የሰጠውን የጦርነቱን ድል ደግሞ <የአድዋ ድል> (The Victory of Adwa) ብሎ ሲገዝበው ይኖራል።

    የታሪክ ሊቃውንት እንደሚያስቀምጡት የአድዋ ጦርነት በአፍሪካ ምድርና ታሪክ ከተከናወኑት ጦርነቶች ከፍተኛውን የዋጋና የክብር ስፍራ ይዟል። የሰሜን አፍሪካን በስፋት ይገዛ የነበረው አኒባል የአልፕን ተራሮች ዞሮ የአውሮፓን ኃያል መንግሥት ካሸነፈ ወዲህ (Hannibal’s crossing of the Alps)፣ አንድ አውሮፓዊ ጦር በአፍሪካውያን ጦር ሲሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር። ስለሆነም፣ ጦርነቱ ብዙ መልክና ብዙ ቅጽል ተሰጥቶታል።

    የአድዋ ድል ለኢትዮጵያ ነጻነትና ኩራትን፣ በዓለም ዙሪያ በተለይ በአሜሪካዎቹ ሰፋፊ እርሻዎች ለ500 አመታት በባርነት ለተጋዙ ጥቁር ሕዝቦች ደግሞ፥ የማንነት ማረጋገጫ፣ የዘመናት ጭቆናና የስነ-ልቦና ቁስልን አውልቆ የመጣያ የተስፋ ትንሳኤ ሆኖም ነበር።

    የታሪክ ተመራማሪና ደራሲውፖል ሄንዝ በጻፉት ንብረ ጊዜ፥ የኢትዮጵያ ታሪክ (Layers of Time: A History of Ethiopia, by Paul B. Henze) በተሰኘው የታሪክ ድርሳናቸው “አውሮፓውያን የፈለጉትን ገድለዋል፣ ባሪያ ፈንግለዋል፣ አካባቢን፣ ሀብትን፣ ጉልበትን መዝብረዋል፤ ምክንያቱ በግልጽ ባይታወቅም ‘ኢትዮጵያን በጦር ከማስገበር ይልቅ እንቃረጣት ብለው’ ብሪታኒያ፣ ፈረንሳይና ጣልያን የሦስትዮሽ ስምምነት (Tripartite Agreement) ተፈራርመው አጼ ምኒልክን ‘እወቁልን’ ብለው ጦማር ሰደዋል። አጼ ምኒልክም ‘ስለነገራችሁኝ አመሰግናለሁ፣ ነገር ግን እኔ በሌለሁበት የተወሰነውን አላውቅም’ በማለታቸው ጣልያን ኢትዮጵያን በወረራ ያዘች።

    ወረራውን ለመቀልበስ በአጼ ምኒልክ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት ሰላማዊ ትግል ቢያደርግም የወራሪዎቹ ብልጣብልጥነት ጦርነቱን አይቀሬ አደረገው። ወደ ጦርነት ተገዶ የገባው የኢትዮጵያ የጦር ኃይል በአምባላጌ፣ በመቀሌና በአድዋ በተከታታይ ባደረገው ጦርነት የበላይነት ወስዶ የካቲት 23 ቀን 1988 ዓ.ም. ላይ በአድዋ የድል ባለቤት መሆኑ ተበሰረ። የድሉ ዜና እንደናኘ በአፍሪካ ተስፋ፣ በአውሮፓ ድንጋጤ ፈጠረ። የኢትዮጵያ ድል አውሮፓውያን በዓለም የነበራቸውን ልዕለ ኃያልነት ለመጀመሪያው ጊዜ ጥያቄ ውስጥ ከቷል። ፖል ሄንዝ ”ዛሬ ላይ ሆነን ስናየው” የኢትዮጵያ ድል የአውሮፓ ተሰሚነት የቁልቁለት ጉዞ መነሻ ነበር” ሲሉ በጽሁፍ አስፍረዋል።

    ድሉ ታላቋ ብሪታንያን ኢትዮጵያን በእኩል ዓይን ዓይታ ”የምስራቁን የደቡቡን የምእራቡን ድንበራችንን እንካለል” ብላ በፊርማ እንድታጸድቅ አስገድዷታል። ከዚህ በተጨማሪ በአውሮፓ ቅኝ ግዛት መዳፍ ስር ሲማቅቁ የነበሩትን አፍሪካውያን እና ካሪቢያን ጥቁሮች ለነፃነታቸው እንዲታገሉ ብርታት እና ምሳሌ ሆኗቸዋል። ለጥቁር አሜሪካውያን ምሁራን ከፍተኛ የመንፈስ መነቃቃት እንዲያገኙ አድርጓል።

    የአድዋ ድል (ማለትም፥ በአውሮፓውያን ዘንድ የአድዋ ጦርነት ሽንፈት) በተሸናፊ የአውሮፓ ገዢዎች ዘንድ ቁጭት ፈጥሮ ከ30 ዓመት በኋላ ፋሺዝም በጣልያን ውስጥ ስር እንዲሰድ እና መሪ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም (አይዲዮሎጂ) እንዲሆን ምክንያት ሆኗል። ለኢትዮጵያ ደግሞ የተረጋጋ መንግስታዊ አስተዳደር አስገኝቷል። በዚህ የከሸፈ የቅኝ-ግዛት ዕቅድና የአውሮፓውያን ተስፋፊነት የተደሰቱ ሶሻሊስት አመለካከት ያላቸው ወገኖች በጣልያን፣ በብሪታንያና በፈረንሣይም ነበሩ።

    ዕውቁ የታሪክ ተመራማሪና የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ፕሮፌሰር የነበሩት ሪቻርድ ፓንክረስት እና ሌላው ኢትዮጵያዊ የታሪክ ተማራማሪ ዶ/ር አብዱልሳማድ አህመድ በጋራ በጻፉት ስለ አድዋ ድል በጻፉት መጽሐፍ (Adwa Victory Centenary Conference, 26 February – 2 March 1996) ውስጥ እንዳሰፈሩት የኢጣሊያኑ ክሪቲካ ሶሻሌ (Critica Sociale) ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ፊሊፖ ቱራቲ (Filippo Turati) በወኔና በምልዓት ለእውነት ስለእውነት ጻፈ። “ጣልያን ወደ አድዋና ወደ ሌሎችም ከኢትዮጵያ ጋር ወደ ተደረጉት ጦርነቶች የገባችው፣ ለእንግሊዛውያን አገልጋይና አሽከር ሆና ነው። በዚህም የተነሳ የጣሊያናውያን ሀብትና ደም ያላግባብ ፈሰሰ” ሲል ወረራውን በማውገዝ ድፍረት የተሞላበት ጽሁፉን ማስነበቡን ይገልጻሉ።

    ጋዜጠኛው በጽሁፉ “የጣልያንና የእንግሊዝ መንግሥታት በአፍሪካ ስለተቀዳጁት የቅኝ-ግዛትና የተስፋፊነት ድል እንደጽጌረዳ የፈካ ውሸት እየፈበረኩ ይመጻደቁ እንጂ፣ በእርግጥ ኢትዮጵያ ድል አድርጋለች… ቪቫ ምኒልክ! ቪቫ ኢትዮጵያ!” ሲል አወድሷል።

    በአጼ ምኒልክ መሪነት የኢትዮጵያ ኃይል በጣልያን ወራሪ ኃይል ላይ በአድዋ የተቀዳጀው ድል ድልድይ ሆኖ የጥንታዊቷን ኢትዮጵያ የታላቅነት ክብር ከዘመናዊ ዓለም ጋር ያገናኘ ድልድይ ሆኗል። ታዲያ ይህ ድልድይ በ1890ዎቹ ግንባታው የተጀመረው የተቀረው የአፍሪካ ክፍል በውጭ ኃይሎች አገዛዝ ቀንበር ስር ሲወድቅ ኢትዮጵያውያን ብቻ በተከታታይ የተሰነዘረባቸውን ወረራ በድል ሲመልሱ ነበር።

    በዚያው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያውያን ለውጭ ወራሪዎች የማይንበረከኩ መሆናቸውን ማሳየታቸውን ማስታወስ ይቻላል። በ1870ዎቹ የግብፃውያንን፣ በ1880ዎቹ የመሃዲስቶችን ተደጋጋሚ ጥቃቶች መክተው መልሰዋል። የአድዋ ድል ደግሞ ይህን የነፃነት ቀናዒነት ይበልጥ ከማድመቅ አልፎ የዓለምን ትኩረት ስቧል።

