Home › Forums › Semonegna Stories › በኢትዮጵያ ህግ ሺሻ ማጨስ ህገ-ወጥ ነውን?
- This topic has 0 replies, 1 voice, and was last updated 6 years, 3 months ago by Semonegna.
-
AuthorPosts
-
September 30, 2018 at 6:24 am #7815SemonegnaKeymaster
በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች አዲስ አበባ ላይ መታሰራቸው በተለይም ከሺሻ ቤቶችና ጫት ቤቶች መወሰዳቸው ጋር ተያይዞ ሺሻ ህገ-ወጥ ነው? ከሆነስ ግለሰቦቹ ወደ ፍርድ ቤት ለምን አልቀረቡም? ወደ ተሐድሶ ካምፕ ለምንድን ነው? የሚላኩት የሚሉ ክርክሮች መነሳት ጀምረዋል።
አዲስ አበባ (ቢቢሲ አማርኛ)– ሰሞኑን በአዲስ አበባ በተከሰተው ቀውስ የሟቾች ቁጥር 28 መድረሱን ፖሊስ ገልጿል። ቀውሱንም ተከትሎ በአዲስ አበባ የተለያዩ መጠጥ ቤቶችን ጨምሮ የመዝናኛ ቦታዎች ወደ ሦስት ሺ ሁለት መቶ የሚሆኑ ሰዎች በጅምላ እንደታሰሩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት አምነስቲ አስታውቋል።
ፖሊስ በበኩሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፆው መቶ ሰባ አራት ለፍርድ እንደሚቀርቡ እንዲሁም አንድ ሺ ሁለት መቶ አራት ሰዎችን ለማነፅና ለማስተማር በሚል ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ ለተሐድሶ ስልጠና ተልከዋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር የሞከሩትን እንዳሰረ ቢገልፅም አምነስቲ (Amnesty International) በበኩሉ እስሩን አውግዞ በአሁኑ ሰዓት እየታዩ ያሉ ለውጦችን ወደ ኋላ የሚጎትት ነው ብሏል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች አዲስ አበባ ላይ መታሰራቸው በተለይም ከሺሻ ቤቶችና ጫት ቤቶች መወሰዳቸው ጋር ተያይዞ ሺሻ ህገ-ወጥ ነው? ከሆነስ ግለሰቦቹ ወደ ፍርድ ቤት ለምን አልቀረቡም? ወደ ተሐድሶ ካምፕ ለምንድን ነው? የሚላኩት የሚሉ ክርክሮች መነሳት ጀምረዋል።
◌ ደኅንነታቸውና ያልተረጋገጠ የስፈተ ወሲብና ጸጉርን ለማሳድግ የሚረዱ እና የከንሰር መድኃኒቶች በህገወጥ መንገድ ሊገቡ ሲሉ ተያዙ
የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድሃኒት እና የጤና ክብካቤ አስተዳደር ባለስልጣን የትምባሆ ቁጥጥር መመሪያ መጋቢት ወር 2007 ዓ.ም ያወጣ ሲሆን፤ በመመሪያውም መሰረት የትምባሆ ምርቶች በማለት የሚዘረዝራቸው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ከትምባሆ ቅጠል የተዘጋጁ በማጨስ፣ በመሳብ፣ በማኘክ፣ በማሽተት ወይም በሌላ መንገድ የሚወሰድ ማንኛውም ንጥረ ነገር ሆኖ የጋያ ወይም የሺሻ ትምባሆን፣ የኤሌክትሮኒክ ኒኮቲን ይጨምራል።
የመመሪያው ዓላማም በዝርዝር የተቀመጠ ሲሆን ትምባሆን በመጠቀምና ለትምባሆ ጢስ በመጋለጥ በማህበረሰቡ ላይ የሚደርሰውን የጤና፣ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አካባቢያዊ ጉዳቶችን ለመከላከልና ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የፈረመማቻቸውን የትምባሆ ቁጥጥር ኮንቬንሽንም ለማስፈፀም ነው።
መመሪያው ከባለስልጣኑ ፈቃድ ሳያገኝ የትምባሆ ምርትን ለንግድ ተግባር ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባት፣ ማከፋፈል ወይም በጅምላ መሸጥ እንደማይቻል ያስቀመጠ ሲሆን፤ የትምባሆ ምርትን ማስተዋወቅና ስፖንሰር ማድረግ በፍፁም የተከለከለ እንደሆነ በግልፅ አስቀምጧል።
በዚህም መሰረት ማጨስ የተከለከለባቸው ቦታዎች ተብለው የተቀመጡት፤ በህዝብ መጓጓዣዎች፣ በጤናና በትምህርት ተቋማት፣ በምግብ ቤቶች፣ በመዝናኛ ቦታዎች፣ በአውሮፕላን ማረፊያ፣ በፋብሪካዎችና በህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሾች ናቸው።
ምንም እንኳን በነዚህ ቦታዎች ቢከለከልም ከትምህርት ተቋማት፣ ከመንግሥት መስሪያ ቤትና ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት አገልግሎት ከሚሰጡ ተቋማት ውጭ ለማጨስ የተከለለ ወይም የተሰየመ ክፍል ለብቻው የአየር ማናፈሻ (ventilation) የተገጠመለት ከሆነ በሌሎቹ ቦታዎች ማጨስ እንደሚቻል ተቀምጧል።
በዩኒቨርስቲ፣ በኮሌጅና በሌሎች ተቋማት የተከለለ ክፍል ካለ ትምባሆንም ሆነ የትምባሆን ምርት መገልገል እንደሚቻልም መመሪያው ያትታል።
ማንበብዎን ይቀጥሉ፦ በኢትዮጵያ ህግ ሺሻ ማጨስ ህገ- ወጥ ነውን?
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.