የመጀመሪያው የአፍሪካ-ቻይና የንግድ ትርዒት አዲስ አበባ ውስጥ ይካሄዳል

Home Forums Semonegna Stories የመጀመሪያው የአፍሪካ-ቻይና የንግድ ትርዒት አዲስ አበባ ውስጥ ይካሄዳል

  • This topic has 1 reply, 2 voices, and was last updated 6 years ago by Anonymous.
Viewing 1 post (of 1 total)
  • Author
    Posts
  • #10966
    Anonymous
    Inactive

    ኢትዮጵያና ቻይና የኮሙኒኬሽንና ብሮድካስት ሳተላይት በጋራ ለመገንባት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ
    —–
    ኢትዮጵያና ቻይና የኮሙኒኬሽንና ብሮድካስት ሳተላይት በጋራ ለመገንባት የሚያስችላቸውን ፍሬምወርክ ስምምነት ተፈራረሙ።

    ስምምነቱን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ኢንስቲቲዩት ዳይሬክተር ዶክተር ሰለሞን በላይ እና የቻይና ሮኬት ካምፓኒ ምክትል ፕሬዝዳንት ሃን ቺንፒንግ ተፈራርመውታል።

    ግንባታው በኢትዮጵያና ቻይና ባለሙያዎች ትብብር የሚከናወን ሲሆን÷ 50 በመቶ የሀገር ውስጥ እሴት እንደሚጠቀም ነው የተገለጸው።

    በግንባታው የሚሳተፉ ኢትዮጵውያን ከቻይና የቴክኖሎጂ ልምዱን ይወስዳሉ ነው የተባለው።

    ተጠቃሚ መለየት፣ ማስተባበር፣ ፍላጎትና ቦታ መረጣ የመሳሰሉት ተግባራት ሰኔ ወር ላይ ይጀመራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

    የአሁኑ የሳተላይት ግንባታ ፍሬምወርክ ስምምነት ሳተላይትን የስራ እድል መፍጠሪያና ሃብት ማመንጫ ማድረግን ታሳቢ ያዳረገ እንደሆነ ነው የተገለጸው።

    በሁለቱ ሀገራት ትብብር የተሰራችው የመጀመሪያዋ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ህዳር 20 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ህዋ ትላካላች ተብሎ እንደሚጠበቅም ነው ከኢፌዴሪ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ የሚያመላክተው።

    ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Viewing 1 post (of 1 total)
  • You must be logged in to reply to this topic.