-
Search Results
-
አዲስ አበባ (ሰሞነኛ)– በ”ለሁሉ” የተለያዩ የክፍያ ማዕከላት የውሃ፣ መብራትና ስልክ ክፍያ ለመፈጸም ሄደው መጉላላት እየገጠማቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪች ገለጹ።
በአዲስ አበባ 34 የሚሆኑ የውሃ፣ የመብራት፣ የስልክና ሌሎች የአገልግሎት መስጫ “ለሁሉ” ማዕከላት ያሉ ቢሆንም ሰሞኑን በአገልግሎት ፈላጊዎች ወረፋ ተጨናንቀዋል። ተገልጋዮቹ የወርሃዊ ክፍያቸውን ለመፈጸም ረዥም ሰልፍ በመያዝ እንግልትና መስተጓጎል እየገጠማቸው መሆኑንም ገልፀዋል።
የኢዜአ ጋዜጠኛም ከ”ለሁሉ” አገልግሎት መስጫ ማዕከላት መካከል በፒያሳ ጊዮርጊስ፣ በአራት ኪሎና ለገሃር አካባቢ በሚገኙ የክፍያ ማዕከላት ተዘዋውሮ ችግሩ መኖሩን ተመልክቷል።
አራት ኪሎ በሚገኘው የክፍያ ማዕከል የተገኙት ወይዘሮ አስካለ ኃይሌ እንደሚሉት ከተወሰኑ ወራት ወዲህ በከተማዋ ባሉ ብዙ የክፍያ ማዕከላት ወረፋና መጉላላት ተባብሷል።
◌ VIDEO: The newly established i-Pro Mobile Assembly Company in Dessie struggling to get building
በአራት ኪሎ የ”ለሁሉ” የክፍያ ማዕከል ክፍያ ለመፈጸም የተገኙት ወ/ሮ ኤልሳቤት ግርማም በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳላቸው ነግረውናል።
በአራዳ ክፍለ ከተማ ኢትዮ-ቴሌኮም ጊቢ ውስጥ በሚገኘው “ለሁሉ” የክፍያ ማዕከል ክፍያ ለመፈጸም የተገኙ ተገልጋዮችም በመስተጓጎላቸው ምሬታቸውን ገልፀውልናል።
ከጉለሌ ክፍለ ከተማ የመጡት ወ/ሮ ብስኩት ይጥና እና አቶ መስፍን ተገነውም የውሃና መብራት ክፍያ ለመፈጸም ማልደው ቢገኙም አገልግሎቱን ማግኘት እንዳልቻሉ ገልፀውልናል።
አገልግሎት የሚሰጡ ሰራተኞች በቁጥር ጥቂት መሆናቸውና “ሲስተም የለም በማለት”፣ ከፍተኛ መጨናነቅ እየተፈጠረ መሆኑንም ጭምር ተገልጋዮቹ ገልፀዋል።
በመሆኑም “ክፍያውን የሚያስፈጽሙልን አካላት ከቴክኖሎጂ ጋር በተጣመረ ቅልጥፍና ሊያስተናግዱን ይገባል” በማለትም ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
ካነጋገርናቸው ተገልጋዮች መካከል ለሦስት ቀናትና ከዚያ በላይ ክፍያ ለመፈጸም እንደተመላለሱ ጠቅሰው ለችግሩ የሚመለከተው አካል አፋጣኝ መፍትሄ እንዲያበጅላቸው የጠየቁም አሉ።
በፒያሳ ጊዮርጊስ አካባቢ የሚገኘው “ለሁሉ” ማዕከል ኃላፊ ወ/ሮ ጽዮን ዮሃንስን እንዲሁም የአራት ኪሎ ክፍያ ማዕከል ሃላፊ ወ/ሮ ወይንሸት ገብረጻዲቅ ችግሩ መኖሩን አምነዋል። ወ/ሮ ጽዮን እንደሚሉት ችግሩ የተፈጠረው ሌላኛው የአራዳ የክፍያ ማዕከል ዝግ በመሆኑ ነው።
እንደ ወ/ሮ ወይንሸት ገለፃ ህብረተሰቡ በጊዜ የመክፈል ልማድ ስለሌለው ወደ መጨረሻው ቀን ክፍያው በሚፈጽምበት ወቅት አንዲህ ያለው መጨናነቅ ይፈጠራል ብለዋል።
ኢዜአ በ”ለሁሉ” የክፍያ መፈጸሚያ ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት ከኃላፊዎች ምላሽ ለማግኘት ቢሞክርም “ከቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር ፍቃድ ያስፈልጋል” በማለት መላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
——
ሌሎች ዜናዎች፦- የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የኤሌክትሮኒክ ግብይት (ኢ-ኮሜርስ) ማዕከል ኢትዮጵያ ውስጥ ሊገነባ ነው
- ቤልካሽ ኢትዮጵያ ሄሎማርኬት እና ሄሎሾፕ የተሰኙ ሁለት የኤሌክትሮኒክስ መገበያያ ገፆችን ሊያስጀምር ነው
- ገበያ የተባለው የግል ድርጅት እና የኢኖቬሽንና ቴክሎጂ ሚኒስቴር ተባብረው ለመሥራት ስምምነት ተፈራረሙ
- ሁለተኛው SolveIT ሀገር አቀፍ የፈጠራ ውድድር (የኢዲስ አበባ ከተማን) በይፋ ተጀመረ ― የአሜሪካ ኢምባሲ
- ቮልስዋገን በኢትዮጵያ የመኪና መገጥጠሚያ ፋብሪካ ሊገነባ ነው፤ የጀርመን የቴክኖሎጂ ድርጅቶች በስፋት ለመግባት እያመቻቹ ነው
ግንባታው በሦስት ዓመት የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚጠናቀቀው የተፈጥሮ ጋዝ ማስተላለፊያ ከኦጋዴን ኢላላና ካሉብ (ሶማሊ ክልል) ተነስቶ ጅቡቲ ወደብ የሚደርስ ሲሆን ጅቡቲ ላይ ነዳጁ ይቀነባበራል።
አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – ኢትዮጵያ ለምትገነባው የተፈጥሮ ጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧ ከጅቡቲ ጋር ስምምነት ተፈራረመች።
በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ መንግስታት መካከል የተፈረመው ስምምነት ኢትዮጵያ ለምትገነባው የተፈጥሮ ጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧ በጅቡቲ ምድር ለማቀነባባሪያ የሚሆን መሬት ለማግኘትና ጥበቃ ለማድረግ የሚያስችል ነው።
ስምምነቱን የፈረሙት በኢትዮጵያ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ሳሙኤል ኡርካቶ (ዶ/ር) ና በጅቡቲ የነዳጅና ተፈጥሮ ሃብት ሚኒስትር ሚስተር ዮኒስ አሊ ጒዲ ናቸው።
