Home › Forums › Semonegna Stories › የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሥራ መልቀቂያ ጥያቄ አቀረቡ፤ ዶ/ር አምባቸው መኮንን ተክተዋቸዋል
Tagged: አማራ ክልል, አምባቸው መኮንን, ገዱ አንዳርጋቸው
- This topic has 1 reply, 2 voices, and was last updated 5 years, 10 months ago by Anonymous.
-
AuthorPosts
-
March 8, 2019 at 5:39 am #10126SemonegnaKeymaster
የአቶ ገዱ አንዳርጋቸውን የስልጣን መልቀቅ ጥያቄ ተከትሎ የአዴፓ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የጠቅላይ ሚኒስትር የመሠረተ ልማት እና የከተማ ልማት አማካሪ ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር አምባቸው መኮንን ርዕስ መስተዳደር ሆነው ተሹመዋል።
አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው መልቀቂያ ጥያቄ አቀረቡ። ርዕሰ መስተዳድሩ እየተካሄደ ባለው የክልሉ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ነው ጥያቄውን ያቀረቡ ሲሆን፥ ምክር ቤቱም ጥያቄያቸውን ተቀብሏል። የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ)በበኩሉም የርዕሰ መስተዳድሩን ጥያቄ መቀበሉን የ አማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት እና ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግበዋል።
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ባለፈው ዓመት የካቲት ወር ለሦስተኛ ዙር በርዕሰ መስተዳድርነት ተመርጠው ሲያገለግሉ እንደነበር ይታወሳል። በአጠቃላይም ከታህሳስ ወር 2006 ዓ.ም. ጀምሮ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በመሆን አገልግለዋል።
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው “ታላቁን የአማራ ሕዝብ ለመምራት ዕድል የሰጠኝን ፓርቲዬን አመሠግናለሁ፤ በስልጣን ዘመኔ በሰጠኋቸው ውሳኔዎች ያስከፋኋችሁ ካላችሁ ከልብ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ወኔና ጉልበት ሆኖኝ የኖረውን የአማራ ሕዝብ አመሠግናለሁ፤ ለአዲሱ ርዕሰ መስተዳድርም መልካም የሥራ ዘመን እመኛለሁ” ብለዋል በመሰናበቻ ንግግራቸው።
የአቶ ገዱ አንዳርጋቸውን የስልጣን መልቀቅ ጥያቄ ተከትሎ ምክር ቤቱ የአዴፓ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑትን ዶ/ር አምባቸው መኮንንን ርዕስ መስተዳደር አደርጎ ሾሟል። ዶ/ር አምባቸው ከአዴፓ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነታቸው በተጨማሪ የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮን የመሠረተ ልማት እና የከተማ ልማት አማካሪ ሚኒስትር በመሆን እያገለገሉ ነበር።
እድገታቸው ጋይንት፣ ጎንደር ውስጥ የሆነው ዶ/ር አምባቸው መኮንን የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ሆነው ከመሾማቸው በፊት በተለያዩ የመንግስት ቦታዎች ለ28 ዓመታት ሠርተዋል።
ዶ/ር አምባቸው ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ፣ ቀጥሎም ደቡብ ኮርያ ከሚገኘው ከኮርያ የልማት ኢንስቲትዩት (Korea Development Institute) በፐብሊክ ፖሊሲ የማስተርስ ዲግሪ፣ ከዚያም እንግሊዝ ሀገር ካንተርበሪ ከተማ ከሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኬንት (University of Kent) ሌላ ማስተርስ ዲግሪ እና የዶክትሬት ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።
ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
——
ሌሎች ዜናዎች፦- የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተቀናጀ የግብርና ምርምር ፕሮጀክት ተመረቀ
- የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የእንቦጭ ማስወገጃ ማሽኖች ምርምር ምን ላይ ደረሰ?
- ዓባይ ኢንዱስትሪያል የልማት አክስዮን ማኅበር ደጀን ከተማ ላይ የሲሚንቶ ፋብሪካ ሊገነባ ነው
- የአርሶ አደሩን መሬት እየነጠቁና እያደኸዩ ኢንቨስትመንትን ማሳደግ አይቻልም – አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
- “መንግስት ዜግነታችንን የካደ ግፍ ፈጽሞብናል” ለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ውስጥ ቤታቸው የፈረሰባቸው ዜጎች
March 8, 2019 at 8:31 pm #10140AnonymousInactiveፖለቲካውን ከክረት በማላቀቅ ሀገሪቱን ከውጥረት ለማውጣት የበኩላችንን ለመወጣት ዝግጁ ነን – ዶክተር አምባቸው መኮንን
—–ፖለቲካውን ከክረት በማላቀቅ ሀገሪቱን ከውጥረት በማውጣት አስተማማኝ ሰላም የሰፈነባት፤ ዜጎቿ በሙሉ ነፃነት የሚንቀሳቀሱባት ለማድረግ የበኩላችንን ለመወጣት ዝግጁ ነን አሉ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን።
ዛሬ በክልሉ ምክር ቤት ርእሰ መስተዳደር በመሆን የተሾሙት ዶክተር አምባቸው ቃለ መሃላ ከፈፀሙ በኋላ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ንግግር የአማራ ህዝቦችን የማስተዳደር ሀላፊነት ስለ ተሰጣቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።
አዲሱ ርዕሰ መስተዳደር በንግግራቸው በክልሉ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ቀደም ሲል የተከናወኑ ስራዎች እንዳሉ ሆኖ በቀጣይ ግን የማስተካከያ ስራ የሚፈልጉ እንደ መንገድና መብራትን የመሰሉ የመሰረተ ልማት ስራዎች ክፍተቶች እንዳሉ ጠቁመዋል።
በክልሉ ርብርብ የሚፈልጉ የህዝብ የመልማት ፍላጎት እንዳለም በማንሳት፥ ያሉትን አወንታዊ እና አሉታዊ ሁኔታዎችን በመገምገም ፈጣን ስምሪት እንደሚከናወን ነው የጠቆሙት።
የክልሉ መንግስት በቀጣይ ትኩረት የሚያደርግባቸውን ጉዳዮችም በዝርዝር ያስቀመጡ ሲሆን፥ ጠንካራ መንግስታዊ መዋቅር በየደረጃው መዘርጋቱን በማረጋገጥ ጠንካራ የለውጥ አመራር መገንባት አንዱ መሆኑን አንስተዋል።
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.