Home › Forums › Semonegna Stories › የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ቸርነት ሳይሆን ህልውና ነው ― ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ
Tagged: ሰርካለም ይገረሙ, ኃይማኖት ቢችል, አልማዝ አፈራ, አፈወርቅ ካሱ, የሴቶች ቀን, ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ
- This topic has 1 reply, 2 voices, and was last updated 5 years, 9 months ago by Anonymous.
-
AuthorPosts
-
March 13, 2019 at 3:41 am #10202SemonegnaKeymaster
“የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ማምጣት ቸርነት አይደለም። ነገር ግን ለአንድ ሀገር ህልውና በመሆኑ አንዱ ሰጭ ሌላው ተቀባይ በሆነ መልኩ ሳይሆን ሰብዓዊ ወይም ሰዋዊ መብትም ጭምር ነው።” ዶ/ር አልማዝ አፈራ
ደብረ ብርሃን (ሰሞነኛ) – የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን “የላቀ ትኩረትና ቁርጠኝነት ለሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ቃል የዩኒቨርሲተው ከፍተኛ አመራሮች ተማሪዎች፣ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች፣ የዞን ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች መምሪያ ኃላፊዎችና የሊግ ተወካዮች በተገኙበት መጋቢት 2 ቀን 2011 ዓ.ም. በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።
በበዓሉ ላይ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር ወ/ሮ ኃይማኖት ቢችል እንደገለጹት የሴቶችን ቀን ስናከብር በሴቶች ላይ ይደርስ የነበረውን ጭቆና ለማስወገድ የተደረገውን የትግል እንቅስቃሴና ውጤታማነት ለመዘከር፣ ሴቶች ከነበረባቸው ጭቆና ተላቀው በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ፣ በስነ-ልቦናዊ እና ፖለቲካዊ እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር የሚቻልበትን ሁነት ለመዘከር መሆኑን አንስተዋል። እንደ ዳይሬክተሯ ገለፃ፥ በዓሉ ሴቶች ውጤታማ የሆኑባቸውን ሥራዎች በመዘከር ለማበረታታት ያስችላል ብለዋል።
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ማኅበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር አልማዝ አፈራ በዓሉን በንግግር ሲከፍቱ፥ የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ማምጣት ቸርነት አይደለም። ነገር ግን ለአንድ ሀገር ህልውና በመሆኑ አንዱ ሰጭ ሌላው ተቀባይ በሆነ መልኩ ሳይሆን ሰብዓዊ ወይም ሰዋዊ መብትም ጭምር ነው ብለዋል። ፕሬዚዳንቷ አክለው እንደገለጹት፥ ሴት የቤተሰብና የሀገር መሠረት ስለሆነች እኛ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰቦች ከዘር፣ ከጾታና ከሀይማኖት አድሎ በጸዳ መልኩ መሥራትና መታገል እንዲሁም በግልፅ ብቻ ሳይሆን በረቀቀ ዘዴ ጭምር የሚደረጉ ጾታዊ ትነኮሳዎችን ለመዋጋት መሥራት አለብን ብለዋል።
◌ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተቀናጀ የግብርና ምርምር ፕሮጀክት ተመረቀ
በበዓሉ ላይ ሁለት ጥናታዊ ጽሁፎች የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት እና እናትነት /Motherism/ በሚሉ ርዕሶች በዶ/ር ሰርካለም ይገረሙ እና በመ/ር ጌትነት ጥበቡ ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል። በውይይቱም የቀረቡት ጽሁፎች አስተማሪ በመሆናቸው ለተግባራዊነታቸው ሁሉም አካል ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንዳለበት ተጠቁሟል።
በመጨረሻም አርዓያ ለሆኑ ሴት መምህራንና በ2011 ዓ.ም የመጀመሪያው ወሰነ ትምህርት ከ1ኛ-3ኛ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ሴት ተማሪዎች የእወቅናና የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል። አቶ ደረጀ አጅቤ የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ተወካይ የማበረታቻ ሽልማቱን ከሰጡ በኋላ ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ሴቶች ቤተሰባቸውን ይመራሉ፣ ያስተዳድራሉ፤ ለዚህም መስዋዕትነት ይከፍላሉ። አመራር ለመሆን ሴቶች ራሳቸው መስዋዕትነት መክፈል ይኖርባቸዋል። ሴቶችን አመራር ስናደርጋቸው ምቹ የሥራ ቦታና ሁኔታ ልንፈጥርላቸው ይገባል ብለዋል።
ምንጭ፦ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
March 16, 2019 at 2:22 am #10248AnonymousInactiveየስኬታማ ሴቶችን ተሞክሮ ማስፋፋት ይጠበቃል – ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ
—–ክቡር የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ የስኬታማ ሴቶችን ተሞክሮ ማስፋፋት እንደሚጠበቅ ገለጹ፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር “የላቀ ትኩረትና ቁርጠኝነት ለሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ቃል የማርች 8 በዓልን አክብሯል፡፡ በዓሉን ምክንያት በማድረግም የብዙ ሳይንሳዊ ፈጠራ ስራዎች ባለቤት የሆኑት ዶክተር ፋንታዬ ይማሙ ተሞክሯዎቻቸውን ለሌሎች ተመራማሪ ሴቶች እንድያካፍሉ ማድረጉ ይታወቃል፡፡
ፕሮፌሰር አፈወርቅ ለፕሮግራሙ ታዳሚ ሴት መምህራን፣ ተማሪዎችና ተመራማሪዎች፣ ለመስሪያ ቤቱ ሴት ሰራተኞች የዶክተር ፋንታዬን ፈለግ በመከተል ልምዳቸውን ማስፋፋት ይጠበቅባችኹል፣ ዓላማችን ብዙ ዶ/ር ፋንታዬዎችን ማየት ነው ብለዋል፡፡
ዶክተር ፋንታዬ በሳይንሱ ዘርፍ ለአገራችን የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችን በማበርከታቸው ለተደረገላቸው ግብዣና የምስጋና የምስክር ወረቀት መስሪያ ቤቱን በማመስገን እንደ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ዓይነት አስታዋሽ ያስፈልገናልም ብለዋል፡፡
ምንጭ፦ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.