760 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው ማስተላለፊያ ቧንቧ ግንባታው 3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚፈጅ ሲሆን 700 ኪሎ ሜትር በኢትዮጵያ፣ 60 ኪሎ ሜትሩ ደግሞ በጅቡቲ ምድር የሚያልፍ ነው።
◌ ALSO: Ethiopia is ready to use Red Sea Ports of Assab and Massawa of Eritrea
ግንባታው በሦስት ዓመት የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚጠናቀቀው የተፈጥሮ ጋዝ ማስተላለፊያ ከኦጋዴን ኢላላና ካሉብ (ሶማሊ ክልል) ተነስቶ ጅቡቲ ወደብ የሚደርስ ሲሆን ጅቡቲ ላይ ነዳጁ ይቀነባበራል።
የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትሩ ዶ/ር ሳሙኤል ኡርካቶ ስምምነቱ የሁለቱን አገራት የረጅም ጊዜ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ግንኙነት እንደሚያጠናክረው ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እየገነባችው ያለው የተፈጥሮ ሃብት መጠቀሚያ መሠረተ ልማት የአገራቱን የጋራ ተጠቃሚነት የሚያጠናክር ነው ብለዋል። በከፍተኛ ድርድር ውሳኔ ያገኘው ይህ ስምምነት ዓለም አቀፍ መስፈርት ያሟላ መሆኑንም ዶ/ር ሳሙኤል አክለዋል።
የጅቡቲው የነዳጅና ተፈጥሮ ሃብት ሚኒስትር በበኩላቸው ስምምነቱ የሁለቱን ወንድማማች አገራት የጋራ ተጠቃሚነት ስለሚያጎለብት ጅቡቲ ጥበቃውን ታጠናክራለች ነው ያሉት። የመሠረተ ልማት ግንባታው በጅቡቲ በማለፉ ከምታገኘው ጥቅም ባሻገር በርካታ ዜጎቿን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።
የተፈጥሮ ጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧውን መቀመጫውን ሆንግ ኮንግ ከተማ ያደረገው ያቻይናው GCL-Poly ኩባንያ እንደሚገነባው ተጠቁሟል። GCL-Poly ኩባንያ የተቋቋመው እ.ኤ.አ በ1996 ሲሆን፥ በተለያዩ የኃይል ማመንጫ ግንባታዎች ላይ የተሰማራው ጎልደን ኮንኮርድ ሆልዲንግስ ሊሚትድ (Golden Concord Group Limited) የተባለው ግዙፍ ድርጅት ቅርንጫፍ (subsidiary) ነው።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
——
ሌሎች ዜናዎች፦
- የጊዳቦ ግድብ ሥራ ፕሮጀክት በዚህ ወር ይመረቃል
- ባለፉት 6 ወራት ለኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 484 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡ ተገለጸ
- የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የኤሌክትሮኒክ ግብይት (ኢ-ኮሜርስ) ማዕከል ኢትዮጵያ ውስጥ ሊገነባ ነው
- አዳማ ከተማ ውስጥ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው እና ጥቅም ላይ የማይውሉ መድኃኒቶችን ማስወገጃ ማዕከል ተገነባ
- ቮልስዋገን በኢትዮጵያ የመኪና መገጥጠሚያ ፋብሪካ ሊገነባ ነው፤ የጀርመን የቴክኖሎጂ ድርጅቶች በስፋት ለመግባት እያመቻቹ ነው
[caption id="attachment_9717" align="aligncenter" width="600"] PHOTO: Ethiopian Broadcasting Corporation[/caption]
አዲስ አበባ (ሰሞነኛ)– ኢትዮ ቴሌኮም 980 ሺህ ብር የሚያወጣ የአምቡላንስ ድጋፍ ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አበረከተ። ድርጅቱ ሠራተኞቹን በማስተባበር አሁን ያበረከተውን አምቡላንስ ጨምሮ በተለያዩ ሰብዓዊ ተግባራት ድጋፍ ለመስጠት ከማኅበሩ ጋር በትብብር እንደሚሠራ አስታውቋል።
የካቲት 4 ቀን 2011 ዓ.ም. በማኅበሩ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተካሄደው ርክክብ ሥነ ስርዓት ላይ የተገኙት አዲሱ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ዋና ፀሀፊ ዶ/ር መሸሻ ሸዋረጋ፣ ኢትዮ ቴሌኮም ላደረገው ድጋፍ ያላቸውን ምስጋና ገልጸው፥ ሌሎች ተቋማትም ይህንን አርአያ እንዲከተሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰብዓዊ ዕርዳታ ፈላጊ ወገኖች መኖራቸውንና እነዚህን ተደራሽ ለማድረግ ለስድስት ወር ብቻ 1.5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የተናገሩት ዶ/ር መሸሻ፥ በዚህ ረገድ ያለውን ክፍተት ለመሙላት የማኅበሩ የበላይ ጠባቂና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዚዳንት አስተባባሪነት የሚመራ ኮሚቴ በማቋቋም ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል ገንዘብ ለማሰባሰብ በዝግጅት ላይ እንገኛለን ብለዋል።
◌ NEWS: Ethio Telecom and Ethiopian Electric Power to cooperate in sharing transmission lines
