Home › Forums › Semonegna Stories › ሰናይ መልቲሚዲያ ከሕዝብ፣ ለሕዝብ፣ በሕዝብ የሚቋቋም ሳተላይት ቴሊቪዥን!
Tagged: ሰናይ መልቲሚዲያ, ሰናይ ቲቪ
- This topic has 0 replies, 1 voice, and was last updated 5 years, 7 months ago by Semonegna.
-
AuthorPosts
-
June 20, 2019 at 12:26 am #11149SemonegnaKeymaster
ሰናይ መልቲሚዲያ በበሳል ባለሙያዎችና በፕሬስ እድገት ውስጥ ከፍተኛ ሚና በተጫወቱ አንጋፋና ወጣት ጋዜጠኞች አስተባባሪነት የተቋቋመ የሕዝብ የሚዲያ ነው።
ትላንት፣ ዛሬ እና ነገን እንደ ድልድይ የሚያስተሳስር ፣ የኢትዮጵያን ታሪክ፣ የዛሬን ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት አስገብቶ፣ ነገ ላይ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር የሚረዱ አዳዲስ መርሀግብሮችን (ፕሮግራሞች) እና አቀራረቦችን ማስተዋወቅና አሁን በሥራ ላይ ያሉ የመገናኛ ብዙኃን ክፍቶችን መሙላት ዋንኛ ዓላማዉ በማድረግ፣ ሕዝብ በእኩልነት ሃሳቡን መግለጽ የሚቻልበት ሚዲያ ነው። ለዚህም “ሰናይ” ብለን ብዙኃኑ ባለው አቅሙ የድርሻው ባለቤት ሆኖ የእኔ የሚለውን ታላቅ የመልቲሚዲያ ተቋም ይፋ ለማድረግ እንወዳለን።
ሰናይ መልቲሚዲያ የሕዝብ፣ ለሕዝብ፣ በሕዝብ የሆነ የመጀመሪያ ሚዲያ፤ እያንዳንዱ ዜጋ ያለብሔር ልዩነት፣ ያለጾታ፣ ያለእድሜና ክልል ገደብ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሰናይ ቴሌቪዥን (ሰናይ ቲቪ)፦
- የተሻለ ፕሮግራም የሚሰራበት የራሱ ቲቪ አክስዮን ባለድርሻ ይሆናል ፤ምርትና አገልግሎት የሚያስተዋውቅበት ቲቪ አክስዮን ባለድርሻ ይሆናል፤የመረጃ፣ የቁም-ነገር እና የመዝናኛ ፍላጎትንና ጥምን የሚያረካ ቲቪ አክስዮን ባለድርሻ ይሆናል፤
- የሰናይ ቲቪ የመጀመሪያው የሕዝብ ሚዲያ ኔትወርክ (network) ሲሆን በመጀመሪያ በቴሌቭዥን ሳተላይት ስርጭት ጀምሮ በመቀጠል ወደ ሬድዮ፣ ድረ-ገፅ እና በሶሻል ሚዲያ (social media) የሚያካትት ይሆናል፤
- በሰናይ ቲቪ እያንዳንዱ ዜጋ ካለበት ቦታ የኔ በሚለው መልኩ በቀጥታ እንዲሳተፍና እቅድ ውስጥ መካተት የሚችልበትን ሁኔታ ይፈጥራል፤ እውነተኛና ነፃ አማራጭ ሚዲያ ይሆናል። ድምፅ አልባ ለሆነውም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሃሳቡን በነፃነት የሚገልጽበት መንገድ ይከፈታል፤ የተለያዩ አመለካከቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት ጭምር ይሆናል።
ሰናይ መልቲሚዲያ የተመሰረተው እየታሰሩ፣ እየተፈቱ ለሕዝብ መሰዋዕትነት ሲከፍሉ በቆዩ ነባር የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኞች አስተባባሪነት፤ ብዙኃኑ ሕዝብ ሊገዛው በሚያስችል መልኩ ሰላሳ አምስት ሺህ (35,000) አክስዮኖችን በማቅርብ ሲሆን፤ እያንዳንዳቸው አንድ ሺህ ብር ዋጋ ያላቸው በአጠቃላይ የሰላሳ አምስት ሚሊዮን ብር ዕጣ ለሽያጭ አቅርበዋል። በዚህም መሰረት የአንድ አክስዮን ዋጋ 1,000.00 (አንድ ሺህ) ብር ሲሆን፤ ዝቅተኛውና አንድ ሰው ሊገዛ የሚችለው የአክስዮን መጠን 5,000.00 ብር (አምስት ሺህ ብር) ዋጋ ያላቸው አምስት ዕጣዎች ሲሆን፤ አንድ ሰው ሊገዛ የሚችለው ከፍተኛው የአክስዮን ብር መጠን 2,800,000.00 ( ሁለት ሚሊየን ስምንት መቶ ሺህ ብር) ዋጋ ያላቸው 2,800 ( ሁለት ሺህ ስምንት መቶ) የአክስዮን ዕጣዎች ናቸው። ይህ ማለት፤ ማንም ወገን ከስምንት ከመቶ በላይ አክስዮን አንዳይገዛ ገደብ አለበት። ሰናይ መልቲሚዲያ በአንድ ወገን ቁጥጥር ስር እንዳይወድቅ የሚደረግበት ማዕቀፍ ተበጅቷል።
ሰናይ ቲቪ የማንኛውንም የፖለቲካ ወገንተኝነትን የማያስተናግድ፣ የግለሰቦች የፖለቲካ እምነት የማያንጸባርቅ፣ ፍጹም ገለልተኛ ሚዲያ ነው። በመሆኑም፤ ማንኛውም ሰው፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና የሃይማኖት ተቋማት በስተቀር፣ የአክስዮን ባለድርሻ መሆን ይችላል። ለበለጠ መረጃ የፕሮጀክት አማካሪውን “ጌት አማካሪዎች” (GET Business & Investment Consultants) የንግድና ኢንቨስትመንት ማማከር፣ ድርጀቱን በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ-ቁጥር +251 (011) 8 12 12 33/34 በመደወል መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።
ምንጭ፦ ጌት አማካሪዎች/ ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.