    የአውሮፓ መንግሥታት ዲፕሎማቶቻቸውን ወደአዲስ አበባ እንዲልኩ፣ ከኢትዮጵያ ጋር 19 ድንበርን የሚመለከቱ ስምምነቶችን እንዲፈራረሙ አደረጋቸው ። በአርነት ትግሉ መስክ በቅኝ ግዛት ሥር ለነበሩት እህት የአፍሪካ አገሮች ታጋዮችም ኢትዮጵያ ፋና ወጊ መብራታቸውና የራዕይ ምንጫቸው ነበረች።

    የአድዋ ድል የፓን አፍሪካን ንቅናቄ መሠረት መሆኑን የኢትዮጵያውያንን የአድዋ ውሎ ከዘከሩ የታሪክ ጠበብት መካከል የዋሽንግተኑ የታሪክ ሊቅ ፕሮፌሰር ራየሞንድ ጆናስ፥ “የአድዋ ጦርነት – የአፍሪካውያን ድል በዘመነ ግዛት” (The Battle of Adwa: African Victory in the Age of Empire, by Raymond Jonas” በሚለው መጽሐፋቸው አስፍረዋል፡፡ በዚህ ጽሁፋቸው “የአድዋ ድል ለአፍሪካውያን ቅኝ አገዛዝን ታግሎ መጣል እንደሚቻል ያሳየ፣ የኢትዮጵያንም ታላቅነት ያስመሰከረ” ስለመሆኑ ደጋግመው አውስተዋል።

    ለዚህም ነው የናይጄሪያ ድኀረ ነፃነት የመጀመሪያ ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶ/ር ናምዲ አዚኪዊ (Nnamdi Azikiwe) “ኢትዮጵያ ጥቁር ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርባት አገር ነች። በዚህ ክፍለ አህጉር ላይ የአፍሪካ ቀደምት አባቶች የመሠረቱት መንግሥት የታሪክ ዋቢ ነች። ኢትዮጵያ ከዘመን ወደ ዘመን እየተሸጋገረች ህልውናዋን ጠብቃ መኖሯ የሚደነቅና መደነቅም ያለበት ነው” በማለት የተናገሩት።

    ከአድዋው ድል አርባ ዓመት በኋላ ጣልያን ቂሟን ልትወጣ ወረራ ስታካሂድ በግልጽም ይሁን በተዘዋዋሪ የአውሮፓና የአሜሪካ መንግሥታት ከእሷ ጎን ቆመዋል። በተቃራኒው ድሉ በአፍሪካም ይሁን በተቀረው ዓለም የተቀጣጠለውን የአፍሪካዊነት የትግል ስሜት አነሳስቷል፤ እልህ አጭሯል። በአጠቃላይ መላው ጥቁር ሕዝብ፣ በቁጥር አነስተኛ ቢሆኑም ለፍትህ የታመኑ አውሮፓዊያን ነጮችም ለኢትዮጵያ ያላቸውን ወገናዊነት እንዲያጠናክሩ ጥርጊያውን አመቻችቷል። የነኝህም ጥረት በውጭ የነበረውን ሕዝባዊ ድጋፍ ወደ ኢትዮጵያ ያደላ እንዲሆን አድርጎታል። ባህላዊ እሴቶቻቸውን ያልጣሉ የአፍሪካ ምሁራን ከነበሩባቸው የአህጉሩ ከተሞች፣ ከካርቢያን ደሴቶች፣ ከጥቁር አሜሪካዊያን በኩል ተሰባስበው ወረራው ያጫረባቸውን የመጠቃት ስሜት በይፋ አንጸባርቀዋል።

    ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ለነበሩት የአፍቃሪ ኢትዮጵያዊነት እንቅስቃሴ መሪዎችም የአድዋው ድል የሞራል እርሾ ሆኗቸዋል። ከእንቅስቃሴው ግንባር ቀደም መሪዎች አንዱ ጀምስ ድዋኔ (James Mata Dwane) ግብጽና ሱዳን ውስጥ ያሉትን ክርስቲያን አፍሪካዊያን ሁኔታ ትኩረት ሰጥተው መፍትሄ ይፈልጉለት ዘንድ ለአጼ ምኒልክ ደብዳቤ የፃፉት የአድዋውን ድል ተከትሎ ነበር።

    ስለአድዋ ድል የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ዊንስተን ቸርችል “የካቲት 23 ቀን 1888 የአድዋ ጦርነት ተካሂዶ፥ ጣልያን በኢትዮጵያውያን የደረሰባት ሽንፈት ደረሰባት። (ይህም) ሌሎች ሕዝቦችን የሚነካ ሁለት ውጤቶች አስከተለ፤ አንደኛ፥ ሰሜን አፍሪካ ላይ አውሮፓዊ ክብርን ትልቅ ምች መታው። ሁለተኛ፥ በአውሮፓ ፖለቲካ ማንነት ረገድ የኢጣልያ ዋጋ ወደታች ወረደ” ብለው ጽፈዋል።

    ዊንስተን ቸርችል ስለ ኢጣልያ ሽንፈትና ውጤቱ ከመጻፍ ይልቅ ስለ ኢትዮጵያ ድልና በአፍሪካና በሌሎቹ ጭቁን አገሮች ዘንድ የኢትዮጵያን ማንነት ሽቅብ መናሩን መግለጽ አልፈለጉም። ይህ ሊሆን የቻለው ምናልባትም አድዋ ላይ የተገኘው ድል ለጥቁር ሕዝቦች ከነጻነት ለመውጣት የተስፋ እርሹ በመሆኑ፣ ለአውሮፓውያኑ የቅኝ ግዛቶቻቸውን ሊያጡ የሚችሉበት ጅምር በመሆኑ ሊሆን ይችላል።

    የሆነ ሆኖ አድዋ ላይ የተለኮሰው የድል ችቦ በቅኝ ግዛት ስር ለነበሩት የአፍሪካ አገሮች ቀንዲል ሆኗል። ለዚህም ክብር ለመስጠት 17 የአፍሪካ አገሮች የሰንደቅ ዓላማ ቀለማቸውን ከኢትዮጵያ ወስደዋል። አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ የሆነው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለም ማሊ፣ ጋና፣ ካሜሩን … አገሮች በተለያየ ቅርጽ የአገራቸው መለያ ሰንደቅ አላማ እንዲሆን አድርገዋል።

    Pankhurst, Richard. “”Viva Menelik!”: The Reactions of Critica Sociale to the Battle and to Italian Colonialism” In Adwa Victory Centenary Conference, 26 February – 2 March 1996, edited by Abdussamad Ahmad and Richard Pankhurst, 517-548. Addis Ababa: Institute of Ethiopian Studies, Addis Ababa University, 1998.

    ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

    የአድዋ ድል


    Semonegna
    Keymaster

    አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ አድርጎ ለትውልድ ለማሸጋገር የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተናገሩ።

    የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) እንደዘገብው፥ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የአዲስ አበባን የወንዞችና ወንዝ ዳርቻዎች ማልማት አዲስ ፕሮጀክትን በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት “በተራሮች ከፍታ ላይ የምትገኘው አዲስ አበባ እንደ ስሟ አዲስ ሆና ለትውልድ የምትሸጋገር ውብ ከተማ ማድረግ ይገባል” ብለዋል።

    በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) መሪነት በከተማ አስተዳደሩ አስተባባሪነትና በከተማዋ ነዋሪዎችና በወጣቶች ትብብር ለትውልድ የሚሸጋገር ድንቅ ከተማ መገንባታችንን እንቀጥላለንም ነው ያሉት ኢንጂነር ታከለ። ፕሮጀክቱ ለትውልድ የሚተላለፍ የትውልድ አሻራ ያለበትና ሁላችንም የጋራ እሴቶቻችንን የምናስተላልፍበት በመሆኑ ልንደሰት ይገባል በማለት አጽንዖት ሰጥተዋል።

    ፕሮጀክቱ ከተማዋ እንደስሟ እንድትኖር ወንዞችና የወንዞች ዳርቻዎች ሁሉ የቆሻሻ መናኸሪያ ሳይሆኑ የሰው ልጅ በተለይም ደግሞ ወጣቶች ቁጭ ብለው በመነጋገር ሀሳብ የሚቀያየሩበትና ለቀጣይ ትውልድ የተሻለች የጋራ ሀገር ለመገንባት የሚያስችል መሆኑንም አብራርተዋል።

    ፕሮጀክቱ ከእንጦጦ ተራራ ተነስቶ ፒያሳን አካሎ እስከ ብሔራዊ ቤተመንግስት የሚዘልቅ እንዲሁም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል እስከ ብሔራዊ ቤተመንግስት ገራዥ የሚያልፍ ሆኖ እንደማሳያ የሚጀመር ነው ብለዋል።

    በከተማዋ የተያዘው የልማት የወደፊት ስሌት (strategy) ሕዝቦቿ ከልማቱ ጋር የሚያድጉና የሚበለፅጉ እንዲሆኑ የሚያስችል እንጂ አንዱን የህንፃ ባለቤት በማድረግ ሌላውን ለማፈናቀል የሚሠራ አለመሆኑንም ተናግርዋል ኢንጂነር ታከለ ኡማ።

    የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ በበኩላቸው ከተማዋ ብዙ ታላላቅ ቅርሶች ያሏት፣ አብያተ መንግስት፣ ቤተ እምነቶችና እንደመርካቶ ያሉ የታላላቅ ገበያዎች መገኛ ናት ብለዋል። ከዚህም ባሻገር የኢትዮጵያ ምርጥ ሕዝቦች በፍቅር በአንድነት በደም ተሳስረው የሚኖሩባት ከተማ መሆኗንም አስረድተዋል ኃላፊው።

    ራሳችን ተንፍሰንና ተዝናንተን ቁጭ ብለን የምንወያይበት እነጂ የተጣበበ የአስተሳሰብ መንገድ እንዳይኖረን ሰፋ ያለ የስፍራ አጠቃቀምን የሚያሳዩ የቱሪስት መዳረሻዎች የሉንም ያሉት ኃላፊው፤ ፕሮጀክቱ ለልጆቻችን ልናተርፍላቸው የሚገባ የመዝናኛ፣ የመነጋገሪያና የመናፈሻ ቦታ እንዳለውም ተናግረዋል። ከዚህም ባሻገር ልጆቻችን ሌሎች ሰዎችን ጋብዘው የሚጠቀሙበት የቱሪስት መዳረሻ እንደሚሆንም ተናግረዋል።

    ምንጭ፦ ኢዜአ / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

    ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ


    Semonegna
    Keymaster

    የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ማኅበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር አልማዝ አፈራ በዚህ ፕሮጀክት የተሳተፉ ተመራማሪዎችን ያሉትን ተግዳሮቶች ተቋቁመው ለዚህ በመብቃታቸው ምስጋና ቸረዋቸዋል።

    ደብረ ብርሃን (ሰሞነኛ)– የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ማኅበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ከኢፌዴሪ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ይምሎ ቀበሌ በተቀናጀ የአሳ፣ የዶሮ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ላይ ሲያካሂድ የቆየውን የምርምር ፕሮጀክት አጠናቆ ለዞኑ አስተዳደርና ለአካበቢው ማኅበረሰብ አስረከበ።

    በርክክብ ሥነ-ስርዓቱ ወቅት የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መምህርና መሪ ተመራማሪ ዶ/ር ገዛኸኝ ደግፌ እንደተናገሩት ምርምሩ በትንሽ ቦታ አሳን፣ ዶሮንና አትክልትን አቀናጅቶ ማልማት የሚያስችል የቴክኖሎጅ ዕውቀትን በመጠቀም የአሳ፣ የዶሮና የአትክልት ልማቱን አቀናጅቶ መሥራት እንደሚቻል ነው ብለዋል። በዚህም የዶሮ ኩስን ለአሳዎች ምግብ እንዲውል እንዲሁም “vermicompost” ቆሻሻን ወደ ጠቃሚ ነገርነትና ማዳበሪያነት የሚቀይሩ ትሎችን ለዶሮዎችና ለአሳ ምግብነት እንዲውል የሚያስችል እንደሆነ አብራርተዋል።

    በምስራቅ ጎጃም ዞን ስንዴ አምራች ወረዳዎች ለገበሬዎች የቀረቡላቸው ኮምባይነሮች በምርታቸው ላይ ጉልህ አስተዋጽዖ እያደረጉ ነው

    አቶ ተፈራ ወንድማገኘሁ የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳደሪ እንዳሉት ይህ ለምርቃት የበቃው የምርምር ሥራ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በዞኑ ከሚያከናውናቸው ምርምሮች አንዱ ሲሆን ፣ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፈጻሚነትና በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የገንዘብ ድጋፍ የተሠራ መሆኑን ተናግረዋል። ዋና አስተዳዳሪው አክለው እንዳስታወቁት ይህንን ምርምር በዞኑ በሚገኙ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ለማስፋፋት ትልቅ ኃላፊነትና አደራ የተጣለባቸው መሆኑን አውስተው ለተግባራዊነቱም እንደሚሠሩ ተናግረዋል።

    የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ ባደረጉት ንግግር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸው ከሚደግፋቸው በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በሚባል ደረጃ ከ60 በላይ ምርምሮች መካከል የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አንዱና ውጤታማው በመሆኑ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ በሚችሉ ትናንሽ ፕሮጀክቶች በመደገፍ የሀገራችንን ልማት ማረጋገጥ ይኖርብናል ብለዋል። ይህን ፕሮጀከት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች እንዲተላለፍ ማኑዋልና ስታንዳርድ ተዘጋጅቷል። የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደርም በአማራ ክልል ለሚገኙ ሁሉም ዞኖች እንዲያደርስ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሲሆን በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲሰራጭ አናደርጋለን ብለዋል።

    ዶ/ር አልማዝ አፈራ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ማኅበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት በበኩላቸው በዚህ ፕሮጀክት የተሳተፉ ተመራማሪዎችን ያሉትን ተግዳሮቶች ተቋቁመው ለዚህ በመብቃታቸው ምስጋና ቸረዋቸዋል። እንደ ፕሬዚዳንቷ ገለፃ፥ በሀገራችን እስከ ሁለት ሚሊዮን የሚደርሱ ሥራ-አጥ ወጣቶች መኖራቸው የሚታወቅ ሲሆን እንደነዚህ ዓይነት የምርምር ሥራዎች ደግሞ ወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ በማድረግ ሚናቸው የጎላ ነው ብለዋል። ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲም ብዙ የምርምር ውጤቶች ያሉት ሲሆን እነዚህን ምርምሮች ወደ ፕሮጀክት መቀየር የሚያስችል ተሞክሮ ስለሆነ ይህ ትልቅ ማሳያ ይሆነናል ብለዋል። በመጨረሻም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርንና የኤፍራታና ግድም ወረዳ አስተዳደርን ላደረጉት ድጋፍና ትብብር ምስጋና አቅርበዋል።

    ምንጭ፦ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

    የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተቀናጀ የግብርና ምርምር ፕሮጀክት


    Anonymous
    Inactive

    ቡናን ከምርት እስከ ውጭ ገበያ ያለውን ሂደት በቴክኖሎጂ ለማገዝ ስምምነት ተፈረመ
    —–

    ‹‹ቲታንስ ዲ አፍሪቅ›› በተለያዩ የቴክኖሎጂ ዘርፎች በአፍሪካ ውስጥ የሚሰራ ድርጅት ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ቡናን ከምርት ጀምሮ እስከ ውጭ ገበያ ያለውን ሂደት በቴክኖሎጂ ለማገዝ ተስማምቷል፡፡

    የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ‹‹ከቲታንስ ዲ አፍሪቅ›› ጋር ቴክኖሎጂን የሚጠቀም የግብርና ስራ ላይ በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡

    በዚህ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የግብርና ስራ ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር እቅድ እንደተያዘም ተገልጿል፡፡

    ኢትዮጵያ የቡና አምራች ሀገር ብትሆንም ዘርፉ በቴክኖሎጂ ባለመደገፉ እና እሴት መጨመር ላይ ትኩረት ባለመደረጉ ከዘርፉ የሚገባትን ያክል ተጠቃሚ አይደለችም፡፡

    ይህንን ችግር ለመቅረፍ ዘርፉን በቴክኖሎጂ መደገፍ አስፈላጊ በመሆኑ ነው ድርጅቱ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለመስራት የተስማማው፡፡

    ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ሹመቴ ግዛው እና የቲታንስ ዲ አፍሪቅ ማኒጂንግ ዳይሬክተር ዶክተር ጊልበርት ሳጊያ ተፈራርመዋል፡፡

    ቴክኖሎጂ በሁሉም ዘርፍ የሚገባ በመሆኑ የትኛውንም ስራ በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋማዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እየሰራ መሆኑን ሚኒስቴር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡

    ‹‹ቲታንስ ዲ አፍሪቅ›› አፍሪካ ውስጥ በቴክኖሎጂ የበለፀገ ማህበረሰብ ለመገንባት እየሰራ ያለ ድርጅት ነው፡፡

    ምንጭ፡- የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር

    Semonegna
    Keymaster

    ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ከየካቲት 10 ቀን 2003 (እ.ኤ.አ.) ጀምሮ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችንና አባል ለመሆን ብቁ የሚያድርጓትን የማሻሻያ እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች።

    አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የሚያስችላትን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየሠራች መሆኑን ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

    በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የባለ ብዙ ዘርፍ የንግድ ግንኙነትና ድርድር ዳይሬክተር አቶ ሙሴ ምንዳዬ የዓለም ባንክ የንግድና ክልላዊ ትብብር ዳይሬክተር ጋር ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደትን እና የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና ስምምነትን ለማጽደቅ እያደረገች ባለው እንቅስቃሴ ዙሪያ በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በተወያዩበት ወቅት ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እና በድርድሩ ሂደት የሚገጥሟትን ችግሮች ተቋቁማ ወደ ድርጅቱ እንድትቀላቀል ለማድረግ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

    ምንም እንኳን ኢትዮጵያ በተከታታይ የኢኮኖሚ እድገት ብታስመዘግብም የግል ዘርፉ በኢኮኖሚው ውስት ያለው ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ነው

    አቶ ሙሴ አያይዘው በአሁኑ ወቅት መንግስት በተለይም በአገልግሎት ንግድ ሰጭ ተቋማት ላይ እየሠራቸው ያሉት የማሻሻል (ሪፎርም) ሥራዎች እና የቴሌኮም ድርጅትን የቁጥጥር/ርጉላቶሬ/ መስሪያ ቤት የተለያዩ ዘርፎች ለግሉ ሴክተር ለማስተላለፍ በሚኒስትሮች ምክር ቤት መጽደቁ ሀገሪቷ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የምታደርገውን ድርድር ሊያግዝ የሚችል መልካም አጋጣሚ ነው ያሉ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ በ2011 ዓ.ም. 4ኛውን የሥራ ቡድን ስብሰባ ለማካሄድ የተለያዩ ዶክመንቶችን የማዘጋጀት ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል።

    በዓለም ባንክ የማክሮ፣ ንግድና ኢንቨስትመንት ዳይሬክተር ወ/ሮ ካሮሊን ፍረንድ (Caroline Freund) በበኩላቸው ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በዓለም የንግድ ድርጅት ድርድር እና በአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ዙሪያ የሚሠራቸው ሥራዎች መልካም መሆናቸውን ገልጸው ወደፊት ለሚደረጉ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድርኮች እንዲሁም ዘመናዊና ደረጃውን የጠበቀ ቢሮና መሠረተ- ልማት እንዲኖር ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

    እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን 1995 በ124 አገራት የአባልነት ፊርማ የተመሠረተውን የዓለም ንግድ ድርጅት (World Trade Organization)፣ በአሁኑ ሰዓት ዋና መቀመጫውን ጄኔቭ ከተማ፣ ስዊዘርላን አድርጎ 164 አገራትንም በአባልነት አቅፏል።ኢትዮጵያም የዚህ ድርጅት አባል ለመሆን ከየካቲት 10 ቀን 2003 (እ.ኤ.አ.) ጀምሮ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችንና አባል ለመሆን ብቁ የሚያድርጓትን የማሻሻያ እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች።

    ምንጭ፦ በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
    ——
    ሌሎች ዜናዎች፦

    የዓለም ንግድ ድርጅት


    Semonegna
    Keymaster

    አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – STEMpower የተሰኘ መቀመጫውን USA (ሳሌም፥ ማሳቹሴትስ፣ አሜሪካ) ያደረገ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሒሳብ ትምህርቶችን በዩኒቨርሲቲዎች እየረዳ የሚገኝ ሲሆን በአገራችን 13 ማዕከላትን ከፍቶ በትብብር እየሠራና እየረዳ ይገኛል።

    ድርጅቱ የድጋፍ አድማሱን በማስፋት በኢትዮጵያ ተጨማሪ 10 ማዕከላትን (ሰባት ማዕከላትን በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች፣ ሶስቱን በተለያዩ ከተሞች እ.አ.አ. በ2019) ለመክፈት ከኢፌዴሪ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲሁም ከሰባቱ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የትብብር ስምምነት የካቲት 14 ቀን 2011ዓ.ም. ተፈራርመዋል።

    የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ሂሩት ወልደማርያም (ፕ/ር) STEMpower ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርቶችን ለማበልጸግ እያደረገ ያለውን ትብብር በማመስገን፥ ዩኒቨርሲቲዎችም ዕድሉን በመጠቀም በአግባቡ ማዕከላቱን ማሳለጥ እንደሚጠበቅባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

    አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማስተማሪያ ክፍሎቹ ውስጥ ዲጂታል ሰሌዳዎችን መጠቀም ጀመረ።

    የሳንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አፈወርቅ ካሱ (ፕ/ር) በበኩላቸው ለሰባቱ ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች (አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲአዲግራት ዩኒቨርሲቲአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲጅማ ዩኒቨርሲቲ እና ወሎ ዩኒቨርሲቲ) ማዕከሉን በመጠቀም በአካባቢዎቻቸው ያሉትን የማኅበረሰብ ችግሮች መፍታት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

    የSTEMpower አስተባባሪ ዳይሬክተርና ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ቅድስት ገብረአምላክ፥ “STEMpower ከየት ወዴት?” በሚል ርዕስ ከድርጅቱ አመሠራረት ጀምሮ ዓላማውን፣ አሁን ያለበት ሁኔታ እና የወደፊት ዕቅድ አጭር ማብራሪያ ለተሳታፊዎቹ አቅርበዋል። ለወደፊትም ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር በስፋት እንደሚሠሩ ፣ በ2040 የበለጸገች ኢትዮጵያን ማየት እንደሆነ ገልጸዋል።

    አገራችን ኢትዮጵያ የራሷን የሆነ ጥንታዊ ታሪክና ባህል ያላት አገር እንደመሆኗ ድርጅቱ በማኅበራዊ ሳይንስ ላይም ትኩረት እንዲያደርግ ከተሳታፊዎቹ አስተያየት ተሰንዝሯል።

    የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ማዕከሎቹ በከፍተኛ ትምህርት እና በሳይንስ ትምህርቶች አከባቢ የሚስተዋሉትን ችግሮች በመቅረፍ የአገሪቱን ብልጽግና ከማረጋገጥ ረገድ መልካም ሁኔታ እንደሚፈጥሩ ገልጸዋል።

    ምንጭ፦ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
    ——
    ሌሎች ዜናዎች፦

    STEMpower


    Semonegna
    Keymaster

    ድሬዳዋ (ሰሞነኛ)– ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ያስተማራቸውንና ያሰለጠናቸውን የሕክምና ኮሌጅ ዕጩ ዶክተር ምሩቃንን እና የአርክቴክቸር ትምህርት ክፍል ዕጬ ምሩቃንን በዛሬው እለት የካቱት 16 ቀን 2011 ዓ.ም በደማቅ ሥነስርዓት አስመረቀ።

    የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በኪነ-ሕንጻ በመደበኛ የትምህርት መርሃግብር ለ5 ዓመታት አስተምሮ ካስመረቃቸው 36 የኪነ-ሕንጻ ተማሪዎች መካከል 12ቱ ሴቶች ናቸው። ከኪነ-ሕንጻ ተመራቂዎች በተጨማሪ ዩኒቨርሲቲው የሕክምና ኮሌጅ ለ3ተኛ ጊዜ በሕክምና ዘርፍ ያስተማራቸውን 17 ተማሪዎችንም በሕክምና ዶክተር አስመርቋል።

    የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ማሰገንቢያ የሚውል አስር ሚሊዮን ብር ለገሰ

    የገጠሩን ህብረተሰብ ጤና በመጠበቅ ምርታማነትን ለማሳደግና በኮንስትራክሽን ዘርፍ ያሉ ክፍተቶችን ለማረም ምሩቃን ተግተው መስራት እንዳለባቸው በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ኢብራሂም ዑስማን አሳስበዋል። ከንቲባ ኢብራሂም ዑስማን ለተመራቂዎቹ ዲግሪና በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የተዘጋጀውን ልዩ ሽልማትና ዋንጫ አበርክተዋል።

    ከንቲባው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ተመራቂዎች የቀሰሙትን ዕውቀት ወደ ተግባር በመለወጥና በቁርጠኝነት በመስራት በሀገሪቱ የተጀመረውን ተስፋ ሰጪ የለውጥ እንቅስቃሴ ከዳር ለማድረስ ተግተው ሊሠሩ ይገባል በማለት ተናግረዋል። በተለይ ተመራቂ ሐኪሞች የገጠሩን ህብረተሰብ ጤና በአስተማማኝ መንገድ በመጠበቅ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ለማድረግ ታች ህብረተሰቡ ድረስ ወርደው መስራት እንደለባቸው አሳስበዋል።

    ከንቲባው አክለውም፥ “የኪነ-ሕንፃ ተመራቂዎች የሀገራችን ቀደም የኪነ-ሕንፃ ጥበብን ከዘመናዊው ጥበብና ዕውቀት ጋር በማዋሃድ በሀገሪቱ እየተስፋፋ ያለውን የዘርፉን ዕድገት ማስቀጠል አለባቸው” ብለዋል።

    ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን ያስተላለለፉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ያሬድ ማሞ በበኩላቸው ሁለቱም ሙያዎች ለሀገሪቱ የዕድገት ጉዞ መሳካትና ለማህበረሰቡ መለወጥ የጎላ ጠቀሜታ እንዳላቸው ተናግረዋል።

    በኦሮሚያ ክልል አቦካዶ አምራች ገበሬዎች የተሻሻሉ ዘሮችን በመጠቀም ምርታቸውን ማሳደግ ችለዋል

    የሕክምና ባለሙያዎች ሰብዓዊ ርህራሄና ታታሪነትን ተላብሰው በሕክምና ዘርፍ ልዩ አሻራ ማስቀመጥ እንዳለባቸው በመጠቆም፥ “የሕክምና ባለሙያዎች በቸልተኝነት ሳቢያ የታመሙ ሰዎች በእጃቸው እንዳይጠፉ ምንግዜም ተጠንቀቁ” በማለት አሳስበዋል። በተጨማሪም፥ “የኪነ-ሕንፃ ተመራቂዎች በሀገሪቱ ዕድገት ላይ ትልቅ ሚና መጫወት ይገባቸዋል” ብለዋል።

    የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማኅበር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ዘርዓይ መስፍን በበኩላቸው በምረቃው ላይ ተገኝተው በከፍተኛ ማዕረግ ለተመረቁት ተማሪዎች ሽልማት ሰጥተዋል። የኪነ-ሕንፃ ተመራቂዎች እስከ መጨረሻ በመማርና እውቀትን በማካፈል ከፊታቸው የሚጠብቃቸውን ግዳጅና ብሩህ ተስፋ ለማሳካት ትኩረት ሰጥትው መንቀሳቀስ እንደለባቸው አሳስበዋል።

    ከተመራቂ ሐኪሞች መካከል 3 ነጥብ 8 ውጤት በማምጣት በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቀው ዶ/ር አቤል ወልደጊዮርጊስ በየትኛውም የሀገሪቱ የገጠር ዳርቻ በመጓዝ ወገኖቹን ለመርዳት ዝግጁ መሆኑን ተናግሯል። “ይህም በሕክምናው መስክ የተቸገሩትን ወገኖችን የመርዳት የልጅነት ህልሜ እውን ለማድረግ ያግዘኛል” ብሏል።

    በኪነ-ሕንፃ ዘርፍ 3 ነጥብ 5 ውጤት በማምጣት በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቀችው ወጣት ትርሲት ታምራት በሀገሪቱ እየጎለበተ ባለው የኪነ-ህንፃ ዘርፍ ሙያዊ እውቀቷን በመጠቀም አንዳች አሻራ ለማስቀመጥ መዘጋጀቷን ተናግራለች።

    ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ)/ ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

    ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ


    Semonegna
    Keymaster

    የነዋሪዎች የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት መዘመን በመታወቂያ ማጭበርበርን ለመቀነስ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ሲታመንበት፤ መታወቂያ አሰጣጡ ደረጃውን የጠበቀና በአሻራ የተደገፈ እንደሆነም ተጠቁሟል።

    አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) አዲስ አበባ ዲጂታል የነዋሪዎች መታወቂያ በሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ መስጠት እንደምትጀምር የከተማዋ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ አስታወቀ። በኤጀንሲው የነዋሪዎች አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ አብዱራሂም ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) እንዳሉት ተቋሙ አገልግሎቱን ለማዘመን እየሠራ ነው።

    አዲሱ የዲጂታል መታወቂያ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አገልግሎቱ የሚጀመር ሲሆን ለዚህም በቂ መታወቂያ ካርዶች መዘጋጀታቸውን ነው አቶ መሐመድ ያነሱት። በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የአዲሱ መታወቂያ አሰጣጥ ጥንካሬና ድክመት ታይቶ በቀጣይ በሁሉም ክፍለ ከተማ ወረዳዎች መስጠት ይጀመራል ብለዋል። አዲሱ መታወቂያ የብሔር ማንነትና የትውልድ ቦታ የሚገልጽ ይዘት የሌለው ሲሆን በአንጻሩ የደም ዓይነት እንዲጠቀስ መደረጉም ተገልጿል።

    የልደት፣ የጋብቻ፣ የፍቺና የሞት ወሳኝ ኩነት ምዝገባዎች ከሐምሌ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በአንድ ማዕከል የሶፍትዌር ምዝገባ በዘመናዊ መልኩ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን የአጄንሲው የመረጃ ቅበላና ማስረጃ አቅርቦት ዳይሬክተር አቶ አንተነህ ካሳ ተናግረዋል። ሆኖም የነዋሪዎች አገልግሎት በተበታተነ መልኩና በወረቅት ላይ የተመሠረተ እንደነበር ያነሱት አቶ አንተነህ፥ አሁን አገልገሎቱን ዲጂታል ለማድረግ እየተሠራ ነው ብለዋል።

    በችግሮች የተተበተበው የ አዲስ አበባ ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤቶች (condominium houses) ግንባታና አሰጣጥ ጉዳይ

    የነዋሪዎች የመታወቂያ አገልግሎትን ማዘመን ከከተማ አስተዳደሩ ቁልፍ ሥራዎች አንዱ መሆኑን የጠቀሱት አቶ መሐመድ ለዚሁ ሥራ በጀት ተመድቦለት ዝግጅት መጠናቀቁንም ተናግረዋል። የነዋሪዎች መታወቂያ አገልግሎት መዘመን በመታወቂያ ማጭበርበርን ለመቀነስ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ያነሱት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፥ መታወቂያ አሰጣጡ ደረጃውን የጠበቀና በአሻራ የተደገፈ እንደሆነም ጠቁመዋል። ደኅንነቱ የተጠናከረ የነዋሪዎች መረጃ ምዝገባ ሶፍትዌር፣ የመታወቂያ ማተሚያና የአሻራ መቀበያ መሳሪያዎች መዘጋታቸውንም ተናግረዋል።

    አገልግሎቱ የኢንተርኔት አቅርቦትን የሚፈለግ በመሆኑ የኔትወርክ መቆራረጥ እንዳያጋጥም የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር እየሠሩ ነውም ብለዋል። ነባሩ መታወቂያ በዲጂታል ሙሉ ለሙሉ እስኪቀየር ድረስ የወረቀት መታወቂያ አሰጣጡ እንደማይቋረጥም አቶ መሐመድ ገልጸዋል።

    በጉለሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 3 ነዋሪ አቶ ልዑልሰገድ በላይ እስካሁን ያለው መታወቂያ አሰጣጥ ዘመናዊ አይደለም፤ መታወቂያውም ኤሌክትሮኒክ አለመሆኑ በቀላሉ ለብልሽት ይዳረጋል ይላሉ። ከተማ አስተዳደሩ አሁን የዲጂታል መታወቂያ መስጠት ልጀምር ነው ማለቱ እንዳስደሰታቸው የተናገሩት አቶ ልዑል ሰገድ፥ በፍጥነት ተግባራዊ በማድረግም ማጭበርበርን መቀነስ ይግባል ብለዋል።

    የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት የከተማዋን የትራንስፖርት ችግር መፍታት ያልቻለው ለምን ይሆን?

    የዲጂታል መታወቂያ ሊጀመር መሆኑ ፋይዳው የላቀ መሆኑን የተናገሩት የዚሁ ወረዳ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ጽህፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ውዱ አሰፋ፥ አንድ ሰው የነዋሪነት መታወቂያ አንድ ጊዜ ብቻ እንዲያወጣ በማድረግ የተለያየ መታወቂያ በማውጣት የሚሠሩትን ወንጀል ያስቀራል ብለዋል። በተለይ የጣት አሻራ እና የአይን አሻራ የሚወስድ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም መሆኑ አገልግሎቱን ለማዘመን፣ ለህጋዊ ማስረጃዎች ተዓማኒነት ፋይዳው የላቀ መሆኑን ነው ያነሱት።

    በጉለሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ አንድ ነዋሪ ኮማንደር መሀመድ ሁሴን አዲስ የሚጀመረው መታወቂያ የብሔር ማንነትን ስለማያካትት የብዙ ሰዎችን ጥያቄ እንደሚመልስ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪ መታወቂያው እንበለጸጉት ሀገራት ደረጃውን የጠበቀና ማንም በቀላሉ በሀሰተኛ መንገድ ሊያዘጋጀው የማይችል መሆኑም ሌላው መልካም ጎኑ ነው ሲሉም ገልጸፀዋል።

    በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት የወሳኝ ኩነት ምዝግባና ነዋሪዎች አገልግሎት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መልዓከ ብርሃኑ፥ የነዋሪዎችን አገልግሎት የማዘመን ሂደቱ የግብዓት እና የሠራተኛ እጥረትን ከመቅረፍ መጀመር አለበት ነው ያሉት። የከተማው ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ በቅድሚያ ብቁ የሰው ኃይል፣ ግብዓትና ምቹ የቢሮ ሁኔታ ፈጥሮና አሟልቶ ወደ አገልግሎት እንዲገባም ጠይቀዋል። የነዋሪዎች አገልግሎት አሰጣጥን በቴክኖሎጂ ማዘመን ሰው ሠራሽ ስህተቶችን ለመቀነስ፣ ወንጀሎችን ለመከላከል እንደሚያግዝም ተናግረዋል።

    የወሳኝ ኩነት ምዝግባ የነዋሪዎች አገለግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መሐመድ አብዱራሂም በየወረዳዎቹ የነዋሪዎች አገልግሎትን ለማዘመን ሠራተኞች በተለያየ ዙር እየሰለጠኑ መሆኑን አክለው አስታውቀዋል። በማዕከል ደረጃ አዲስ ለሚጀምረው የነዋሪዎች አገልገሎት አሰጣጥ 20 ብቁ የመረጃ እና ግንኙነት ቴክኖሎጂ (ICT) ባለሙያዎች ከመደበኛ ሠራተኞች በተጨማሪ ተመድበዋል ነው የተባለው።

    ምንጭ፦ ኢዜአ / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

    የዲጂታል መታወቂያ


    Semonegna
    Keymaster

    አዲስ አበባ (ሰሞነኛ)– በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርን የግንባታ አፈፃፀም በፌዴራል ዋና ኦዲተር የተደረገ የክዋኔ ኦዲት መሠረት በማድረግ ይፋዊ ስብሳባ ጥር 27 ቀን 2011 ዓ.ም. አካሂዷል። በስብሰባው ቋሚ ኮሚቴው የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የ11 ዩኒቨርሲቲዎች የግንባታ ፕሮጀክት በተጠና ዕቅድ ላይ ያልተመራ እንደነበረ ገልጿል።

    በኦዲት ሪፖርቱ ግንባታዎቹ በምዕራፍ ተከፋፍለው መቼ እንደሚሠሩ፣ እያንዳንዱ ሥራ ምን ያህል ወጪ እንደሚጠይቅና በአጠቃላይ በመሪ ዕቅድ መሠረት ተግባራዊ ባለመደረጉ በግንባታው ሊሟሉ የሚገቡ የግብዓት፣ የቤተ ሙከራና የመፅሐፍት ግዥ ማሟላት እና የካሣ ክፍያ በተገቢው ሁኔታ መፈፀም አለመቻሉ ተገልጿል።

    በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ11 ዩኒቨርሲቲዎች የግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ደስታ በሰጡት ምላሽ ግንባታዎቹ የ5 ዓመት መሪ ዕቅድ ቢያዘጋጁም በዕቅዱ መሠረት ለማከናወን የበጀት እጥረት በመኖሩ በዕቅዱ መሠረት መፈፀም እንዳልተቻለ፤ የግብዓትና የቤተ ሙከራ እቃዎችን የመንግሰት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በወቅቱ ባለማቅረቡ የተፈጠረ ችግር መሆኑን ገልፀው፥ እንደመፍትሔ ተማሪዎች ወደ አጎራባች ዩኒቨርሲቲዎች ሄደው የቤተ ሙከራ ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ እንደሚገኝ እና የካሣ ክፍያን በተመለከተ ክልሎች የተከፋዮችን ዝርዝር በተሟላ ሁኔታ አደራጅተው የማይልኩና ለተከፋዮቹም በቀጥታ በአካውንታቸው እንዳይገባ የተለያዩ ምክንያቶችን በማስቀመጥ ክፍያው እነሱ በፈለጉት አግባብ መፈፀሙን ተናግረዋል።

    የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ማሰገንቢያ የሚውል አስር ሚሊዮን ብር ለገሰ

    ለዲዛይን መጣጣምና ቁጥጥር ለሚሠሩ አማካሪዎች ክፍያ በበጀት ብር 28,600,000.00 የተያዘ ሲሆን ከአማካሪ ድርጅቱ ጋር ውል ሲፈራረሙ ብር 117,668,636.09 በመሆኑ ብር 89,068,636.09 (311%) በብልጫ መዋዋሉ የኦዲት ግኝቱ አመልክቷል።

    አማካሪዎች ክፍያን በተመለከተ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ተጨማሪ ምላሽ 28 ሚሊዮን ብር በ2008 ዓ.ም. /ለአንድ ዓመት/ ብቻ ለሚከናወን ግንባታ የተገመተ እንደሆነ እና ብር 117 ሚሊዮን ግንባታው በሚቆይባቸው አጠቃላይ ዓመታት የተቀመጠ ወጪ መሆኑን ተናግረዋል።

    ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሚሠራቸው የግንባታ ሥራዎች ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ ከፌዴራል፣ ከክልል፣ ከዞን፣ ከወረዳና ከከተማ አስተዳደሮች ጋር ተቀናጅቶ መሥራት የሚጠበቅበት ቢሆንም ቅንጅት ባለመፈጠሩ ምክንያት የውሃ፣ የመብራትና የስልክ አገልግሎት ችግር ማጋጠሙን፣ የካሣ ክፍያ ተፈፅሞላቸው ከይዞታቸው ያልተነሱ መገኘታቸውን እና በደምቢ ዶሎ፣ በወራቤ፣ በራያ፣ በመቅደላ፣ በአምቦና ቦንጋ ዩኒቨርሲቲዎች ለካሣ ክፍያ በበጀት ለግንባታ ተነሽዎች 100 ሚሊዮን ተይዞ የነበረ ቢሆንም ተከፍሎ የተገኘው 215,071,377.16 መሆኑንና ይህም ክፍያ የብር 115,071,377.16 ብልጫ ያለው መሆኑ ተገልጿል።

    ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅት ከመፍጠር አንጻርም ከክልልና ከከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ ድጋፍና ትብብር በተለያየ ሁኔታ እንደተደረገላቸው፤ የሚመለከታቸውን አካላትን ማወያየታቸውንና አስፈላጊ ክፍያዎችንም ለአገልግሎት አቅራቢ ተቋማት መፈፀማቸውን ገልፀው ነገር ግን በተለይም የኤሌክትሪክ አገልግሎት አስካሁን በተሟላ ሁኔታ ሊያገኙ አለመቻላቸውን የተቋሙ ኃለፊዎች ተናግረዋል።

    በኦሮሚያ ክልል አቦካዶ አምራች ገበሬዎች የተሻሻሉ ዘሮችን በመጠቀም ምርታቸውን ማሳደግ ችለዋል

    በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ የ3,210,218.24 ብር የካሣ ክፍያ ሰነድ ማስረጃ ሳይኖረው መከፈሉን፤ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የግንባታ ሳይት 17 አባወራዎች የግንባታ ካሣ ቢከፈላቸውም አለመነሳታቸው፤ በራያ ዩኒቨርሲቲ የግንባታ ፕሮጀክት ለሚገኙ 35 ካሣ ተከፋዮች ክልሉ በመጀመሪያ አጥንቶ ካፀደቀው ብር 7,347,757.30 ውስጥ ብር 4,049,779.00 በመቀነስ ብር 3,279,978.30 ብቻ የከፈለና ለሌሎች በጥናቱ ውስጥ ለሌሉ 6 ተነሺዎች ብር 399,706.32 ካሣ መከፈሉ በኦዲት ግኝቱ ተገልጿል።

    የካሣ ክፍያ በበጀት ከፀደቀው ሊቀነስ የቻለው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በዕቅድ ያስቀመጠውን የካሣ ተመን እንዲቀንሱ በተሰጣቸው ትዕዛዝ መሠረት መፈፀሙን፤ ካሣ ተከፍሏቸው ከተነሱ በኋላ እንደገና ተመልሰው የሚሠፍሩ ነዋሪዎችን በተመለከተም ተነሺዎች ካሣው አንሶናል፣ ተተኪ ቦታ አልተሰጠንም የሚሉና ሌሎች ምክንያቶችን በማንሳት ተመልሰው የሚሠፍሩ መሆኑን አቶ ሰለሞን ደስታ አስረድተዋል።

