Home › Forums › Semonegna Stories › የቴሌኮም ማጭበርበር የፈጸመችው ኢትዮጵያዊ ለ12 ዓመታት እስራት እና 63 ሚሊዮን ብር መቀጮ ተጣለባት
Tagged: ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ, ዓለም ታምራት, ጠቅላይ አቃቤ ሕግ
- This topic has 0 replies, 1 voice, and was last updated 6 years ago by
Semonegna.
-
AuthorPosts
-
May 9, 2019 at 5:30 am #10791
Semonegna
Keymasterተከሳሽ ዓለም ታምራት ከተለያዩ ዓለም ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ ጥሪዎችን በማስተላለፍ ኢትዮ ቴሌኮም የዘረጋውን መሠረተ ልማት ወደ ጎን በመተው ዓለም አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት በመስጠት ጥፋተኛ ተብላለች።
አዲስ አበባ (ሰሞነኛ)– ዓለም ታምራት የተባለችው ተከሳሽ የቴሌኮም መሣሪያዎችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት፣ ለመጠቀም እና የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሕጋዊ ፍቃድ ሳይኖራት ወደ ሕገወጥ ተግባሩ መግባቷ ተጠቁሟል። ወንጀሉ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ልዩ ስሙ ገርጅ አካባቢ መፈጸሙ ታውቋል።
የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 761/2004 አንቀጽ1/ለ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሳሽ ከቀድሞው ኢፌዲሪ መገናኛ እና ኢንስፎርሜሽን ሚኒስቴር በተሰጠ ፍቃድ ብቻ ወደ ሀገር ውስጥ ለመጠቀም የሚቻሉትን የኮል ተርሚኔሽን (call termination)፣ ኮል ባክ (call back)፣ ጥሪ የመቀበል እና ጥሪ የመላክ አገልግሎት መስጠት እንደነበር ተነግሯል።
ሆኖም ግለሰቧ ከሕግ አግባብ ውጪ ኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርዶችን በውስጣቸው በማስገባት በአንድ ጊዜ ብዛት ያላቸውን እቃዎች በቅናሽ በመግዛት እና ጥሪዎችን ማስተላለፍ የሚችሉ ብዛታቸው 4 የሆኑ ጌትዌይ (gateway) የቴሌኮም መሣሪያዎችን በድብቅ በማስገባት ወንጀል ፈጽመዋል።
በድብቅ የገቡ መሣሪያዎችን ከበይነመረብ (internet) የግንኙነት አውታር ጋር በማገናኘት የሚያገኙትን ኔትወርክ (network) በማብዛት ወደ ዋየርለስ ኔትወርክ (wireless network) እንዲቀየር በማድረግ የራሳቸውን ኔትወርክ መፍጠር የሚችሉ 15 ቶፒ ሊንክ የተባሉ መሣሪያዎችን ከሌሎች አጋዥ መሣሪያዎች ጋር መጠቀማቸው በክሱ ቀርቧል።
ግለሰቧ ከውጭ ሀገር ወደ ሀገር ውስጥ የሚደረጉ የስልክ ጥሪዎችን ኢትዮ ቴሌኮም በዘረጋው ኔትወርክ በኩል እንዲያልፉ በማድረግ ኢትዮ ቴሌኮምን 6,379,342.19 ብር ማሳጣቷ ተጠቅሷል።
ተከሳሽ ዓለም ታምራት ከተለያዩ ዓለም ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ ጥሪዎችን በማስተላለፍ ኢትዮ ቴሌኮም የዘረጋውን መሠረተ ልማት ወደ ጎን በመተው ዓለም አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት በመስጠት ጥፋተኛ ተብላለች።
ጉዳዩን ተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 14 ወንጀል ችሎትም አቃቤ ሕግ ያቀረበውን የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን በመመልከት በሚያዝያ 14 ቀን 2011 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በ12 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ63 ሚሊዮን የገንዘብ መቀጮ አሳልፎባታል።
ምንጭ፡- የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ / የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
ሌሎች ዜናዎች፦- በከባድ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 59 ባለስልጣናትና ባለሃብቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ
- ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከኔዘርላንድ ኤንባሲ ጋር በመተባበር ለሕግ ባለሙያዎች የትምህርት ዕድል ሰጠ
- አጣየ፣ ካራቆሬ፣ ማጀቴ እና አካባው በሚኖሩ ዜጎች ላይ የታጠቁ ኃይሎች እያደረሱት ያለው ኢ-ሰብአዊ በደል
- ሕገ-ወጥ የገንዘብ እና የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመከላከል ተጨማሪ 36 አዳዲስ ኬላዎች ተቋቁመዋል – የገቢዎች ሚኒስቴር
- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መፃሕፍት ኤጀንሲ አሠራሩን ለማዘመን ከእንግሊዝ ሀገር አቻው ጋር ውይይት ተደረገ
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.