Search Results for 'የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን'

Home Forums Search Search Results for 'የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን'

Viewing 5 results - 1 through 5 (of 5 total)
  • Author
    Search Results
  • Anonymous
    Inactive

    በአገራችን ላይ ሊቃጡ የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችን አስቀድሞ በመከላከል እና ቢከሰቱም እንኳን የከፋ ጉዳት ከማድረሳቸዉ በፊት በአፋጣኝና በአጭር ጊዜ ምላሽ በመስጠት ረገድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ዓይነተኛ ሚናን መጫወት ችሏል።

    አዲስ አበባ (ኢመደኤ) – የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ባሳለፍነዉ 2011 በጀት ዓመት በተለያዩ ቁልፍ የሀገሪቱ ተቋማት እና መሠረተ ልማቶች ላይ ሊፈጸሙ የነበሩ 791 የሚደርሱ የሳይበር ጥቃቶችን (cyber-attacks) ማክሸፍ መቻሉን ገለጸ።

    በኢመደኤ የኢትዮጵያ ሳይበር የድንገተኛ ዝግጁነት እና ምላሽ ሰጪ ዲቪዥን (Ethiopian Cyber Emergency Readiness & Response Team – ETHIO CERT) ኃላፊ የሆኑት አቶ አብርሃም ገብረጻዲቅ እንደገለጹት፥ በአገራችን ላይ ሊቃጡ የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችን አስቀድሞ በመከላከል እና ቢከሰቱም እንኳን የከፋ ጉዳት ከማድረሳቸዉ በፊት በአፋጣኝና በአጭር ጊዜ ምላሽ በመስጠት ረገድ ኢመደኤ ዓይነተኛ ሚናን መጫወት መቻሉን ገልጸዋል። ኃላፊዉ ጨምረዉ እንደገለጹት በ2011 በጀት ዓመት በአገሪቱ ላይ የተቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን አስቀድሞ መከላከል በመቻሉ ሊደርስ ከነበረው የደኅንነት እና የገንዘብ ኪሳራ በድምሩ ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት ማዳን መቻሉን የገለጹ ሲሆን፤ ከዚህም በላይ በገንዘብ የማይተመን ሰላምን እና ፍትህ ማስጠበቅ ተችሏል ብለዋል። በቀጣይ 2012 ዓ.ም. በጀት ዓመት አገራዊ የሳይበር ጥቃትን የመከላከል ሽፋን በማሳደግ እና ዓለም አቀፍ ትስስርንና ቅንጅትን በማጠናከር የአገሪቱን ቁልፍ የሳይበር መሠረት ልማቶችን ደህንነት የማስጠበቅ ሥራ እንደሚሠራም ኃላፊዉ ገልጸዋል።

    በኢመደኤ የኢትዮጵያ ሳይበር የድንገተኛ ዝግጁነት እና ምላሽ ሰጪ ዲቪዥን በኢትዮጵያ የሳይበር ሥነ-ምህዳር የሚገኙ የሳይበር መኃረተ ልማቶችን ከጥቃት ከመከላከልና ምላሽ ከመስጠት ባለፈ የሳይበር ደህንነት ክፍተት ትንተና (vulnerabilities) በማከናወን የሳይበር ጥቃት አስቀድሞ የመከላከል፣ የሳይበር ጥቃቶች ከመፈጠራቸው በፊት የማስቀረት፣ የተፈጠሩት ሳይበር ጥቃቶች ከጥቃቱ በፊት ይሠሩበት ወደነበረው ይዞታቸው የመመለስ እና በተመሳሳይ ጥቃት እንዳይጠቁ የደኅንነት ክፍተታቸውን እንዲደፈን የማድረግ፤ እንዲሁም ከዓለም አቀፍ የሳይበር ጥቃት መከላከያ ተቋማት ጋር በቅንጅትና በትስስር ሥራዎችን የሚሠራ ክፍል ነዉ።

    ምንጭ፦ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

    ኢመደኤ


    Anonymous
    Inactive

    እነዚህን የተከለከሉ የምግብ ምርት ዓይነቶች ዝርዝራቸውን በማውጣት ምርቶቹን ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸውና ተቆጣጣሪ አካላት ምርቶቹን በአፋጣኝ ከገበያ ላይ ባለስልጣኑ ጥሪውን አቅርቧል።

    አዲስ አበባ (ኤፍ.ቢ.ሲ.) – የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን 57 የምግብ ምርት ዓይነቶችን ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀም አሳሰበ።

    ባለስልጣኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በላከው መግለጫ በምግቦቹ ጥራትና ደኅንነት ላይ ባደረገው የገበያ ጥናት የምግብ ምርቶቹ መሰረታዊ የገላጭ የፅሁፍ ክፍተት ያለባቸው፣ የሚመረቱበት ቦታ የማይታወቅ፣ የንጥረ ነገር ይዘት የሌላቸው፣ አምራች ድርጅቶቹ የማይታወቁ፣ የምርት መለያ ቁጥር፣ የተመረቱበት ጊዜ እና የምርቱ ማብቂያ ጊዜ ገላጭ ፅሁፍ የሌላቸው ናቸው ብሏል።

    ከዚህ ጋር ተያይዞም ምርቶቹን ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸውና ተቆጣጣሪ አካላት ምርቶቹን በአፋጣኝ ከገበያ ላይ እንዲሰበስቡም ጥሪውን አቅርቧል።

    የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ሕብተረሰቡ እንዳይጠቀማቸው የተከለከሉ የምግብ ምርት ዓይነቶች ዝርዝር፤

    • የከረሚላ ምርቶች፦
      • ጆሊ ሎሊፖፕ፣
      • አናናስ ከረሚላ፣
      • ኮላስ ከረሚላ፣
      • ኦሊ ፖፕ፣
      • ቤስት ከረሚላ፣
      • የስ ከረሚላ (ኮፊ ከረሚላ)፣
      • ማሚ ሎሊ ፖፕ፣
      • ሳራ ከረሚላ፣
      • ጃር ሎሊ ፖፕ፣
      • ጸሃይ ሎሊ ፖፕ፣
      • ዩኒክ ሎሊ ፖፕ፣
      • እንጆሪ ከረሚላ፣
      • ብርቱካን ከረሚላ፣
      • ይናቱ ሎሊ ፖፕ እና
      • ሃላዋ ከረሚላ፤
    • የማር ምርቶች፦
      • አፍያ የተፈጥሮ ማር፣
      • ሪትም ማር እና
      • በላይ ማር፤
    • የገበታ ጨው፦
      • ዊዲ የገበታ ጨው፣
      • ሱላ የገበታ ጨው፣
      • ናይ የገበታ ጨው፣
      • ሃያት የገበታ ጨው፣
      • አቤት የገበታ ጨው፣
      • በእምነት የገበታ ጨው፣
      • እናት የገበታ ጨው፣
      • አባይ የገበታ ጨው፣
      • አባት የገበታ ጨው፣
      • ሴፍ የገበታ ጨው እና
      • ጣዕም የገበታ ጨው፤
    • የለውዝ ቅቤ፦
      • ደስታ የለውዝ ቅቤ፣
      • አስነብ የለውዝ ቅቤ፣
      • ኑኑ የለውዝ ቅቤ፣
      • አቢሲኒያ የለውዝ ቅቤ፣
      • ብስራት የለውዝ ቅቤ፣
      • ፈሌ የለውዝ ቅቤ፣
      • ሳባ የለውዝ ቅቤ፣
      • አዳ የለውዝ ቅቤእና
      • አደይ የለውዝ ቅቤ፤
    • የኑግ ዘይት፦
      • አደይ አበባ የኑግ ዘይትእና
      • ቀመር የኑግ ዘይት፤
    • አልሚ የህጻናት ምግቦች፦
      • ምሳሌ የህጻናት ምግብ፣
      • ኤልሞ የልጆች ምግብ፣
      • ሂሩት የህጻናት አጃ፣
      • ዘይነብ የህጻናት አጥሚት፣
      • ተወዳጅ ገንቢ የህጻናት አጥሚት፣
      • ተወዳጅ የህጻናት ሽሮ እና
      • ፋሚሊ ሃይል ሰጭና ገንቢ የህጻናት ሽሮ፣
    • ሌሎች የተከለከሉ የምግብ ምርት ዓይነቶች፦
      • ቪንቶ፤ ዴኮ፣ እስፔሻል፣ ዳና፣ ቃና፣ ላራ፣ ዛጎል አቼቶ፣ ናይስ አቼቶ፣ አምቴሳ አቼቶ፣ ማይ አቼቶ፣ መስ አቼቶ እና ቫይኪንግ አቼቶ ምርቶች

    እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን የምግብና ምግብ ነክ ምርቶች ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ታግደዋል። ባለስልጣኑ ከሦስት ሳምንታት በፊትም 46 የብቃት ማረጋገጫ የሌላቸው የታሸጉ የምግብ ምርቶች ላይ እርምጃ መውሰዱንና፤ ሕብረተሰቡም እንዳይጠቀማቸው መከልከሉን መዘገባችን ይታወሳል። ዘገባውንና የተከለከሉትን የምግብ ዓይነቶች ዝርዝር ለማግኘት እዚህ ጋር ይጫኑ

    ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ./ ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

    የተከለከሉ የምግብ ምርት ዓይነቶች


    Semonegna
    Keymaster

    አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – የአምራች ድርጅቶቻቸው አድራሻና ምንጫቸው የማይታወቁ እንዲሁም የብቃት ማረጋገጫ የሌላቸውን የምግብ ምርቶች ገበያ ላይ እየዋሉ መሆኑን የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ባደረገው የገበያ ቅኝት ማገኘቱን አስታወቀ።

    ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ድርጅቶች ተመርተው ወደ ገበያ በተሰራጩ ምርቶች ላይ በተደረገ የገበያ ቅኝት በብሔራዊ ደረጃ የተቀመጠውን መስፈርት ያላሟሉ፣ ምንም ዓይነት ገላጭ ጽሁፍ የሌላቸው፣ የአምራች አድራሻ እና መለያ ቁጥር የሌላቸው የሕፃናት ምግብ፣ የለዉዝ ቅቤ፣ የምግብ ዘይት፣ የምግብ ጨውና ማር ገበያ ላይ መገኘታቸው በተደረገው የቁጥጥር ሥራ የተገኘ ሲሆን ባለስልጣኑ አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል።

    በመሆኑም ህብረተሰቡ ከታች ስማቸው የተገለጹትን የሕፃናት ምግቦች፣ የለዉዝ ቅቤ፣ የምግብ ዘይት፣ የምግብ ጨውና ማር ምርቶችን እንዳይጠቀማቸው እያሳሰበ፤ ተመሳሳይ ምርቶች በሌሎች አካባቢ የመገበያያ ስፍራዎች ሊኖር ስለሚችሉ ህብረተሰቡ በአቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቆጣጣሪ፣ ለፖሊስ አካላት ወይም በፌደራል ደረጃ ለባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ በነጻ ስልክ መስመር 8482 በመጠቆም እንዲያሳውቅ ጠይቋል።

    በማያያዝም የክልል ተቆጣጣሪዎችና በየደረጃው የሚገኙ የቁጥጥር አካላት ምርቶቹን ከገበያ ላይ በአፋጣኝ የመሰብሰብ ሥራውን እንዲሠሩ ባለስልጣን መሥሪያቤቱ ጥሪውን አቅርቧል።

    ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው የተከለከሉ የምግብ ምርቶች ዝርዝር

    የሕፃናት ምግቦች
    1. ፍቅር ምጥን
    2. ማስ የሕፃናት ምግብ
    3. ተወዳጅ ኃይል ሰጪና ገንቢ የሕፃናት ምግብ
    4. ስሚ የሕፃናት ምጥን ገንፎ
    5. ፋሚሊ ኃይል ሰጪና ገንቢ የሕፃናት ምግብ
    6. አባድር
    7. ሂሩት ሕፃናት ሂሩት ባልትና
    8. አዩ ለልጆች የተዘጋጀ ምጥን ምግብ
    9. ምቹ 100% ተፈጥሯዊ ይዘቱን የጠበቀ የሕፃናት ምግብ
    10. ፍቅር ኑሪሺ ዩር ቤቢስ ፍቅር/Nourish your babies Fiker

    የምግብ ጨው
    1. ሸዋ የገበታ ጨዉ/Shoa table salt
    2. Greep iodized salt
    3. SNAME iodized table salt
    4. አባተ አዮዲን ጨው/ Abate iodized salt
    5. Refined and iodized Woef table salt
    6. ምርጥ የገበታ ጨዉ
    7. አቤት የገበታ ጨዉ

