Search Results for 'ወልቂጤ'

Home Forums Search Search Results for 'ወልቂጤ'

Viewing 16 results (of 16 total)
  • Author
    Search Results
  • Semonegna
    Keymaster

    ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከግብር በፊት ያገኘው ትርፍ ብር 658.75 ሚሊዮን ሲሆን ይህም ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ተመዝግቦ ከነበረው ትርፍ ጋር ሲነጻጸር 13.97 ሚሊዮን ወይም 2.2 በመቶ ዕድገት አሳይቷል።

    አዲስ አበባ (ሰሞነኛ)– በአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እውቅና ካገኙ የግል ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ 19ኛ መደበኛና 17ኛ ድንገተኛ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ኅዳር 22 ቀን 2011 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ አካሄደ።

    በጉባኤው ላይ በቀረበው የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት መሠረት፥ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ የባንኩ አጠቃላይ ሀብት ብር 26.7 ቢሊዮን ደርሷል። ይህም ባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው ብር 21.1 ቢሊዮን ጋር ሲነጻጸር የ26.4 በመቶ ዕድገት ያሳየ ሲሆን፣ ባንኩ ቀጣይነትና ዘላቂነት ያለው ዕድገት ማስመዝገብ መቀጠሉን ያመለክታል።

    ከግብር በፊት ባንኩ ያገኘው ትርፍ ብር 658.75 ሚሊዮን ሲሆን ይህም ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ተመዝግቦ ከነበረው ትርፍ ጋር ሲነጻጸር 13.97 ሚሊዮን ወይም 2.2 በመቶ ዕድገት አሳይቷል። በበጀት ዓመቱ መጨረሻ የባንኩ አጠቃላይ ሀብት ብር 26.7 ቢሊዮን በማድረስ ባለፈው ዓመት ከነበረው ብር 21.1 ቢሊዮን ጋር ሲነጻጸር የ26.4 በመቶ ዕድገት አሳይቷል። በ2010 የበጀት ዓመት መጨረሻ ላይ የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ መጠን ብር 21.6 ቢሊዮን ደርሷል። ይህም አሃዝ ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የብር 5.1 ቢሊዮን ወይም የ30.6 በመቶ ዕድገት የሚያሳይ ነው።

    Nib International Bank announces 658.7 million birr pre-tax profit in the fiscal year

    በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ብድር የወሰዱ 541 ደንበኞችን ጨምሮ እስካሁን ወደ 11,626 የሚሆኑ ደንበኞች በተለያዩ ወቅቶች ለተለያዩ ዓላማዎች የብድር ተጠቃሚ ሆነዋል። በዚሁ መሠረት በ2010 በጀት ዓመት የባንኩ የብድር መጠን ወደ ብር 13.5 ቢሊዮን ያደገ ሲሆን ይህም አሃዝ ካለፈው ዓመት ተመመሣሣይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የብር 2.8 ቢሊዮን ወይም 26.5 በመቶ ዕድገት አሳይቷል።

    በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የባንኩ አጠቃላይ ካፒታል ብር 3.4 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ይህ አሃዝ ካለፈው ዓመት ተመሣሣይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የብር 414.5 ሚሊዮን ወይም የ14 በመቶ ዕድገት አሳይቷል። በበጀት ዓመቱ የባንኩ የተመዘገበ/የተፈረመ ካፒታል ብር 2.2 ቢሊዮን፣ የተከፈለ ካፒታል ደግሞ ብር 2.2 ቢሊዮን ደርሷል።

    ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ያለውን ጠንካራ መሠረት ለመጠበቅ እንዲቻል የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት፣ አራት ኪሎ የሚገኘው፣ በሆሳዕናና በሐዋሣ ከተሞች የሚገኙት ሕንጻዎች የግንባታ ሥራ በማፋጠን ላይ ሲሆን፤ በወልቂጤና በዱከም ከተሞች አስገንብቶ ያስመረቃቸው ሕንፃዎችም የተለያዩ አገልግሎቶችን ለመስጠት በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ። የባንኩ ቋሚ ንብረት በባለፈው ዓመት ከነበረበት ብር 495.6 ሚሊዮን ወደ ብር 1.9 ቢሊዮን ማደጉንም በስብሰባው ላይ ተገልጿል።

    ምንጭ፦ NibBankSC.com
    ——
    ተመሳሳይ ዜናዎች፦

    ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ


Viewing 16 results (of 16 total)