እነዚህን የተከለከሉ የምግብ ምርት ዓይነቶች ዝርዝራቸውን በማውጣት ምርቶቹን ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸውና ተቆጣጣሪ አካላት ምርቶቹን በአፋጣኝ ከገበያ ላይ ባለስልጣኑ ጥሪውን አቅርቧል።
አዲስ አበባ (ኤፍ.ቢ.ሲ.) – የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን 57 የምግብ ምርት ዓይነቶችን ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀም አሳሰበ።
ባለስልጣኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በላከው መግለጫ በምግቦቹ ጥራትና ደኅንነት ላይ ባደረገው የገበያ ጥናት የምግብ ምርቶቹ መሰረታዊ የገላጭ የፅሁፍ ክፍተት ያለባቸው፣ የሚመረቱበት ቦታ የማይታወቅ፣ የንጥረ ነገር ይዘት የሌላቸው፣ አምራች ድርጅቶቹ የማይታወቁ፣ የምርት መለያ ቁጥር፣ የተመረቱበት ጊዜ እና የምርቱ ማብቂያ ጊዜ ገላጭ ፅሁፍ የሌላቸው ናቸው ብሏል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም ምርቶቹን ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸውና ተቆጣጣሪ አካላት ምርቶቹን በአፋጣኝ ከገበያ ላይ እንዲሰበስቡም ጥሪውን አቅርቧል።
የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ሕብተረሰቡ እንዳይጠቀማቸው የተከለከሉ የምግብ ምርት ዓይነቶች ዝርዝር፤
- የከረሚላ ምርቶች፦
• ጆሊ ሎሊፖፕ፣
• አናናስ ከረሚላ፣
• ኮላስ ከረሚላ፣
• ኦሊ ፖፕ፣
• ቤስት ከረሚላ፣
• የስ ከረሚላ (ኮፊ ከረሚላ)፣
• ማሚ ሎሊ ፖፕ፣
• ሳራ ከረሚላ፣
• ጃር ሎሊ ፖፕ፣
• ጸሃይ ሎሊ ፖፕ፣
• ዩኒክ ሎሊ ፖፕ፣
• እንጆሪ ከረሚላ፣
• ብርቱካን ከረሚላ፣
• ይናቱ ሎሊ ፖፕ እና
• ሃላዋ ከረሚላ፤
- የማር ምርቶች፦
• አፍያ የተፈጥሮ ማር፣
• ሪትም ማር እና
• በላይ ማር፤
- የገበታ ጨው፦
• ዊዲ የገበታ ጨው፣
• ሱላ የገበታ ጨው፣
• ናይ የገበታ ጨው፣
• ሃያት የገበታ ጨው፣
• አቤት የገበታ ጨው፣
• በእምነት የገበታ ጨው፣
• እናት የገበታ ጨው፣
• አባይ የገበታ ጨው፣
• አባት የገበታ ጨው፣
• ሴፍ የገበታ ጨው እና
• ጣዕም የገበታ ጨው፤
- የለውዝ ቅቤ፦
• ደስታ የለውዝ ቅቤ፣
• አስነብ የለውዝ ቅቤ፣
• ኑኑ የለውዝ ቅቤ፣
• አቢሲኒያ የለውዝ ቅቤ፣
• ብስራት የለውዝ ቅቤ፣
• ፈሌ የለውዝ ቅቤ፣
• ሳባ የለውዝ ቅቤ፣
• አዳ የለውዝ ቅቤእና
• አደይ የለውዝ ቅቤ፤
- የኑግ ዘይት፦
• አደይ አበባ የኑግ ዘይትእና
• ቀመር የኑግ ዘይት፤
- አልሚ የህጻናት ምግቦች፦
• ምሳሌ የህጻናት ምግብ፣
• ኤልሞ የልጆች ምግብ፣
• ሂሩት የህጻናት አጃ፣
• ዘይነብ የህጻናት አጥሚት፣
• ተወዳጅ ገንቢ የህጻናት አጥሚት፣
• ተወዳጅ የህጻናት ሽሮ እና
• ፋሚሊ ሃይል ሰጭና ገንቢ የህጻናት ሽሮ፣
- ሌሎች የተከለከሉ የምግብ ምርት ዓይነቶች፦
• ቪንቶ፤ ዴኮ፣ እስፔሻል፣ ዳና፣ ቃና፣ ላራ፣ ዛጎል አቼቶ፣ ናይስ አቼቶ፣ አምቴሳ አቼቶ፣ ማይ አቼቶ፣ መስ አቼቶ እና ቫይኪንግ አቼቶ ምርቶች
እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን የምግብና ምግብ ነክ ምርቶች ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ታግደዋል። ባለስልጣኑ ከሦስት ሳምንታት በፊትም 46 የብቃት ማረጋገጫ የሌላቸው የታሸጉ የምግብ ምርቶች ላይ እርምጃ መውሰዱንና፤ ሕብረተሰቡም እንዳይጠቀማቸው መከልከሉን መዘገባችን ይታወሳል። ዘገባውንና የተከለከሉትን የምግብ ዓይነቶች ዝርዝር ለማግኘት እዚህ ጋር ይጫኑ።
ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ./ ሰሞነኛ ኢትዮጵያ