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ በበኩላቸው፣ ሰብዓዊነት ትልቅ ተግባርና ኃላፊነት በመሆኑ የዚህ ዓላማ አጋር በመሆናችን ደስታ ይሰማናል ብለዋል። የተቋሙ ሠራተኞችም በየወሩ ከደሞዛቸው ከሚያደርጉት የአባልነት መዋጮ ባሻገር በበጎ ፈቃደኝነት በዓመት ሁለቴ የደም ልገሳ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። በሀገራችን ያለውን የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት ማቃለል የምንችለው ስንተባበር በመሆኑ ተቋማት ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ያሉት ወ/ት ፍሬህይወት ተቋማቸው ከማኅበሩ ጋር ተባብሮ በመሥራት በቀጣይም መሰል ድጋፎችን ማድረግ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
የማኅበሩ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቦርድ አባልና የረጅም ዓመታት የቀይ መስቀል ቤተሰብ የሆኑት አርቲስት ፋንቱ ማንዶዬ፣ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች በሰብዓዊ ተግባር ላይ በመሰማራት የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም ከ20 ዓመት በፊት በ1000 ብር የድርጅት አባልነት መዋጮ ጀምሮ በየዓመቱ በማሳደግ ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ በዓመት ለማኅበሩ 100 ሺ ብር ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን ከ15000 በላይ ሰራተኞቹ ደግሞ የቀይ መስቀል መደበኛ አባል በመሆን በወር ከ30 ሺ ብር በላይ ድጋፍ ያደርጋሉ። በተጨማሪም የተቋሙ ሠራተኞች ማኅበር እንደተቋም አባል በመሆን በየዓመቱ የ50 ሺህ ብር ድጋፍ ያደርጋል።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከሚሰጣቸው ሰብዓዊ አገልግሎቶች መካከል ነፃ የ24 ሰዓት የአምቡላንስ አገልግሎት አንዱ ሲሆን በዓመት በአማካኝ በአንድ አምቡላንስ ለ3600 ሰዎች አገልግሎት ይሰጣል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ (ሰሞነኛ)– የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትና የውጪ ምንዛሬ እጥረት ለሀገር በቀል የመድኃኒት እና የሕክምና መገልገያ አምራቾች እውነተኛ ፈተና መሆን አለመሆናቸው በገለልተኛ አካል ሊጠና ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ባለድርሻ አካላት ተናገሩ።
ጥር 24 ቀን 2011 ዓ.ም ከሀገር ውስጥ አምራቾች በተደረገው ውይይት የ6 ወር የመድኃኒት አቅርቦት አፈፃፀም 25% መሆኑን ተከትሎ ለአቅርቦቱ ዝቅተኛ አፈፃፀም በተደጋጋሚ በምክንያትነት የሚሰጡት የውጭ ምንዛሪ እጥረትና የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ በገለልተኛ አካል ተጠንቶ ድጋፍ የሚያስፈልገውን በመደገፍ የሚያጭበረብረውን በማጣራት እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል ሲሉ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ገልፀዋል።
ኤጀንሲው ለሀገር ውስጥ አምራቾች በቅድሚያ ክፍያ እንዲሁም 25 በመቶ ጨረታ ላይ እንዲወዳደሩ እንደሚደግፉ የተጠቀሱት አስተያየት ሰጪዎቹ አሁንም አምራቾች መድኃኒቶችን በበቂ መጠን ጥራት ማቅረብ አለመቻላቸው አጠራጣሪ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
◌ News: Humanwell Healthcare Group inaugurates Humanwell Pharmaceutical Ethiopia PLC in Chacha town
እንደአስተያት ሰጪዎች ገለጻ ሀገር በቀል አምራቾች ኤጀንሲው የሚሰጣቸው የቅድሚያ ክፍያ ሒሳብ በአግባቡ ቃላቸውን ለመተግበር እያዋሉት መሆኑ ወይም ሌላ ዓላማ መዋሉ ሊጠና ይገባል ብለዋል። አክለውም የሚሰጠውን ገንዘብ ለሌላ የግል ንግድ እየተጠቀሙበት መሆኑን ጥርጣሬ እንዳላቸው ገልጸዋል።
በተያያዘ ዜና የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በአዳማ ከተማ የግማሽ ዓመት አቅድ አፈጻጸም ላይ እንዳሉት ሀገር በቀል የመድኃኒት አምራቾች ኤጀንሲው በሚያቀርበው ገንዝብ ለግል አቅራቢዎች ትርፍ ለማሳደድ እንደሚያውሉት መረጃ አለ ሲሉ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም የሚደረገው ድጋፍ በአግባቡ የመያጠቀሙበት ከሆነ በሂደት እየለዩ እርምጃ ለወሰድ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
