ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የ2011ዓ.ም. አዲስ ገቢ ተማሪዎችን በታህሳስ ወር መጨረሻ ላይ ለመቀበል ቅድመ ዝግጅት መጨረሱን ገለጸ። ዩኒቨርሲቲ አዲስ እንደመሆኑ መጠን ራሱን ለማስፋፋት ያስችለው ዘንድ መምህራንን እና ሠራተኞችን በስፋት እየቀጠረ ነው።
አሰበ ተፈሪ (ሰሞነኛ) – ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የ2011ዓ.ም. አዲስ ገቢ ተማሪዎችን በታህሳስ ወር መጨረሻ ላይ ለመቀበል ቅድመ ዝግጅት መጨረሱን ገለጸ።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙክታር ሙሀመድ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው በ2010ዓ.ም. ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ተቀብሎ ማስተማር የጀመረ ሲሆን፥ በማስፋፊያ ግንባታ መዘግየት ምክንያት በ2011ዓ.ም. የተመደቡትን ተማሪዎች እስካሁን ድረስ ጥሪ ያላደረገ አብራርተው በዚህ ወር መጨረሻ ግን ለተማሪዎቹ ጥሪ እንደሚያደርግ ገለጸዋል።
የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ግርማ መኮንን በበኩላቸው የተማሪዎች የመኖሪያ ቤቶች (ዶርምተሪ) ግንባታ እየተጠናቀቀ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ 15 ቀናት ውስጥ በማስታወቂያ ለተማሪዎቹ ጥሪ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
◌ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የጤና እና የህክምና ሳይንስ ኮሌጅ የህክምና ዶክተሮችን ጨምሮ 220 የጤና ባለሞያዎችን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን በተገኙበት ዛሬ አስመርቋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ አዲስ እንደመሆኑ መጠን ራሱን ለማስፋፋት፣ የትምህርት ክፍሎችን (ዲፓርትመንቶች) እና የተማሪዎችን ቁጥር ለመጨመር ያስችለው ዘንድ መምህራንን እና ሠራተኞችን በስፋት እየቀጠረ ነው።
ዩኒቨርሲቲው ባለፈው ዓመት በአካባቢው ያለውን የብዝሀ ሕይወት ለመንከባከብና ለመጠበቅ በሚል ዓላማ ከኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ጋር ተባብሮ ለመሥራት የሚያስችለውን ስምምነት መፈራረሙን መዘገባችን ይታወሳል።
ምንጭ፦ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር | ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
——
ሌሎች ዜናዎች፦