    የለዉዝ ቅቤ
    1. ኤደን የለዉዝ ቅቤ
    2. ጽጌ የለዉዝ ቅቤ
    3. ፀዬየ ለዉዝ ቅቤ
    4. ማቲፍ የለዉዝ ቅቤ
    5. ምሥራቅ የለዉዝ ቅቤ
    6. ታደለ ንጹህ የለዉዝ ቅቤ
    7. ምእራፍ የታሸጉ ምግቦች
    8. ህብረት የለዉዝ ቅቤ
    9. ደስታ የለዉዝ ቅቤ
    10. ሳራ የለዉዝ ቅቤ
    11. ሰን ናይት የለዉዝ ቅቤ
    12. አቢሲኒያ የለዉዝ ቅቤ

    የምግብ ዘይት
    1. ጸደይ የምግብ ዘይት
    2. ኑር
    3. ኦሜጋ
    4. ቅቤ ለምኔ
    5. ሰብር የኑግ ዘይት
    6. ያሙ የምግብ ዘይት
    7. ሜራ የኑግ ዘይት
    8. ፍፁም የተጣራ የኑግ ዘይት
    9. ቀመር የምግብ ዘይት
    10. ኔግራ የምግብ ዘይት
    11. ከበለመን የምግብ ዘይት

    ማር ምርት
    1. ሃበሻ ንጹህ የተፈጥሮ ማር
    2. ተርሴስ ማር
    3. ንጹህ ማር
    4. ኢትዮ ማር
    5. ማስ የጫካ ማር
    6. ራይት ማር

    ምንጭ- የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን/ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን/ ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

    የተከለከሉ የምግብ ምርቶች


    Anonymous
    Inactive

    የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒት እና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን አገልግሎቱን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዘመኑን ይፋ አደረገ
    —–

    የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒት እና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን የምግብና መድኃኒት ፈቃድ አሰጣጥ፣ የመድሃኒት ግዢ ፈቃድ፣ የምግብና መድኃኒት የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰጣጥን ቀልጣፋና ግልፅ የሚያደርግ ዘመናዊ አሰራርን መተግበር ጀምሬያለሁ ብሏል፡፡ዛሬ በሒልተን ሆቴል በተካሄደው የአገልግሎቱ ማስታወቂያ መርሃ ግብር ተገኝተን እንደሰማነው እስካሁን በማኑዋል የነበረው የተቋሙ አሰራር በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ታግዞ የተሻለ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

    eRIS የተባለው ኤሌክትሮኒክ የቁጥጥርና የመረጃ ስርዓት ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ የምግብና የመድኃኒት ምርቶችን ደህንነት የማረጋገጥ ስራውን የሚያሻሽል ነው ተብሏል፡፡የምዝገባ ሥርዓቱን ማዘመን የመድሃኒት አቅርቦት እጥረትን ለመቀነስ ያስችላል የሚል ተስፋም ተጥሎበታል ተብሏል፡፡ የካቲት 20 ቀን 2011 ዓም ይፋ የተደረገው ዘመናዊ አሠራር በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር አዋጅ አንድ አካል መሆኑንም ሸገረ ኤፍ ኤም ራድዮ ዘግቧል፡፡

    ምንጭ፦ ሸገረ ኤፍ ኤም ራድዮ

    Semonegna
    Keymaster

    አዳማ (ኢዜአ)–የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒት እና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን 22 ነጥብ 78 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው ህገ-ወጥ መድኃኒቶች እንዲወገዱ ማድረጉን አስታወቀ።

    ባለፉት ስድስት ወራት በጤና አገልግሎት ግብአቶች ላይ ቁጥጥርና ፍተሻ ተደርጎ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ መድኃኒትና የህክምና መገልገያ መሣርያዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ መደረጉም ተመልክቷል።

    በባለስልጡኑ የፕሮጀክትና ፕላን ማስተባበሪያ ዳይሬክተር ወ/ሮ ዓለም እሸቴ እንዳሉት መስፈርቱን ያላሟሉና ህገ ወጥ የሆኑ መድኃኒቶች ጥቅም ላይ እንዳይውሉና በአግባቡ እንዲወገዱ የተደረገው ባለፉት ስድስት ወራት ነው። መደኃኒቶቹ የተያዙት በመውጫና መግቢያ ኬላዎች ላይ በተደረገ የቤተ-ሙከራ ፍተሻ እንዲሁም በኦዲቲንግ ኢንስፔክሽን ወቅት መሆኑንም ጠቁመዋል።