ከዚሁ ውይይት በተጨማሪ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ የጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል አቅርቦቱን የበለጠ ለማሻሻል ብቻውን መስራቱ ውጤታማ ሊያደርገው እንደማይችል የኤጀንሲው የግዥ ትንበያና ገበያ ጥናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብይ ክፍሎም አብራርተው የሀገር ውስጥ አምራቾቹ ሊያስቡበት እንደሚገባም አቶ አብይ አክለው ገልፀዋል።
◌ News: SanSheng Pharmaceutical PLC inaugurated in the Eastern Industry Zone in Dukem, Ethiopia
የአገር ውስጥ አምራቾች አፈፃፀማቸውን መፈተሽ እንዳለባቸውና አፈፃፀማቸው ዝቅ ባለ ቁጥር በመድኃኒት እጦት የሚያልፈውን የሰው ሕይወት ሊያስቡ እንደሚገባ የመድኃኒትና የህክምና መሣርያዎች ግዢ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጎይቶም ጊጋር ገልፀዋል።
የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ሣሙኤል ኃይሉ በበኩላቸው በአሁኑ ሠዓት የመድኃኒት እጥረት እንደ ቀልድ የሚታይ ጉዳይ አይደለም ብለዋል።
አቅርቦቱ ዝቅ እንዲል ካደረጉ ምክንያቶች መካከል የውጭ ምንዛሬና የመብራት መቆራረጥ በዋናነት በውይይቱ የተጠቀሱ ሲሆን ኤጀንሲው ይህን ለማስተካከል አፈፃፀማቸውን ለመለካት የሚያስችል ነጥቦችን የያዘ ረቂቅ ሰነድ (KPI) ቀርቦ የጋራ ማድረግ ተችሏል።
በመጨረሻም ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ ባንክ፣ የኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት መገኘታቸው በቀጣይ ችግሩን በመቅረፍ የሕብረተሠቡን የመድኃኒት ፍላጎት ለማሟላት ያስችላል ብለዋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
ጎንደር (ሰሞነኛ)– በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እየተተገበረ ለሚገኘው የጤና መረጃ አብዮት ትልቅ የሰው ኃይል የሚፈጥር የቀጠና/ወረዳ ጤና መረጃ ሥርዓት (District Health Information System 2 – DHIS2) አካዳሚ እና የኤለክትሮኒክስ ጤና ፈጠራ ቤተሙከራ (e-health innovation lab) በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግቢ ጥር 30 ቀን 2011 ዓ.ም ተመረቀ።
በምረቃ ፕሮግራሙ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ፣ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አበባው ገበየሁ፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሄልዝ ኢንፎርማቲክስ (Health Informatics) ትምህርት ክፍል የሁለተኛ እና ሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች፣ የአቅም ግንባታ እና የሜንተርሽፕ ድጋፍ ፕሮጀክትን (Capacity Building and Mentorship Project – CBMP) ከሚተገብሩ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ ተሳታፊ መምህራን እና የጤና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
◌ VIDEO: Ethio-American Doctors Group (EADG): Building a regional healthcare system & medical tourism
የምረቃ መርሀግብሩን በንግግር የከፈቱት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ የተመረቀው አካዳሚ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና በተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች እየተተገበረ የሚገኘውን የአቅም ግንባታ እና የሜንተርሽፕ ድጋፍ ፕሮጀክት (CBMP) ለመደገፍ ታስቦ የተከፈተ መሆኑን ገልፀው፤ በተለይ በአማራ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለሚገኙ የጤና ተቋማት የሰው ኃይል በማሰልጠን ትልቅ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። ሀገሪቱ የያዘችውን የጤና መረጃ ሥርዓት በማዘመን የልህቀት ማዕከል ለመሆን ዩኒቨርሲቲው እየሠራ ይገኛል ብለዋል። ለተሳታፊዎች ለፕሮጀክቱ ቡድን አባላት እዲሁም ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና ለክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ምስጋና አቅርበዋል ዶ/ር ደሳለኝ በንግግራቸው መብቂያ።
በሀገራችን የሚታየው የጤና መረጃ አያያዝ ሥርዓት ከማሰባሰብ እስከ መረጃ መተንተን የሚታዩ በርካታ ክፍተቶች ያሉበት በመሆኑ እንደ DHIS2 ዓይነት ሥርዓቶችን መጠቀም ግድ መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር አበባው፥ ዩኒቨርሲቲው በትክክለኛው ሰዓት አካዳሚውን በመክፈቱ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል። ዶ/ር አበባው አያይዘውም ዩኒቨርሲቲው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን መስጠት አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበው የተጀመረው ሥራ እንደሀገርም እንደ ዩኒቨርሲቲም የሚያኮራ ነው ብለዋል።
