Home › Forums › Semonegna Stories › የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኪነ-ሕንፃ (አርክቴክቸር) ትምህርት ክፍል ተማሪዎችን አስመረቀ
- This topic has 1 reply, 2 voices, and was last updated 5 years, 7 months ago by Anonymous.
-
AuthorPosts
-
March 19, 2019 at 6:52 am #10315SemonegnaKeymaster
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኪነ-ሕንፃ (አርክቴክቸር) ትምህርት ክፍል ዘንድሮ ተማሪዎች ሲያስመርቅ ሦስተኛው ሲሆን፥ 22 ወንዶች እና 7 ሴቶች በድምሩ 29 ተማሪዎች ለምረቃ በቅተዋል።
ባህር ዳር (ሰሞነኛ)– ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የመሬት አስተዳደር ኢንስቲትዩት ስር የሚገኘው የኪነ-ሕንፃ (አርክቴክቸር) ትምህርት ክፍል ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ለሶስተኛ ጊዜ አስመረቀ።
የዩኒቨርሲቲው መሬት አስተዳደር ዳይሬክተር ዶ/ር በላቸው ይርሳው ዓለሙ ለተመራቂ ተማሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት ተመራቂዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ያገኙትን የቀለም እና የተግባር ትምህርት ወደ ተግባር የሚተረጉሙበት እና ከራሳችው አልፎ ህብረተሰባቸውን የሚያገለግሉበት ጥሩ አጋጣሚ በመሆኑ በከፍተኛ ኃላፊነት ስሜት እንዲሠሩ ይጠበቃል ብለዋል። የኪነ-ሕንፃ ትምህርት ትዕግስት እና ፈጠራ የሚጠይቅ በመሆኑ ተመራቂ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ያሳደጉትን የፈጠራ ክህሎት የበለጠ አጎልብተው እራሳቸውን ጠቅመው ማኅበረሰቡን እንዲያገለግሉበት አሳስበዋል።
ዶ/ር በላቸው አክለውም የኪነ-ሕንፃን ሙያ የሚጠይቅ ሥራ የሚሠሩ የፌዴራል፣ የክልል የግልም ሆነ የመንግስት መሥሪያ ቤቶች ከፍተኛ ሃብት እና ዕውቀት ፈሶባቸው የሰለጠኑ ተመራቂዎችን በአግባቡ ሊጠቀሙባቸው ይገባል ብለዋል።
◌ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ዶክተሮችን አስመረቀ
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ እንደተናገሩት፥ የሚገነቡት ከተሞች ብሎም አገራት የሚመስሉት የኪነ-ሕንፃ ባለሙያዎችን በመሆኑ ለከተሞች ውበት፣ የኑሮ ምቹነት፣ ቀጣይነት፣ ወጭ ቆጣቢነት የራሳቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል። ፕሬዝዳንቱ ቀጥለውም አሁን ትልቅ የኪነ-ሕንፃ ጥበብ የሚታይባቸው የአገራችን ቅርሶች የመፈራረስ አደጋ የተጋረጠባቸው ጊዜ ሲሆን መታደግ የሚቻለውም በዕውቀት እና በጥበብ በመሆኑ ተመራቂዎች ያላቸውን ዕውቀት እና ጥበብ በተቋርቋሪነት መንፈስ በመጠቀም ከመፍረስ እንዲታደጓቸው አሳስበዋል።
ዶ/ር ፍሬው ለተመራቂዎች ባስተላለፉት መልዕክት፥ ተመራቂ ተማሪዎች የኢትዮጵያን ቅርሶች፣ መልክዓ-ምድሮች፣ እንስሳት፣ እጽዋት እና ሌሎች የተፈጥሮ ሃብቶች ሌሎች የሌሏቸው መለዮወቻችንን የንድፋቸው ማስጌጫ መጠበቢያ ቅመም በማድረግ እንዲጠቀሙባቸው አሳስበው ዓለም ከደረሰበት እድገት አንጻርም ዘመኑን የዋጀ ንድፍ መሥራት እንደሚገባቸው ተናግረው፤ ከሁሉም በፊት ግን ህሊናቸውን እና ፈጣሪያቸውን ዳኛ አድርገው የሙያ ሥነ-ምግባር በተላበሰ መልኩ እንዲሠሩ በአጽንኦት መክረዋል። በመጨረሻም ተመራቂዎች በሙያቸው ስኬታማ በመሆን የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲን ብሎም የውድ አገራቸውን ስም የበለጠ በበጎ እንዲታወቁ የበኪላቸውን ያደርጉ ዘንድ አደራ ብለዋል ።