    የዩኒቨርስቲዎች ፕሮጀክቶች ግንባታ ለባለይዞታዎች ካሣ ተከፋዮች የግል አካውንታቸው ማስገባት እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣው መመሪያ ቢገልፅም መመሪያው ተጥሶ ለ468 ባለይዞታዎች ለራያ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ ተነሺዎች በጥቅል በደደቢት ብድርና ቁጠባ ሂሣብ ቁጥር ውስጥ እንዲገባ መደረጉ፤ በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ ተነሺዎች ለፍቼ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት መምሪያ፣ ለቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ ተነሺዎች ከፋ ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ግዥ፣ ክፍያና ንብረት አስተዳደር እና ለእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ ተነሺዎች በእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት አጠቃላይ ብር 79,925,769.02 እንዲገባ መደረጉ እና እስከ ህዳር 29/2009 ዓ.ም ድረስ ገንዘቡ ያልተወራረደ መሆኑ ግኝቱ አመልክቷል።

    The Yellow Movement AAU: Speaking up for women and girls – empowering women (Ethiopia)

    ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በሰጡት ምላሽ ካሣ ለባለይዞታዎቹ እንዲከፈል መመሪያ ተዘጋጅቶ በመመሪያው መሠረት ለተነሺዎች ካሣ እንዲከፈል ቢታቀድም ክልሎች በአንድ ጊዜ ገንዘቡ ለተነሺዎች ቢሰጣቸው በዘላቂ አኗኗራቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል በሚልና በሌሎች ምክንያቶች በተነሺዎች በአካውንታቸው ገቢ አለመደረጉን ገልፀዋል።

    የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት በሰጡት አስተያየት ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር አቅዶና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተቀናጅቶ የመሥራት ውስንነት መኖሩን፤ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ አለመደረጉን ገልፀው የግለሰቦች የካሣ ክፍያ ሚኒስቴር መ/ቤቱ በወጣው መመሪያ መሠረት በየግል አካውንታቸው ገቢ ሊደረግ እና የግንባታ ፕሮጀክቶች ከአከባቢው ማህበረሰብ ጋር በተገቢ መጠን ውይይት ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

    ክቡር አቶ ገመቹ ዱቢሶ የፌዴራል ዋና ኦዲተር በሰጡት አስተያየት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የ11 ዩኒቨርሲቲዎችን ለመገንባት ሲያስብ በዕቅዱ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን በተገቢ ሁኔታ ያለየ መሆኑን፤ ከፌዴራልና ከክልል አካላት ጋር ከፍተኛ የቅንጅት ችግር መኖሩን፤ ከግብዓት ጋር በተያያዘ በየዩኒቨርሲቲዎቹ ግቢ ሜዳ ላይ ሣር እየበቀለባቸው ያሉ ግብዓቶች እስካሁንም በመኖራቸው ትኩረት ተሰጥቶ ሊሠራ እንደሚገባ፤ የካሣ ክፍያዎች በተቀመጠው መመሪያ መሠረት ሊፈፀም እና ክፍያዎቹ ለባለመብቶቹ መድረሱን ሚኒስቴር መ/ቤቱ ሊያረጋግጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።

    የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ መሐመድ የሱፍ በኦዲት ግኝቱ የታዩ ችግሮችን በዕቅድ መፍታትና ማረም እንደሚገባ ጠቅሰው ችግሮቹ በሌሎች ተመሳሳይ ግባታዎች እንዳይደገሙ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በትኩረት መሥራት እንዳለበት አሳስበዋል።

    ምንጭ፦ የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

    የ11 ዩኒቨርሲቲዎች የግንባታ ፕሮጀክት


    Semonegna
    Keymaster

    አምቦ (ኢዜአ) – አምቦ ዩኒቨርሲቲ ”ዳክዬ” የተባለ አረምን በምርምር አውጥቶ ለእንስሳት መኖነት ጥቅም ላይ ማዋሉን አስታወቀ። ተቋሙ በተጨማሪም አትክልትን የሚያጠቃ ተባይን ለመከላከል ለአርሶ አደሩ ድጋፍ እየሰጠ ነው።

    ዩኒቨርስቲው በግብርና፣ በጤና፣ በአካባቢ ጥበቃና በሌሎችም ዘርፎች ከ100 በላይ ችግር ፈቺ የምርምር ፕሮጀክቶች አሉት። ከእነዚህ ውስጥ በተለይ ”ዳክዬ” የተባለ አረምን ከአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት ጋር በመተባበር ላለፉት ሦስት ዓመታት ባደረገው ምርምር ውጤታማ መሆናቸውን በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር ብዙነሽ ሚዴቅሳ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ገልጸዋል።

    በምርምር የተገኘው አረም ለመኖነት የሚውለው በመጠለያ ውስጥ ውሃ በተጨመረባቸው ገንዳዎች በማባዛት በማከናወን ከሌላ የእንስሳት ጋር 20 በመቶው ያህሉ በማደባለቅ ነው።

    በኦሮሚያ ክልል አቦካዶ አምራች ገበሬዎች የተሻሻሉ ዘሮችን በመጠቀም ምርታቸውን ማሳደግ ችለዋል

    ገንቢ የሆኑ ንጥረ ነገሮቹን በመያዙ በአሁኑ ወቅት ለወተት ላሞች፣ እንቁላልና ለስጋ ዶሮዎች መኖ በማዋል ውጤታማ መሆናቸውን ዶ/ር ብዙነሽ አስረድተዋል። እስካሁንም መኖውን የሚጠቀሙ ዶሮዎች እንቁላላቸው ከውጭ ዝርያዎች የተለየ፣ የአስኳሉ ቀለም ቢጫና መጠኑም ከፍ ያለ እንዲሁም የወተት ላሞችን ለሰባት ወራት ያህል ምርት ለመስጠትበ ያስችላቸዋል ብለዋል።

    በቀላሉ የሚዘጋጅ በመሆኑ ለእንስሳት መኖ የሚወጣውን ወጪ የሚቀንስ ከመሆኑም በላይ ምርታማነትንም እንደሚጨመር አመልክተው፣ ስለአጠቃቀሙ በማህበር ለተደራጁ ሴቶች ስልጠና ሰጥተው እየተሰራበት መሆኑን ምክትል ፕሬዚዳንቷ ተናግረዋል።

    አትክልትና ሌላውን አዝርዕት የሚያጠቃ ተባይን ለመከላከል ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከውጭ የሚገቡ ኬሚካሎችን ውጤታማነታቸውን በመስክ ሙከራ ተረጋግጦ ሥራ ላይ እንዲውሉ መደረጉንና ለአርሶ አደሩም ድጋፍ እየሰጡ መሆናቸውንም አመልክተዋል።

    ዶ/ር ታደሰ ሽብሩ የዩኒቨርሲቲው ተመራማሪና መምህር ናቸው። በተባይ ምክንያት በተለይ በሽንኩርት፣ ጥቅል ጎመንና ቲማቲም ላይ የሚደርሰው ተጽዕኖ ለመከላከል ለአርሶ አደሩ የመድኃኒት አቅርቦትና የምክር አገልግሎት በነጻ በመስጠት እያገዙ መሆናቸውን ተናግረዋል። በዚህም ውጤታማ በመሆን አገልግሎቱን ለማስፋፋት ጥረት እያደረጉ ናቸው።

    የዩኒቨርስቲው ባለሙያዎች ባደረጉላቸው ድጋፍ ተባይ በአትክልታቸው ላይ ያደርስባቸው የነበረው አሁን መቃለሉን የተናገሩት ደግሞ በምዕራብ ሸዋ ዞን ቶኬ ኩታዬ ወረዳ የደጋ ፍሌ ቀበሌ አርሶ አደር እሸቱ ለሚ ናቸው።

    በአምቦ ከተማ የቀበሌ ሁለት ነዋሪ ወ/ሮ ትዕግስት አበበ በበኩላቸው ከ11 ሴቶች ጋር ተደራጅተው ዩኒቨርሲቲው ባመቻቸላቸው የመኖና የስልጠና ድጋፍ በዶሮ እርባታ ላይ በመሰማራት ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል። በተለይ የዶሮዎቹ እንቁላል ከሽያጭ አልፎ ለልጆቻቸው ምግብነት በማዋል ተጠቃሚ እንደሆኑ ገልጸዋል።

    አምቦ ዩኒቨርስቲ በቀጣይነትም የምርምር ውጤቶችን ለሁሉም የአካባቢው ወረዳዎች ለማዳረስ ሥራውን እንደሚያጠናክር አመልክቷል።

    ምንጭ፦ ኢዜአ / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

    አምቦ ዩኒቨርስቲ ዳክዬ


    Anonymous
    Inactive

    በአዲስ-አዳማ የክፍያ መንገድ ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ተደረገ
    —–

    የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በአዲስ-አዳማ የክፍያ መንገድ ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ።

    በአዲስ-አዳማ የክፍያ መንገድ የተሻሻለው ታሪፍ ከየካቲት 22 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።