በአሁኑ ሰዓት 90 በመቶ የሚሆኑ የጤና ተቋማት በDHIS2 ሥርዓት ሪፖርቶችን ማቅረብ መጀመራቸው ከጤና ጥበቃ ሚንስተር የመጡ ኃላፊዎች ተናግረዋል። መሆኑም ተመርቆ የተከፈተው አካዳሚ የጤና ኬላዎችን በመከታተል እና በመገምገም ድጋፍ ማድረግ እንዲሁም ወረዳዎችን በመረጃ አያያዝ ሥርዓት ሞዱል የማድረግ ኃላፊነት እንዳለበት ኃላፊዎች ተናግረዋል።
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር ተቀራርቦ እየሠራ የሚገኘው ሥራ ለሌሎች ተቋማትም አርአያ መሆኑን የገለፁት ተሳታፊዎች፥ የ DHIS2 አካዳሚ በዩኒቨርሲቲው መከፈቱ የዩኒቨርሲቲውን አመራሮች እና አጠቃላይ የዩኒቨርሲቲውን ማኅበረሰብ የሚያኮር ሥራ መሆኑ ገልፀዋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በተያዘው የጤና መረጃ አብዮት ዙሪያ ማብራሪያ የቀረበ ሲሆን፥ ዶ/ር ቢንያም ጫቅሉ በአቅም ግንባታ እና የሜንተርሽፕ ድጋፍ ፕሮጀክት (CBMP) እስካሁን የተሠሩ ተግባራትን እና የወደፊት አቅጣጫዎችን አቅርበዋል። በቀረበው ሀሳብ ላይ ውይይት ተደርጎ መርሀ ግብሩ ተጠናቋል።
District Health Information System 2 (DHIS2) ምን እንደሆነ በዝርዝር ለማንበብ እዚህ ይጫኑ (እንግሊዝኛ)።
ምንጭ፦ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
ወላይታ ሶዶ (ሰሞነኛ)– የወላይታ ልማት ማህበር ለሰው ሀብት ልማት ልዩ የትኩረት ሰጥቶ በሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት የህብረተሰቡን ኑሮ ለማሻሻል በትምህርትና ስልጠና በዕውቀትና ክህሎት የበለጸጉ ዜጎችን ማፍራት ዓላማው አድርጎ የራሱን ጉልህ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
ለዚህም ዓለማ የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት በማቋቋም፣ በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ በማድረግ፣ በትምህርት ጥራት ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት፣ የቅድመ መደበኛ ትምህርት በማስፋፋትና ዕድሜያቸው ለትምህርት ደርሶ በድህነት ምክንያት በትምህርት ገበታ ላይ መገኘት ያልቻሉ ልጆችን ወደ ትምህርት ቤት በማስገባት ሙሉ የትምህርት ቁሳቁሶችን በማሟላት ከእኩዮቻቸው ጋር እኩል ለማድረግ በአንድ ዓመት ከአንደኛ ክፍል እስከ ሦስተኛ ክፍል በማስተማር በዓመቱ መጨረሻ በየወረዳው ትምህርት ጽ/ቤቶች የሚዘጋጀውን ፈተና ተፈትነው ሲያልፉ ወደ መደበኛው አራተኛ ክፍል ተዛውረው ትምህርታቸውን የሚቀጥሉበት ወደ አራተኛ ክፍል በማዛወር የተፋጠነ ትምህርት ለአፍሪካ በተሰኘ ፕሮጀክት እየተገበረ ይገኛል።
◌ ቪዲዮ፦ ደቡብ ግሎባል ባንክ ባለፈው የበጀት ዓመት ከታክስ በፊት ሚሊዮን ብር ማትረፉን አስታወቀ
የወላይታ ልማት ማህበር በሰው ሀብት ልማት ዘርፍ ከሚተገብራቸው ፕሮጀክቶች አንዱ ጀኔቫ ግሎባል ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የሚያከናውነው የተፋጠነ ትምህርት ፕሮጀክት ነው። ይህ ፕሮጀክት ከ2013 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በወላይታ ዞን ውስጥ ከ13,500 በላይ በድህነት ምክንያት ወደ ትምህርት ቤት መግባት ያልቻሉ ህጻናትን ተጠቃሚ አድርጓል።
ፕሮጀክቱ ከትናንትናው ዕለት ጥር 29 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ለፕሮጀክቱ አመቻች የአንደኛ ደረጃ መምህራን፣ ከዳሞት ሶሬ ወረዳ ለተወጣጡ መምህራንና ርዕሰ መምህራን በተግባር ተኮር የመማር ማስተማር ስነዘዴ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ሲሆን ስልጠናው አስከ የካቲት 2 ቀን 2011 ዓ.ም.. እንደሚቆይ በልማት ማህበሩ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ቆርጋ ላምቤቦ ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ በተያዘው በጀት ዓመት በዳሞት ሶሬ ወረዳ አስር ትምህርት ቤቶች በ3 ሚሊዮን ብር በ30 የመማሪያ ክፍሎች ለ900 ህጻናት ሙሉ የትምህርት ቁሳቁሶችን በማሟላት አመርቂ ሥራ እየሠራ ይገኛል።
