Home › Forums › Semonegna Stories › አቶ አዲሱ አረጋን ነጻ ያወጣችው የእስክንድር ፌስታል
- This topic has 1 reply, 1 voice, and was last updated 5 years, 7 months ago by Anonymous.
-
AuthorPosts
-
June 22, 2019 at 12:44 am #11162AnonymousInactive
ቄሮ ነጻ ያወጣው እስክንድር ነጋን ሳይሆን እድሜያቸውን ሙሉ የህወሃት ተላላኪና ማላገጫ ሆነው የኖሩትን አቶ አዲሱ አረጋን እና ሌሎች የኢህአዴግ (የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር) ካድሬዎችን ነው።
አቶ አዲሱ አረጋን ነጻ ያወጣችው የእስክንድር ፌስታል
ያሬድ ኃይለማርያምከወያኔ ጋር የተደረገው የነጻነት ትግል የዛሬ ሦስት ዓመት የተጀመረ የመሰላቸው አንዳንድ የኦዴፖ (የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ) አመራሮች አልፎ አልፎ የሚሰጡት መግለጫ እጅግ አስተዛዛቢ እና አስነዋሪም ነው። ባላፊት ሃያ ሰባት ዓመታት ብዙዎች የህወሃት (ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) የማፈኛ መሣሪያ እና አሽከር ካድሬ ሆነው የገዛ ሕዝባቸውን ሲያሰቃዩ፣ ሲገድሉ፣ ሲገርፉ እና ሲያሰድዱ እንዳልኖሩ፤ በብዙ ሚሊዮኖች ‘ጎመን በጤና’ ብለው የአፈና እንቆቋቸውን እየተጋቱ ሁሉንም ነገር እንዳላየ እና እንዳልሰማ መስለው ለሥርዓቱ ጉልበት እንዳልሆኑ፤ ዛሬ በለውጥ ማግስት ያንን የአፈና ሥርዓት ያለፍርሃት ሲታገሉ፣ ሲታሰሩ እና ሲገረፉ የቆዩ የእስክንድር ነጋ አይነት የነጻነት ታጋዮችን ሲያጣጥሉ፣ ሲያንኳስሱ፣ ሲያስፈራሩ እና ሊያሸማቅቁ ሲሞክሩ ማየት እጅግ ያማል።
እነ ቄሮ፣ ፋኖ፣ ዘርማ እና ሌሎችም የመንደር ነጻ አውጪ ቡድኖች ሳይፈጠሩ ወይም መኖራቸው ሳይታወቅ በፊት ከወያኔ ጋር የነበረውን የሃያ ሰባት ዓመት ትንቅንቅ እና እልህ አስጨራሽ ትግል ብቻቸውን የተጋፈጡት እስክንድርን ጨምሮ በጣት የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ የመብት አቀንቃኞች እና ተሟጋቾች፣ ጥቂት ምሁራን እና ጥቂት የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓሪቲ ድርጅቶች አመራር እና አባላት ናቸው። የዛሬዎቹ ሹማምንት የህወሃት ጥርስ እና ክርን ሆነው የገዛ ሕዝባቸውን ይገዘግዙ እንደነበር እንዲህ በአጭር ጊዜ መዘንጋታቸው የሚያስገርም ነው። ከህወሃት ጫና ተላቀው ዛሬ እንደልብዎ እንዲናገሩ ያደረገችዎት ነጻነት ከእነ እስክንድር ነጋ እና ሌሎች ለዜጎች መብት መስዋዕትነት የከፈሉ ኢትዮጵያዊያን በመከራ ጊዜ ከሸከፏት ፌስታል መመንጨቷን ያወቁ አልመሰለኝም።
ቄሮ ነጻ ያወጣው እስክንድር ነጋን ሳይሆን እድሜያቸውን ሙሉ የህወሃት ተላላኪና ማላገጫ ሆነው የኖሩትን አቶ አዲሱ አረጋን እና ሌሎች የኢህአዴግ (የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር) ካድሬዎችን ነው። እስክንድር ነጋ እና ሌሎቹ በግፍ ታስረው የነበሩ የመብት ታሟጋቾች እና የነጻነት አቀንቃኞች ነጻ የወጡት ራሳቸው በከፈሉት መስዋዕትነት ነው። ያጣጣሏት የእስክንድር ነጋ ፌስታል ለእርሶም ነጻ መውጣት ትልቅ ድርሻ አላት።
የመብት ተሟጋቾችን፣ በክፉ ቀን ለሕዝብ ነጻነት ዋጋ የከፈሉ ጋዜጠኞችን፣ ሲታሰሩና ሲሰቃዩ የኖሩ የፖለቲካ መሪዎችን፣ ምሁራንን እና የአገር ባለውለተኛ የሆኑ ግለሰቦችን ባልተገራ የካድሬ አንደበት መዝለፍም ሆነ ክብራቸውን መንካት እና መብታቸውን ማፈን ለውጥ እንመራለን ከሚሉ አካላት አይጠበቅም።
June 22, 2019 at 1:09 am #11166AnonymousInactiveአልተማረም እንዳትለው ዋሽንግተን በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ገብቶ ዲግሪ ጭኖ የወጣ እሳት የላሰ ምሁር ነው።
ፈሪ ነው እንዳትለው ሁሉም በፍርሀት በተሸበበት በዚያ ዘመን “ምኒልክ” የሚባል ስሙ እንደ ነበልባል የሚፋጅ ጋዜጣ አቋቁሞ የመለስ ዜናዊን አስተዳደር ሲያርበደብድ የኖረ ሰው ነው።
ታስሮ ዝነኛ መሆን ፈልጓል እንዳትለው የአሁን ባለስልጣኖች እየዞሩ ለእነ አቦይ ስብሀት በሚያሸረግዱበት ዘመን እሱ ከአንድም ዘጠኝ ግዜ ጨለማ ቤት ውስጥ ታስሮ በፅናት የኖረ ፅኑ ሰው ነው።
ታዋቂ መሆን ይፈልጋል እንዳትለው እስር ቤት ቁጭ ብሎ ከአራት በላይ አለም አቀፍ ሽልማትችን የተቀበለ ተአምረኛ ሰው ነው።
የደሀ ልጅ ነው እንዳትለው መሀል አዲስ አበባ ላይ ስንት ንብረት ያለው ልጥጥ ያለ የልጥጥ ሀብታም ልጅ ነው።
ተስፋ ቆርጧል እንዳትለው አሁንም ደረቱን ነፍቶ ትግሌን እቀጥላለው ይልሀል። እንግዲህ ይህን እስክንድር የተባለን ክስተት ከአንድ ተራ ካድሬ ጋር ሲያወዳድሩት ከማየት በላይ ምን የሚያሸማቅቅ ነገር አለ?! አቤቱ ይቅር በለን!!!
[Dagmawi Dagmawi]
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.