    ከውጭ ሀገር የሚገቡ መድኃኒቶችን ጥራት፣ ደኅንነትና ፈዋሽነታቸውን ለማረጋገጥ ባለስልጣኑ ከዓለም አቀፍ የፖሊስ ድርጅትና ሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካለት ጋር በመተባበር የቁጥጥር ሥራ ማከናወኑንም ገልጸዋል። በቶጎ ውጫሌ፣ ሞያሌ፣ ቃሊቲ፣ መተማና ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ባለስልጣኑ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።

    ወ/ሮ ዓለም አንዳሉት በግማሽ በጀት ዓመቱ የምግብ ጥራትና ደህንነት ቁጥጥር ውጤታማነትን ለማሻሻል በተደረገው እንቅስቃሴም 2ሺህ 389 ሜትሪክ ቶን ዱቄት፣ ሩዝ፣ አኩሪ አተርና የምግብ ጥሬ እቃ ተይዟል።

    “በተደረገ ፍተሻም ምግብና ጥሬ እቃው የመጠቀሚያ ጊዜው በመቃረቡ፣ አምራች ካምፓኒው ባለመታወቁ፣ በጉዞ ወቅት በደረሰ ጉዳትና በነቀዝ በመባላቱ ምክንያት ወደመጣበት አገር እንዲመለስ ተደርጓል” ብለዋል።

    በተጨማሪም ከ200 ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው ፓስታ፣ ዱቄት፣ ዘይት፣ ብስኩት፣ ጁስ፣ ሩዝ፣ ወተት፣ ፍራፍሬና የምግብ ጥሬ እቃዎች በተለያየ ምክንያት በመበላሸታቸውና አስፈላጊውን መስፈርት ያላሟሉ ሆነው በመገኘታቸው ከንግድ ተቋማት ውስጥ ተሰብስበው እንዲወገዱ መደረጉን ነው ያስረዱት።

    ዘይት፣ ጨው፣ የዱቄት ወተት፣ ጁስና ሌሎች 15 አይነት የምግብ ናሙናዎች ላይ በተካሄደ የቤተሙከራ ምርመራ ሰባቱ መስፈርቱን ሳያማሉ በመቅረታቸው ምርቱ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ መደረጉን አስረድተዋል።

    “በመንፈቅ ዓመቱ በጤና አገልግሎት ግብአቶች ላይ ቁጥጥርና ፍተሻ ተደርጎም 4 ነጥብ 23 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው መድኃኒትና የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ተደርጋል” ብለዋል። ዋጋቸው ከ457 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የውበትና የንጽህና መጠበቅያ ምርቶችም ቁጥጥርና ፍተሻ ተደርጎላቸው ሀገር ውስጥ እንዲገቡ መደረጉን አስረድተዋል።

    የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሪት ሄራን ገርባ በበኩላቸው ህገ-ወጥ የጤና አገልግሎትና ግብአቶችን ለመቆጣጠር ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ በስሩ ስድስት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችንና 17 የመውጫና መግቢያ ኬላዎችን በማደራጀት እየሠራ ይገኛል።

    በየደረጃው በሚደረጉ የቁጥጥር ሥራዎች ህዝቡን ተሳታፊ ለማድረግ በተለያዩ የህዝብ ንቅናቄ መድረኮች ላይ ህዝብን የማስገንዘብ ሥራ መሠራቱን ወ/ሪት ሄራን ገልጸዋል። በእዚህም ህገ ወጥ የምግብና የመድኃኒት ንግድን እንዴት መከላከል እንደሚቻልና በዘርፉ ቁጥጥር አለማድረግም በሀገር ላይ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ህብረተሰቡ እንዲገነዘበው የማድረግ ሥራ እየተሠራ መሆኑን አመለክተዋል።

    ዳይሬክተሯ እንዳሉት በቁጥጥር ሥራው ካጋጠሙ ችግሮች መካከል የምግብ ቤተሙከራ አለመጠናከር፣ የባለሙያዎች አቅም ውስንነት፣ የባለድርሻ አካላትና የህዝብ ክንፉ ተሳትፎ የተደራጀና የተቀናጀ አለመሆን ይጠቀሳሉ። ይህንን ችግር ለማቃለል የባለስልጣኑን አዋጅ የመከለስ ሥራ እየተጠናቀቀ ሲሆን ከምግብና መድኃኒት ጋር የተጣጣመ የአደረጃጀት ትግበራ፣ የሰው ኃይል ድልድልና የህግ ማዕቀፎች ዝግጀት መደረጉንም አመልክተዋል።

    ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ 

    ህገ-ወጥ መድኃኒቶች


Viewing 5 results - 1 through 5 (of 5 total)