ከዚህ ጎን ለጎን የእነዚህን ተማሪዎች እናቶች በራስ አገዝ ማህበራት በማደራጀት በመረጡት የገቢ ማስገኛ ሥራዎች ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ በየሳምንቱ ገንዘብ በማስቆጠብና ከራሱ መጠነኛ ድጎማ በማድረግ ገቢያቸውን እንዲያሻሽሉና ወደ ፊት ልጆቻቸው ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ በማድረግ፣ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች አቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠትና የህጻን ለህጻን ትምህርትን በማጎልበት እንደሚሠራ ከፕሮግራም ኦፕሬሽን ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ምንጭ፦ የወላይታ ልማት ማህበር / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
“በርቱ! ባየሁት ነገር ተደስቻለሁ… የሥራ ፍላጎት ተነሳሽነት ለለውጥ ወሳኝ መሆኑን ከጴጥሮስ መረዳት እንችላለን” – የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገብረየሱስ
አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገብረየሱስ የካቲት 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተገኘተው የሥራ እንቅስቃሴን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በቆይታቸውም የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በጋራ ያስገነቡትን የልብ ህክምና ማዕከል፣ በሀገሪቱ ብቸኛና የመጀመሪያ የሆነውን የተመረዙ ሰዎች የሚታከሙበት የቶክሲኮሎጂ ህክምና ማዕከል እንዲሁም የእናቶችና ህጻናት የህክምና ከፍልን ዋና ዳይሬክተሩ ጎብኝተዋል።
በሆስፒታሉ ፈጣን እድገት ተደስቻለሁ ያሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የልብ ህክምና አገልግሎት መስጠት መጀመሩና በሀገሪቱ ካለው የህክምና እጥረት አኳያ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ገልጸው ብዙም ትኩረት ያልተሰጠበት የመመረዝ ህክምና በሆስፒታሉ መሰጠቱም ይበል የሚያሰኝ ነው ብለዋል።
◌ ቪዲዮ፦ የኢትዮጵያዊያን-አሜሪካዊያን ዶክተሮች ቡድን እያስገነባ ያለው ግዙፉ ዓለምአቀፋዊ ሆስፒታል በአዲስ አበባ
ሆስፒታሉ የሰሳንባ ነቀርሳ (ቲቢ) ህክምና ብቻ ይሰጥ እንደነበር ያስታወሱት ዶ/ር ቴዎድሮስ በአሁኑ ሰዓት አጠቃላይ መሠረታዊ የሆስፒታል አገልግሎቶችን መስጠት መጀመሩና የተወሰኑ የህክምና አገልግሎቶች ላይም የበለጠ ስፔሻላይዝድ ለማድረግ መሥራቱ በጣም እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።
ከዚህ ሌላም የሆስፒታሉ ሰራተኞች የሥራ ተነሳሽነትም በጣም እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል። ለሆስፒታሉ ፈጣን ዕድገትም ሁሉም የሆስፒታሉ ሠራተኞች ዋና ተዋናይ መሆናቸውን እንዳዩ ገልጸው በዚህም የሥራ ፍላጎት መኖር ለለውጥ ወሳኝ መሆኑን ከጴጥሮስ መረዳት እንችላለን ብለዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በዚሁ ዕለት የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ከመጎብኘታቸው በተጨማሪም ከየኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢፌዴሪ) የጤና ሚኒስትር አሚር አማን (ዶ/ር) እንዲሁም ከኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር ተገናኝትው በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
ከሰኔ 24 ቀን 2009 ዓ.ም. ቀን ጀምሮ ዋና መቀመጫው ጄነቭ፣ ስዊዘርላንድ የሆነውን የዓለም ጤና ድርጅትን (WHO) በዋና ዳይረክተርነት የሚመሩት ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከዚህ ስልጣናቸው በፊት ከ ከኅዳር 20 ቀን 2005 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 22 ቀን 2009 ዓ.ም. ድረስ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ከጥቅምት 2 ቀን 1998ዓ.ም. እስከ ኅዳር 19 ቀን 2005 ዓ.ም. ደግሞ የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል።
ምንጭ፦ የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
——
ሌሎች ዜናዎች፦- የካንሰር ህክምና አገልግሎት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል
- የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የካንሰርና የልብ ህክምና ማዕከል ግንባታ 56 በመቶ ደርሷል
- ከሆዱ 120 ሚስማር የወጣለት ታካሚ መዳኑ ተገለጸ ― የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
- የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የፎረንሲክ ምርመራ በጋራ ለማከናወን ተስማሙ
- አዳማ ከተማ ውስጥ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው እና ጥቅም ላይ የማይውሉ መድኃኒቶችን ማስወገጃ ማዕከል ተገነባ
