Search Results for 'ኤልሳቤት ገብረሥላሴ'

Home Forums Search Search Results for 'ኤልሳቤት ገብረሥላሴ'

Viewing 1 results (of 1 total)
  • Author
    Search Results
  • Anonymous
    Inactive

    ሴቶች በቴክኖሎጂ ዘርፍ የሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ ለማድረግ ታሳቢ ያደረገው የሶፍትዌር ማበልፀግና የሥራ ፈጠራ ስልጠና በይፋ ተጀመረ።
    —–
    የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና እንጦጦ ፌሎሺፕ በጋር በመተባበር ባዘጋጁት በዚህ ስልጠና ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተወጣጡ 25 ሴቶች ይሳተፋሉ።

    ስልጠናው ከካናዳ በመጡ የዘርፉ ምሁራኖች የሚሰጥ ሲሆን ከስልጠና በኋላ ወደ ሥራ መግባት የሚያስችላቸውን እውቀት ይዘው እንዲወጡና ሥራ እንዲፈጥሩ ይደረጋል።

    የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ዳይሬክተር ወ/ሮ ኤልሳቤት ገብረሥላሴ የዓለምን ኢኮኖሚ እየመራ ባለው የቴክሎጂ ዘርፍ ውስጥ ሴቶች ጉልህ ሚና እንዲጫወቱ ሚኒስቴሩ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

    የእንጦጦ ፌሎውሺፕ መስራችና ሥራ አስኪያጅ ዌንጌላዊት ተካ ፕሮግራሙ አጋጣሚውን በቀላሉ ማግኘት የማይችሉ ሴቶችን በሶፍትዌር ማብልፅግና ሥራ ፈጠራ ላይ ተሰማርተው ራሳቸውን እና ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ ለማድግ የተዘረጋ መሆኑን ተናግረዋል።

    3ወር በሚፈጀው በዚህ ስልጠና የሚሳተፉ ሴቶች አብዛኞቹ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ኑሯቸውን የሚመሩ ናቸው።
    በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ላይ አምባሳደር ገነት ዘውዴ ልምዳቸውን ለሰልጣኖቹ አካፍለዋል።

    ምንጭ፦ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር

Viewing 1 results (of 1 total)