አዳማ ከተማ ውስጥ ግዙፍ የኮንፈረንስና ኮንቬንሽን ማዕከል ሊገነባ ነው

Home Forums Semonegna Stories አዳማ ከተማ ውስጥ ግዙፍ የኮንፈረንስና ኮንቬንሽን ማዕከል ሊገነባ ነው

Tagged: 

Viewing 1 post (of 1 total)
  • Author
    Posts
  • #8798
    Semonegna
    Keymaster

    አዳማ ከተማ ውስጥ የሚገነባው የኮንፈረንስና ኮንቬንሽን ማዕከል ግንባታው ከ3 እስክ 5 ዓመት ጊዜ የሚፈጅ ሲሆን፥ የዘንድሮውን ዓመት ለዝግጅት በመያዝ በቀጣይ ወደ ግንባታ ለመግባት በትኩረት እንደሚሠራ የከተማዋ ከንቲባ አቶ መስፍን አሰፋ ገልጸዋል።

    አዳማ (ኢ.ፕ.ድ./ኤፍ.ቢ.ሲ.) – አዳማ ከተማን የኮንፈረንስና እና ኮንቬንሽን ማዕከል ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን የአዳማ ከተማ አስተዳደር ሠራ ገለጸ። የከተማ አስተዳደሩ የአዳማ ከተማ ሀገሪቱ ውስጥ ካላት መዕከላዊ አቀማመጥ እና ለዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ያላትን ቅርበት መሠረት በማድረግ ከተማዋን የኮንፈረንስ እና ኮንቬንሽን ማዕከል ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ነው የተገለፀው።

    የማዕከሉ ዲዛይን ተሠርቶ የተጠናቀቀ ሲሆን፥ ዲዛይኑም የአካባቢውን ማኅበረሰብ ባህል እና እሴት በጠበቀ መልኩ የተሠራ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ አቶ መስፍን አሰፋ ተናግረዋል።

    ከዚህ ባለፈም ማዕከሉ መንግስትን እና የአካባቢውን ባለሀብቶች በማሳተፍ የሚሠራ መሆኑ ነው የተገለፀው።

    ዲዛይኑ ተሠርቶ እንደተጠናቀቀም ከባለሀብቱ ጋር ወይይት ተደርጓል ያሉት ከንቲባው፥ የማዕከሉ ግንባታ ለከተማዋም ሆነ ለሀገሪቱ ፈርጀ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው አቶ መስፍን አንስተዋል።

    ግንባታው ከ3 እስክ 5 ዓመት ጊዜ የሚፈጅ ሲሆን፥ የዘንድሮውን ዓመት ለዝግጅት በመያዝ በቀጣይ ወደ ግንባታ ለመግባት በትኩረት እንሠራለን ነው ያሉት ከንቲባው። ግንባታውን አጠናቆ ለመጨረስም 2 ቢሊየን ብር ስፈልጋል ያሉት ከንቲባው፥ ለግንባታው የሚያስፈልገው የ10 ሄክታር መሬት የማዘጋጀት ሂደቱም ተጀምሯል ብለዋል።

    Addis-Africa International Convention and Exhibition Center (AAICEC) Share Company

    በሌላ በኩል በከተማዋ ከኢንቨስትመንት ጥያቄ ጋር ተያይዞ የሚነሳውን ቅሬታ መቅረፍም፥ በዚህ ዓመት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራበት ያለ ጉዳይ መሆኑን ነው ከንቲባው የተናገሩት።

    ፋና (ኤፍ.ቢ.ሲ.) እንደዘገበው ብዙ ጊዜ የከተማዋ አቅም እና የኢንቨስትመንት አማራጭ ላይ በቂ ዝግጅት ስለማይደረግ ባለሀብቱ የኢንቨስትመንት ፍቃድ ጠይቆ ምላሽ ሳያገኝ ለበርካታ ዓመታት ወደሥራ ሳይገባ መቆየቱ እና ይህም የተለያየ ቅሬታ መፍጠሩንም ከንቲባው አንስተዋል ።

    የተጠራቀሙ ጥያቄዎችን ለመመለስ እና የዘርፉን ውስንነቶች ለመቅረፍም የከተማዋን አቅም እና የኢንቨስትመንት አማራጮች የመለየት ሥራ እየሠራ ነው ብለዋል።

    አሁን ላይ ለመሥራት ከታሰበው የኮንፈረንስና የኮንቬንሽን ማዕከል አጋዥ የሆኑ ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴሎች ለመስራት ፍቃድ የሚጠይቁ ባለሀብቶች በቅድሚያ የሚስተናገዱ መሆኑን ከንቲባው ጠቁመዋል።

    በመስከረም ወር 2007 ዓ.ም. በይፋ የተመረቀው የአዲስ-አዳማ የፈጣን መንገድ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጊዜ ጀመሮ ከከተማዋ ወደ አዲስ አበባ የሚደረገውን ጉዞ በእጅጉን እንዳቃለለውና በሁለቱ ከተሞች የነበረውን የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ሁነኛ በሚባል መልኩ እንዳሻሻለው ይታወቃል። ይህ 85 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለውና ወደጎን ስድስት መኪናዎችን ማስተናገድ የሚችለው መንገድ ከተገነባ በእላ አዳማ ከተማ ውስጥ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ መጨመሩን ብዙዎች ይመሰክራሉ።

    ምንጮች፦ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ ፋና ብሮድካስቲንግ፣ ሰሞነኛ

    አዳማ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ

Viewing 1 post (of 1 total)
  • You must be logged in to reply to this topic.