የደንበኞቹን ፍላጎት ያልቻለው የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ ገበያ (ኢትፍሩት)

Home Forums Semonegna Stories የደንበኞቹን ፍላጎት ያልቻለው የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ ገበያ (ኢትፍሩት)

Viewing 1 post (of 1 total)
  • Author
    Posts
  • #8736
    Semonegna
    Keymaster

    ኢትፍሩት የአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ሌሎች ሸቀጦችን ጨምሮ በመዲናችን አዲስ አበባ ከ60 በላይ ኮንቴነሮችን ይዞ የደንበኞችን ፍላጎት የማርካትና ገበያዉን የማረጋጋት ዓለማ ሰንቆ እየ ሠራ ቢሆንም የተፈለገውን ውጤት አያመጣሁ አይደለም ብሏል።

    አዲስ አበባ (ኢቢሲ)– የቀድሞው የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ ገበያ (ኢትፍሩት) ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ እየሰጠ ያለው አገልግሎት የደንበኞቹን ፍላጎት እያረካ አለመሆኑን ተጠቃሚዎች ገለጹ።

    የከተማዋ ሸማቾች ምርትና ሸቀጦችን በግል ከሚያቀርቡ የንግድ ተቋማት ይልቅ ኢትፍሩት በዋጋ የተሻለ መሆኑን የሚገልፁት አስተያየት ሰጪዎቹ ፥ ዘይትና ስኳርን ፍለጋ ከጠዋት ተነስቶ እስከ እኩለ ቀን ድረስ በኢትፍሩትና ሸማቾች ሱቆች በራፍ መሰለፍ የተለመደ ተግባር መሆኑን ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ገልፀዋል።

    ኢትፍሩት የአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ሌሎች ሸቀጦችን ጨምሮ በመዲናችን አዲስ አበባ ከ60 በላይ ኮንቴነሮችን ይዞ የደንበኞችን ፍላጎት የማርካትና ገበያዉን የማረጋጋት ዓለማ ሰንቆ እየ ሠራ ቢሆንም የተፈለገውን ውጤት አያመጣሁ አይደለም ብሏል።

    ድርጅቱ የፍራፍሬና አትክልት ምሮቶችን ጨምሮ ከሌሎች አምራቾች እየገዛ ስለሚሸጥ በሚፈለገዉ ልክ የአቅርቦት መጠኑን ማሻሻል አለመቻሉን ለኢቢሲ አመልክቷል።

    Business Cooperation: Meki Batu Vegetable & Fruit Growers and Ethiopian Airlines

    ኢትፍሩት ለከተማዋ ነዋሪ በተመጣጣኝ ዋጋ ሸቀጥና ምርትን በማቅረብ የተጠቃሚዎችን ፍላጎት ለሟሟላት ከአዲስ አበባ ዉጭ በአንዳንድ ክልሎች ቅርንጫፎችን ከፍቶ ህብረተሰቡን በማገልገል ላይ መሆኑን በኮሮፕሬሽኑ የንግድ ሥራ ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መህዲ አስፋው ተናግረዋል።

    ከመሠረታዊ የፍጆታ እቃዎች አቅርቦትና ቁጥጥር ጋር በተያያዘ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ዘመናዊ አሠራር በመዘርጋት ሂደት ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አመልክቷል።

    በቢሮው የግብይት ተሳታፊዎች ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን በቀለ እንደሚሉት እያንዳንዱን ተጠቃሚ ጋር ለመድረስ እንዲያስችል ከኢትፍሩት ሱቆች ባሻገር በግለሰብ ሱቆች መገልገል የሚያስችሉ ከ1 ሚሊየን በላይ ካርዶች ተዘጋጅተዉ ለህብረተሰቡ በመሰረጨት ላይ ናቸዉ።

    ኃላፊው እንደሚሉት ካርዶቹን በመያዝ ህብረተሰቡ ትስስር ከተፈጠረባቸዉ ሱቆች የፍጆታ ሸቀጦችን በመሸመት ካለአስፈላጊ መጉላላትና ሰልፍ ራስን ማዳን ይቻላል።

    ከ8 በላይ የአትክልትና ፍራፍሬና የፋብርካ ምርቶችን ለህብረተሰቡ በማቅረብ ላይ የሚገኘዉ ኢትፍሩት ከ5 መቶ በላይ ሠራተኞችን ይዞ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች በ60 ኮንቴኔር ሱቆች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

    በቅርቡም በንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስር ተደራጅቶ ለህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እይተንቀሳቀሰ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

    ኢትፍሩት የተመሠረተው በቀድሞ የኢትዮጵያ መንግስት (ደርግ)የመንግስት እርሻ ልማድ ድርጅት ስር እ.ኤ..አ በ1980 ዓ.ም. ሲሆን የተመሠረተበትም ዓላማ በመንግስት እርሻ ልማቶች የተመረቱ አትክልትና ፍራፍሬዎችን ለገበያ ለማቅረብ ነበር። ከመንግስት ስርዓት ለውጥ (እ.ኤ..አ 1991 ዓም) በኋላ የሽግግሩ መንግስት በመንግስት የተያዙ ንብረቶችን ለግልና ለሕዝብ ለማስተላለፍ በወጣው አዋጅ መሠረት እ.ኤ.አ በ1993 ዓ.ም.  በአዋጅ ቁጥር 131/1993 ኢትፍሩት የሕዝብ ድርጅት (public enterprise) ሆኖ ዕውቅናን አግኝቷል።

    ምንጭ፦ ኢቢሲ እና ኢትፍሩት 

Viewing 1 post (of 1 total)
  • You must be logged in to reply to this topic.