    ማስተካከያው በክፍያ ጣቢያና በተሽከርካሪ አይነት የተደረገ ሲሆን ከ2 እስከ 16 ኪሎ ሜትር ለተሽከርካሪ 1 እና 2 የተደረገው የዋጋ ተመን 15 ብር ነው።

    የውጭ ምንዛሪ ጭማሪ መደረጉና ለጥገና የሚውሉ ጥሬ እቃዎች ከውጭ የሚገቡ መሆኑ ኢንተርፕራይዙ ለታሪፍ ማሻሻያው ምክንያት መሆናቸውን ጠቅሷል፡፡

    ይሁን እንጅ የታሪፍ ማሻሻያው መንገዱ ነዳጅና ጊዜን በመቆጠብ ከሚሰጠው አገልግሎት አንፃር ተመጣጣኝና አዋጭ መሆኑንም ነው የገለጸው፡፡

    የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የአዲስ-አዳማ የፍጥነት መንገድን ለማስተዳደር፣ የክፍያ መንገድ አገልግሎት ለመሥጠት፣ መንገዱን ለማስጠገንና ሌሎች ተጓዳኝ ሥራዎችን እንዲሰራ ኃላፊነት የተሠጠው በአዋጅ የተቋቋመ የመንግስት የልማት ድርጅት ነው።

    ምንጭ፦ ዋልታ ሚዲያ

    Anonymous
    Inactive

    100 የአሊያንስ ትራንስፖርት አውቶቢሶች ከስራ ታገዱ
    —–
    አንድ መቶ ያህል የአሊያንስ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ንብረት የሆኑ የከተማ አውቶቡሶች ከስራ ታገዱ፡፡ አውቶቡሶቹ የታገዱት በባንክ የብድር አከፋፈል ስርዓት ላይ በተፈጠረ አለመግባባት እንደሆነም ታውቋል፡፡

    ባለፈው ረቡዕ ከሰዓት በኋላ የአሊያንስ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር የቦርድ ሰብሳቢና አባላት በጌትፋም ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር አክሲዮን ማህበሩ በገባው ውል መሰረት ብድሩን በየወሩ ለመክፈል በአገሪቱ ላይ የተፈጠረው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት፣ አውቶቡሶቹ የሚያስፈልጋቸውን የመለዋወጫ እቃ ከውጭ ለማስመጣት በነበረ የውጭ ምንዛሬ እጥረትና ተያያዥ ችግሮች እንቅፋት በመሆናቸው በውል መሰረት መክፈል አለመቻላቸውንና በዚህም ምክንያት አበዳሪያቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቶዎቹ አውቶቡሶች ስምሪት ላይ እንዳይውል ከጥር 28 ጀምሮ እግድ ማውጣቱን ተናግረዋል፡፡

    ከ2500 በላይ ባለ አክሲዮኖች እና ከ600 በላይ ሰራተኞች ያሉት አሊያንስ ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር፤ በ2005 ዓ.ም 25 ያህል አውቶቡሶችን በመግዛት የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የገለፁት የቦርድ ሰብሳቢው ዶ/ር አዲል አብደላ፣ መንግሥት በ2008 ዓ.ም 500 ያህል የከተማ አውቶቡሶች በግል አንቀሳቃሾች ወደ አዲስ አበባ ገብተው በአዲስ አበባና በዙሪያው ላሉ ከተሞች አገልግሎት እንዲሰጡ የቀረጥ ነፃና የብድር አቅርቦት ባመቻቸበት ወቅት 300 ያህል አውቶቡሶች እንዲገዙ ከመንግስት ፈቃድ ማግኘታቸውን አስታውሰዋል፡፡

    ይሁን እንጂ በወቅቱ የነበራቸው አቅም ከ100 አውቶቡሶች በላይ ማስመጣት ባለመቻሉ መቶዎቹን ብቻ በብድር ገዝተው ወደስራ እንዲሰማሩ መደረጉን ገልፀው ባንኩ የ6 ወር የእፎይታ ጊዜ ቢሰጣቸውም አውቶቡሶቹ ወደ አገር ገብተው ከማለቃቸው በፊት የእፎይታ ጊዜው እንዳለቀና አውቶቡሶቹ በቅጡ ስራ ሳይጀምሩ ባንኩ ብድር ክፈሉ በማለቱ ከሌሎች በጀቶችም ከሌላም እያመጡ መክፈል መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡
    “መቶዎቹ አውቶቡሶች የመንግስት ፕሮጀክቶችና ራሱ መንግስት ታሪፍ ያወጣላቸው እንጂ በንግድ ታሪፍ የሚሰሩ አይደሉም” ያሉት የአክሲዮን ማህበሩ የቦርድ አባላት በአሁን ጊዜ የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ለባንኩ ደብዳቤ በመፃፍ፣ ጉዳዩን የሚያጣራ ኮሚቴ በማቋቋምና ራሳቸውም ከባንኩ ጋር በመወያየት ጉዳዩን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

    ምንጭ፦ አዲስ አድማስ ጋዜጣ

    Anonymous
    Inactive

    ውክልናን በቪድዮ፡ የውክልና ሂደትን በ20 ደቂቃ
    —–

    ኬብሮን ነዋሪነቱ በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ሲሆን ኢትዮጵያ ለሚገኙ ወዳጅ ዘመዶቹ ውክልና ለመስጠት አስቦ ሂደቱን በአሜሪካን ሃገር ቢጀምርም ነገሮች እንዳሰባቸው ቀላል ሆነው አላገኛቸውም። በዚህ ምክንያት የተነሳም የውክልና አሰጣጥ ሥርዓቱን ለመቀየር ቆርጬ ተነሳሁ ይላል፤ ኬብሮን ።

    እንዳለውም አደረገው። የውክልና ሥርዓቱን በማዘመን የሚወስደውን ጊዜ ከወራት ወደ ደቂቃዎች ለማሳጠር ችሏል። እንዴት?

    ኬብሮን ደጀኔ ‘ሲሊከን ቫሊ’ በመባል የሚታወቀው የአሜሪካ ቴክኖሎጂ እምብርት ውስጥ ‘ቪዲቸር’ የሚባል ድርጅት ካቋቋመ አምስት ዓመት ሊሆነው ነው። አሁን ደግሞ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን የውልና ማስረጃን አሠራር ለማፋጠን ትልቅ ሚና ለመጫወት በቅቷል።

    በዛሬው ዕለት በ’ቪዲቸር’ የተደገፈው የውክልና አሠራር በዋሺንግተን ዲሲ ባለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተመርቋል። ለሕዝብ አገልግሎትም ሥራ ላይ እንዲውል ይፋ ተደርጓል።

    የተጓተተ የውክልና ሂደት

    ከሁለት ዓመት በፊት ነበር ከውክልና አሠራር ጋር ኬብሮን ግብ ግብ የገጠመው። በኢትዮጵያ ያለን የንግድ ተቋም ዘመድ እንዲያንቀሳቅስለት በማሰብ የውክልና ሂደቱን ቢጀምርም በካሊፎርኒያና በአካባቢው ውክልና የሚጽፍለትም ሆነ የሚያረጋግጥለት ማግኘት ሳይችል ቀረ። ከስድሰት ሰዓታት የአየር ጉዞ በኋላ በዋሽንግተን ዲሲ ሂደቱን አስጀመረ። ውክልና የመስጠት ተግባሩ ግን ቀላል አልነበረም።

    11 የተለያዩ ነገሮችን ማሟላት ይጠይቅ እንደነበር እንዲሁም በሕግ ባለሙያ አረጋግጦ ቢያንስ 40 ቀናት መጠበቅ ግድ እንሆነ ይናገራል። ከስንት ወጣ ውረድ በኋላ ኢትዮጵያ የደረሰው የውክልና ወረቀት ስህተት አለበት በመባሉ በድጋሚ ለማሠራት መገደዱንም ኬብሮን ይናገራል።

    እንደዚህ ዓይነት ችግሮች መኖራቸውን ከዚህ ቀደም ከብዙ ሰዎች ይሰማ የነበረ ቢሆንም በእርሱ ላይ ከደረሰበት በኋላ አሠራሩን ለመቀየር ቆርጦ እንደተነሳ ይናገራል። በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ‘ቪዲቸር’ መካከል በተደረሰው ስምምነት መሰረት የውልና ማስረጃን አሠራር ለመቀየርና ‘ዲጂታላይዝ’ ወይም ‘አውቶሜት’ ለማድረግም ‘ቪዲቸር’ ለተሰኘው የኬብሮን ተቋም ፈቃድ ተሰጠ።

    ሙሉውን ቢቢሲ አማርኛ ላይ ማንበብ ይቀጥሉ

Viewing 15 results - 541 through 555 (of 730 total)