አዲስ አበባ (EIAR) – የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የአርሶ አደሩን እንዲሁም አርብቶና ከፊል አርብቶ አደሩን የአገሪቱ ማህበረሰብ ኑሮ የተሻለ ለማድረግ ብሎም የግብርናው ዘርፍ ዘላቂ እድገት እንዲያስመዘግብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
ኢንስቲትዮቱ የገጠሩን ማህበረሰብ ምርታማነት ከማሣደግም ባለፈ በከተማ ዙሪያ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ዘመናዊ የግብርና ዘዴዎችን በማስተዋወቅ አምራች እንዲሆኑ ለማስቻል እየሠራ ይገኛል ። በዚህም በምርምር የሚያወጣቸውን ከአካባቢ ስነ ምህዳር እንዲሁም አየር ንብረት ጋር ተስማሚ የሆኑ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለከተማ አርሶና አርብቶ አደሮች የማስተዋወቅና የማስፋፋት ሥራ ሲሠራ ቆይቷል። ተቋሙ ይህንን እንቅስቃሴ አጀንዳው አድርጎ መሥራት የጀመረው በ2009ዓ.ም ሲሆን በኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ ስርፀትና ኮሜርሻላይዜሽን ምርምር ዳይሬክቶሬትም ይህንኑ ተግባር እያስተባበረ ይገኛል።
◌ ቪዲዮ፦ እየተገነቡ ያሉት የግብርና ማቀነባበሪያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለሀገሪቱ የእርሻ ሴክተር እና ኢኮኖሚ የሚኖራቸው አስተዋጽኦ
ከከተማ ግብርና የሚገኝ ምርት የምግብ ስርዓትን በማሳደግ ጤናማ ማህበረሰብ ለመገንባት አይነተኛ አስተዋጽኦ አለው። ለዚህም እንደ ማሳያ ማህበረሰቡ በአነስተኛ ቦታ ዘመናዊ የግብርና ዘዴዎችን በመጠቀም ለጤና ጠቃሚ የሆኑ የግብርና ምርቶችን በማምረት ለለት ተእለት ፍጆታው ማዋል ሲጀምር የምግብ ደህንነቱ ከመጠበቁም በተጨማሪ በምርቱ ጥራት ላይ የሚኖረው እምነት ይጨምራል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም እንደ ትራንስፖርት፣ የዘመናዊ እህል ማከማቻ ቦታ እጥረት እንዲሁም የገበያ ችግርና የመሣሠሉ በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰቱ የድህረ ምርት ብክነት መንስኤዎችን ለመቀነስ ያስችላል። የከተማው ማህበረሰብ የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኝ በማድረግ ጤናማ ማህበረሰብ መፍጠር ያስችላል፤ በከተሞች የሚኖረው የምግብ ዋስትና ችግር ከእናቶችና ህፃናት ጤና ከፍተኛ የሆነ ትስስር ያለው በመሆኑ የስርዓተ-ምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ አንጻር ከፍተኛ ፋይዳ አለው።
ኢንስቲትዩቱ ለከተማ ግብርና ልማት ሥራ በሚረዱ ቴክኖሎጂዎች ላይ ምርምር እንደሚሠራና ከኢንስቲትዩቱ የወጡ ከነባር የዶሮ ዝርያዎች የተሻለ የምርት ልዩነት የሚሠጡ የዶሮ ዝሪያዎች፤ ከአንድ የወት ላም በቀን ውስጥ ሊገኝ የሚችለውን የወተት መጠን ማሣደግ የቻሉ የተሻሻሉ የላም ዝርያዎች ፤ እንዲሁም የተለያዩ የሠብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ቴክኖሎጂዎችም ወደ ተጠቃሚ ተሸጋግረው ማህበረሰቡ ውጤታማ ምርት ማምረት የሚያስችለውን አሠራር በመዘርጋት የምግብ ደህንነትን ለማስጠበቅ እየሠራ ይገኛል ። በዚህም የማህበረሰቡ አካል የሆኑ በርካታ ሴቶችና ወጣቶች ተጠቃሚ የሚሆኑባቸው የሥራ እድሎችን ይፈጥራል። ይህንንም እንደ መነሻ በመውሠድ ተቋሙ እነዚህን የከተማ ግብርና ሥራዎች ለማስፋፋትና በምርምር ያወጣቸውን የሰብልና እንሠሣት ቴክኖሎጂዎች በስፋት ለተጠቃሚዎች ለማዳረስ ከፍተኛ እንቅስቀሴዎች ሲያካሂድ ቆይቷል።
◌ ቪዲዮ፦ የተሻሻሉ የአቦካዶ ምርቶች ለገበሬዎች መልካም ምርት እየሰጡ ነው
ከኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በምርምር የሚወጡ የሰብል፣ እንስሳትና ተፈጥሮ ሀብት ቴክኖሎጂዎች በመሠረታዊነት የገጠሩን ህዝብ ያማከሉ ቢሆኑም ቴክኖሎጂዎቹ ውጤታማ በመሆን ከፍተኛ ምርት መስጠት ከሚያስችላቸው አየር ንብረትና ሌሎች ተያያዥ ግብአቶች ጋር ተቀራራቢ ስነምህዳር ባላቸው ከተማዎች እንዲሁም ከተማ ቀመስ ለሆኑ አካባቢዎች በቀላሉ እንዲላመዱ በማድረግ የሚታሠበውን ውጤት ማምጣት ይቻላል ። በተለይም የተሻሻሉ የአትክልትና ፍራፍሬ ቴክኖሎጂዎች፣ የእንስሳት መኖ ቴክኖሎጂዎች፣ የመዓዛማና መድሀኒት ሠብሎች፣ የዶሮ ቴክኖሎጂዎች እንዲሁም ከተፈጥሮ ማዳበሪያና አካባቢ ጥበቃ ጋር የተያያዙ ምክረ ሃሳቦችን ለከተማ ግብርናም በቀላል ወጪ እንዲሁም አነስተኛ ቦታ ተግባራዊ መሆን የሚችሉ ናቸው።
የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ከኦሮሚያ ክልል ፊንፊኔ ልዩ ዞን በረህ ወረዳና በዚሁ ወረዳ የተለያዩ ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎችን እያከናወነ የሚገኘው የልማትና የአቅም ግንባታ ማዕከል (Center for Development and Capacity Building – CDCB) ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የአካባበቢውን ማህበረሰብ በማስተባበር አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን የማስተዋወቅና የማስፋት እንዲሁም የቴክኖሎጂ ዘር ብዜት ተግባራትን የማከናወን ኃላፊነት ወስዶ ሲሠራ ቆይቷል። በዚህም በበርህ ወረዳ ሮጌ ቀበሌ የሚገኙ ነዋሪዎችን በክላስተር በማቀናጀት የሰንዴ ቴክኖሎጂ የዘር ብዜት ሥራ ተካሂዷል። በተጨማሪም በአካባቢው የአርሶ አደር ማሳ ላይ የሽብምራ ቴክኖሎጂ ሠርቶ ማሳያ በማከናወን በሌሎች የአካባቢው ማኅበረሰቦች እንዲጎበኝ ተደርጓል። በተመሳሳይም በዚሁ ወረዳ ሞጎሮ ቀበሌ የሚኖሩ የአካባቢው አርሶአደሮችን በክላስተር በማደራጀት የስንዴ ዘር ብዜት ማከናወን የቻሉ ሲሆን፣ በቀበሌው የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከል የተከናወኑ የተለያዩ የግብርና ቴክኖሎጂ ሙከራዎችም ተካሂደዋል። የሰንዴና የጤፍ ሠርቶ ማሳያዎችን፣ የአርሶ አደር ማሰልጠኛ እንዲሁም የዶሮ ምግብ ማቀነባበርያ ማዕከላትም በወረዳው በሚገኝ ለገቦሎ ቀበሌ የተከናወኑ ተግባራት ናቸው።
በግብርናው ዘረፍ የሚሠሩ የተለያዩ የመንግስት ፓሊሲ አውጪዎችን ጨምሮ የግብርና ተመራማሪዎች፣ የዞንና የወረዳ የግብርና ሃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ የአካባቢው አርሶ አደሮች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት በማሳተፍ በከተማ ግብርና ዙሪያ የተሠሩትን ውጤታማ የሆኑ የቴክኖሎጂ ሠርቶ ማሳያና የዘር ብዜት ሥራዎች በመጎብኘትና ውይይት በማድረግ ውጤታቸውን በጋራ ለመገምገምና ግብረመልስ ለማሰባሰብ እንዲሁም በኢንስቲትዩቱ፣ በወረዳውና በCDCB በቅንጅት የተሠሩትን የቴክኖሎጂ ማስተዋወቅና ማስፋት ሥራዎችን በማሳየትና ውይይት በማድረግ ቋሚ የሆነ ትስስር ለመፍጠር የሚረዳ የመስክ ቀን ህዳር 16 ቀን 2011 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ፊንፊኔ ልዩ ዞን በረህ ወረዳ ሮጌ፣ ሞጎሮና ለገቦሎ ቀበሌዎች ተካሂዷል።
◌ VIDEO: Making Ethiopians not only have food per se but nutritious and quality food – Bless Agri Food Lab
የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በኦሮሚያ ክልል ፊንፊኔ ልዩ ዞን የከተማ አካባቢ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ማዕከል በማድረግ በ2010/11 መኸር ወቅት የቴክኖሎጂ አቅርቦት፣ ማስተዋወቅ እና አቅም ግንባታ ስልጠናዎች ሲያከናውን ቆይቷል። እነዚህ ተግባራትም ከምርምር ማዕከል የሙከራ ጣቢያዎች ጀምሮ እስከ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚዎች ድረስ በስፋት በማሳተፍ የተከናወኑ ሲሆን አላማውም አዳዲስና የተሻሻሉ ዝርያዎችን ለተጠቃሚዎች በማቅረብ፣ የመነሻ ቴክኖሎጂ ብዜት ሥራዎችን በማካሄድንና የአቅም ግንባታ ሥራዎችን በማከናወንን በአገሪቱ ውጤታማ የሆነ የከተማ ግብርና ማስፋፋት ነው። ኢንስትቲዩቱ በዘርፉ ውጤታማ ከሆኑ ሀገራት ቴክኖሎጂ፣ እውቀትና ልምድ በመውሰድ ለአገሪቱ ስነምህዳር ተስማሚና ኢኮኖሚያዊ እድገት አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ የሚችሉና ለከተማ ግብርና አመቺ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በመለየት የማላመድ ሥራ በመሥራት ጥቅም ላይ እያዋለ ይገኛል። ለውጤታማነቱም ተቋማዊ ድጋፍ በማድረግ፣ ለተጠቃሚዎች ስልጠና በመስጠት፣ ከስልጠናም በኋላ ተገቢው የቴክኖሎጂ አጠቃቀም በሥራ ላይ እንዲውል ክትትልና ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የገበያ ትስስር በመፍጠር የበኩሉን አስተዋጽኦ እየተወጣ ይገኛል።
ሆኖም የከተማ ግብርና ተግባራት ሂደት ከዚህ በተሻለ ፍጥነት ወደፊት እንዲራመድ ለማስቻል ዘርፉ በቴክኖሎጂና እውቀት ሊታገዝ የሚገባው ሲሆን ተግባራቱም በከተማ ውስጥ ባሉ አነስተኛ ቦታዎችና ተፈጥሮ ሃብት ሊተገበሩ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል ይላሉ በዘርፉ ለረጅም ጊዜያት ያገለገሉ የግብርና ባለሞያዎች። ከዚህ በተጨማሪም የህብረተሰብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን መሠረት ያደረገ ሊሆን እንደሚገባም ይጠቁማሉ። የተጠቃሚዎችን አቅም ሊገነቡ የሚችሉ የልምድ ልውውጥና የግንዛቤ መፍጠር ሥራን ማከናወን ለሥራው ዘለቄታዊነት መፍትሄ ሊሆን እንደሚገባም ይጠቅሳሉ።
በተለይም በዝቅተኛ የእለት ገቢ ራሣቸውን የሚያስተዳድሩ በከተማ አካባቢ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳዩ በቀጥታ በሚመለከታቸው አካላት ቀና ድጋፍ በአነስተኛ ቦታ ማምረትና ህይወታቸውን መቀየር የሚያስችላቸውን መንገድ መፍጠር፤ የተጀመሩትንም ሥራዎች አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት (EIAR) / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