በምረቃ በርሃግብሩ የተገኙት አርክቴክት አበበ ይመኑ የረዥም ጊዜ የህይወት ተሞክሯቸውን እና የሥራ ልምዳቸውን ለተመራቂዎች ያቀረቡ ሲሆን፥ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በትምህርት ክፍል ደረጃ የሚሠሩት የተማሪዎች ፕሮጀክቶች ደረጃቸው ከፍ እንዲል መሠራት እንዳለበት ጠቁመው፥ በተጨማሪም በሙያው ትልቅ ስም ያላቸው አርክቴክቶች ያላቸውን የሥራ ልምድ፣ የፈጠራ ችሎታቸውንና ክህሎት ማካፈል የሚችሉበት መርሃግብር ቢዘጋጅ ጥሩ እንደሆነ ተናግረዋል። አቶ አበበ ይመኑ በመጨረሻም የኪነ-ሕንፃ ትምህርት በባህሪው የተለየ ክህሎት እና የተለየ ከባቢያዊ ሁኔታ የሚፈልግ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።
በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ከፍተኛ ውጤት ላመጡ እና ከ1ኛ-5ኛ ለወጡ ተማሪዎች ሽልማት ተስጥቷል። ከሴቶች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበችው ተማሪ ቃልኪዳን ጥበቡ እንዲሁ ሽልማት የወሰደች ሲሆን ተማሪ በረከት ምትኩ 3.76 በማምጣት የከፍተኛ ማዕረግ የወርቅ ተሸላሚ ሆኗል።
የዘንድሮው ምርቃት በትምህርት ክፍሉ ሦስተኛው ሲሆን 22 ወንዶች እና 7 ሴቶች በድምሩ 29 ተማሪዎች ለምረቃ በቅተዋል። በዕለቱ በተማሪዎቹ የተሠሩ የኪነ-ሕንፃ ንድፎች አውደ ርዕይ በመርሃ ግብሩ ለተገኙ ተሳታፊዎች እና ተመራቂ ቤተሰቦች ተጎብኝተዋል።
ምንጭ፦ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
April 16, 2019 at 12:41 am #10639AnonymousInactiveፌደራሊዝም በኢትዮጵያ እውነታውና አቅጣጫው
በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ማህበራዊ ሳይንስ ፋክልቲ አዘጋጅነት ‹‹ፌደራሊዝም በኢትዮጵያ እውነታውና አቅጣጫው›› በሚል ርዕስ ተጋባዥ ምሁራን በተገኙበት በዩንቨርሲቲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ የግማሽ ቀን ውይይት ተካሄደ።
የመወያያ ፅሁፉ በታዋቂው ምሁር ዶ/ር ታየ ብርሃኑ የቀረበ ሲሆን በዋነኛነትም አቅራቢው በኢትዮጵያ የፌደራልዝም አመሰራረትና አተገባበር፣ የፌደራሊዝም ምስረታ መነሻ ሀሳብ ምንነትና አደረጃጀት የሚሉ ሀሳቦች ላይ ተኩረት ያደረገ ፅሁፍ አቅርበዋል። ዶ/ር ታየ በፅሁፋቸውም ስለ የኢትዮጵያ ፌደራሊዝም ሲናገሩ በጎሳ ላይ መሰራት ያደረገ መሆኑ በአለማችን ያልተለመደ ብቻ ሳይሆን የሃገሪቷን ነባራዊ ሁኔታዎች ያገናዘበ ስለመሆኑ ጥየቄን እንደሚያጭር ገልፀዋል።
ፅሁፍ አቅራቢው አክለውም ሶስቱን የመንግስት ቅርሶች አሃዳዊ፣ ፌደራላዊና ኮንፌዴሪሽን የሚሉትን በመተንተን በኢትዮጵያ እና በሌሎች አገሮች የፌደራሊዝም ባህሪያትና ገፅታ በንፅፅር አቅርበዋል፡፡ በዚህም ከታዳሚው የግልፅነት ጥያቄዎች ቀርበው ምላሽ ተሠጥቶባቸዋል።
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.