Home › Forums › Semonegna Stories › አለርት ሆስፒታል ውስጥ ዘመናዊ የሕፃናት ሆስፒታል እና የአደጋ ሕክምና ማዕከል ይገነባሉ
Tagged: ሊያ ታደሰ, አለርት ሆስፒታል, አሚር አማን, የሕፃናት ሆስፒታል
- This topic has 0 replies, 1 voice, and was last updated 6 years ago by
Semonegna.
-
AuthorPosts
-
April 11, 2019 at 4:57 am #10567
Semonegna
Keymasterየኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ (ኢፌዴሪ) መንግስት ከኔዘርላንድ መንግስት በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ የሕፃናት ሆስፒታል ለመገንባት የሚውል የ27.44 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ስምምነት ተፈራርሟል። በተጨማሪም የአደጋ (trauma) ሕክምና መስጫ ማዕከል ይገነባል።
አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) የኢትዮጵያ መንግስት ከኔዘርላንድ መንግስት ጋር በመተባበር ከ1.8 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ በአለርቲ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ በአይነቱ ልዩ እና የመጀመሪያ የሆነ አዲስ የሕፃናት አጠቃላይ ሆስፒታል ለመገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።
የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት፥ በሕፃናት ዙሪያ የሚሰጡ የሕክምና አገልግሎቶችን ማሻሻልና ማዘመን አስፈላጊ ከመሆኑ አንጻር ሆስፒታሉ በሕፃናት ዙሪያ ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ የልብ፣ የነርቭ፣ የኩላሊት እንዲሁም ከ30 በላይ የሚደርሱ የሕክምና ስፔሻሊቲ አገልግሎት እንደሚኖሩት ተናግረዋል።
በአለርት ሆስፒታል ውስጥ የሚገነባው የሕፃናት አጠቃላይ ሆስፒታል በሁለት አመት እንደሚጠናቀቅና 317 አልጋዎች እንደሚኖሩት ወጪውም በኔዘርላንድ መንግስት፣ በአሜርካን ፋውንደሽን እና በኢትዮጵያ መንግስት እንደሚሸፍን በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ ተገልጧል።
ከዚሁ ዜና ጋር በተያያዘ፥ የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የአደጋ (trauma) ሕክምና መስጫ ሆስፒታልን ለመገንባት ከእቴቴ ኮንስትራክሽን ድርጅት ጋር ሚያዝያ 2 ቀን 2011 ዓ.ም. ውል ተፈራርሟል።
ጤና ሚኒስቴር ከእቴቴ የኮንስትራክሽን ድርጅት ጋር ውል በተፈራረሙበት ወቅት የጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን እንደተናገሩት፥ በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰቱና ለህመም፣ ለአካል ጉዳት እና ለሞት የሚያጋልጡ አደጋዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ በመምጣታቸው በዚህ ዙሪያ የሚሰጡ የሕክምና አገልግሎቶችን ማሻሻልና ማዘመን አስፈላጊ በመሆኑ በድንገተኛ አደጋዎችና ተጓዳኝ ሕክምናዎችን የሚሰጥ ማዕከል በአዲስ አበባ ከተማ አለርት ሆስፒታል ውስጥ ይገነባል ብለዋል።
ከ751 ሚሊዮን ብር በላይ የተመደበለት እና ባለ 8 ፎቅ የሚገነባለት ይህ ማዕከል በ3 ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የታሰበ ሲሆን፤ ከ550 በላይ አልጋዎች የሚኖረውና በቀን ከ2000 እስከ 5000 ተገልጋዮችን ማስተናገድ የሚችል እንደሚሆን ሚኒስትሩ ጨምረው ተናግረዋል።
የግንባታው በጀት ሙሉ በሙሉ ከመንግስት በመሆኑና ተቋራጩም በተለያዩ የግንባታ ሥራዎች ሰፊ ልምድ ያለው በመሆኑ በግንባታ ሂደቱ ወቅት ያጋጥማል ተብሎ የሚያሳስብ ችግር የለም ተብሏል።
ምንጭ፦ ጤና ሚኒስቴር / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
——
ተመሳሳይ ዜናዎች፦- በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ከ56 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው ሆስፒታል ተመረቀ
- የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የካንሰርና የልብ ህክምና ማዕከል ግንባታ 56 በመቶ ደርሷል
- የአርሲ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ4ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 388 የህክምናና የጤና ተማሪዎች አስመረቀ
- ሀገር በቀል የመድኃኒት አምራቾች መሠረታዊ ችግሮች በጥናት ሊለዩ ይገባል ― የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ
- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገነባው የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል ግንባታ በተያዘለት የጊዜ ገደብ አይጠናቀቅም
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.