Home › Forums › Semonegna Stories › ሜድ ኢን ኢትዮጵያ (በኢትዮጵያ የተሠራ) – ኢትዮጵያውያን ዲዛይነሮች አገራቸውን ለማስተዋወቅ የሚጠቀሙበት አማራጭ
- This topic has 0 replies, 1 voice, and was last updated 6 years, 3 months ago by Semonegna.
-
AuthorPosts
-
October 17, 2018 at 11:06 am #8121SemonegnaKeymaster
ኢትዮጵያውያን የፋሽን ዲዛይነሮች ለዓለም ገበያ የኢትዮጵያን ምርት ይዘው ሲወጡ ምርቱን ብቻ ሳይሆን ሜድ ኢን ኢትዮጵያ በሚለው ሳያሜ ኢትዮጵያዊነትንም በማስተዋወቅ ደረጃ ጉልህ አስተዋጽዖ አያደረጉ እንደሆነ እንደሚሰማቸው ይናገራሉ።
አዲስ አበባ (ኢዜአ)– ኢትዮጵያውያን ዲዛይነሮች በኢትዮጵያ የተመረተ ሜድ ኢን ኢትዮጵያ በተሰኘው መለያ አገራቸውን ለማስተዋወቅ ተስፋ ሰንቀዋል።
ዲዛይነር ሳምራዊት መርሲኤሓዘን ኢትዮጵያ ውሰጥ የተሰራ ሜድ ኢን ኢትዮጵያ የተሰኘ መለያን የያዙ ቦርሳዎችና ሌሎች የቆዳ ውጤቶችን በማምረት አገሯን የማስተዋወቅ ራዕይ ይዛ እየሰራች ትገኛለች።
በእንስሳት ሃብት ከአፍሪካ ቀዳሚ እየተባለች ለዘመናት የምትታወቀው ኢትዮጵያ ከቆዳ ውጤቶች እምብዛም አለመጠቀሟ ዲዛይነር ሳምራዊትን ያስቆጫታል። እንደ እርሷ አገላለጽ አሁንም ቢሆን በቁጭት ከተሠራ በእንስሳት ሃብት ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ በተመረቱ የቆዳ ውጤቶች አገርን ለማስጠራት ጊዜው አልረፈደም።
ለዚህ የእርሷ የቆዳ ቦርሳ፣ ምንጣፍና ሌሎች ምርቶች ተደራሽ በሆኑባቸው አገራት ያለውን ተቀባይነት በማንሳት ታብራራለች። ለዓለም ገበያ የኢትዮጵያን ምርት ይዛ ስትወጣ ምርቱን ብቻ ሳይሆን ሜድ ኢን ኢትዮጵያ በሚለው ሳያሜ ኢትዮጵያዊነትንም እየሸጠች መሆኑን እንደሚሰማት ነው የተናገረችው።
ሥራዋን ከጀመረች ስድስት አመታትን ያስቆጠረችው ዲዛይነሯ፤ ጀርመን፣ ጃፓንና ሆላንድ ምርቷን ከምታቀርብባቸው አገሮች መካከል ሲሆኑ በቀጣይም የዱባይና እንግሊዝ ገበያን ለመድረስ ዕቅድ አላት።
የውጭ ገበያን ሰብሮ ለመግባት መጀመሪያ የራሳችንን መቀበልና የራሳችንን ማድነቅ መጀመር አለብን የሚል ሃሳብም አንስታለች።
በቆዳ ምርቶች ያደጉ አገሮች ለዲዛይን፣ ለአሠራርና አጨራረስ የሚጠቀሙበትን ዘዴ ልምድ በመውሰድ መወዳደር አለብን የሚል እሳቤም አላት ዲዛይነር ሳምራዊት።
“በውጭ ባህል ጥገኛ ከመሆን የብሔር ብሔረሰቦችን የአለባበስ ስርዓት ከዓለም አቀፍ ፍላጎት ጋር በማመጣጠን መለያ በማድረግ ልንታወቅበት የምንችል የገበያ ዘርፍ ነውም” ስትል ትገልጻለች።
የቀደምት ኢትዮጵያውያን እናቶች መገለጫ ከሆነው “ፈትል” በተሠሩ የአገር ባህል ልብሶችም ኢትዮጵያን ለዓለም ለማስተዋወቅ ተስፋ ማድረጋቸውን “የፈትል ዲዛይነር” ሽያጭ ሠራተኛ ወጣት ፌቨን ተስፋዬ ትናገራለች።
የኢትዮጵያ ፈትል በማንኛውም ሰዓት ሊለበስ በሚችል መልኩ በማምረት አሜሪካን ጨምሮ ሌሎች አገሮች ምርቱን ካገኙ በጉጉት እንደሚወስዱ ታዝባለች። ልብሱ የተሠራበት ጥሬ እቃ ከፈትል መሆኑ በተለያዩ አገራት አድናቆትን እያገኘና ባህልን እያስተዋወቀ መሆኑንም ፌቨን ትናገራለች።
ሌላዋ አስተያየት ሰጪ ዲዛይነር ቁንጅና ተስፋዬ ዘወትር የሚለበሱ የኢትዮጵያን ባህል የሚገልጹ ልብሶችን በመሥራት ለአገር ውስጥና ለውጪ ገበያ በማቅረብ ላይ ትገኛለች።
ቪድዮ፦ የኢትዮጵያ አልባሳትና ባህላዊ ዲዛይኖች የዓለም ገበያን ሰብረው እንዲገቡ ለማድረግ ብዙ መሠራት አለበት
የምትሠራቸው አልባሳት የኢትዮጵያን አንዱን ብሔረሰብ አለባበስ በሚገልጽ መልኩ በመሆናቸውም በእያንዳንዱ ልብስ የኢትዮጵያ ብሔረሰቦችን ባህል እያስተዋወቀች መሆኗን ተናግራለች።
ከዚህ በፊት በዓለም ላይ የተሰሩት የአለባበስ ዲዛይኖች እየተደጋገሙ በመሆናቸውና አሁን አሁን እነሱ በሠሩት ዲዛይን መሠረት ዓለም ወደ አፍሪካ ፊቱን እያዞረ መሆኑን በመግለጽ ይህን ዕድል አገራችንን ለማስተዋወቅ መጠቀም አለብን የሚል አስተያየትም ሰጥታለች።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ)
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.