ሀገር በቀል የመድኃኒት አምራቾች መሠረታዊ ችግሮች በጥናት ሊለዩ ይገባል ― የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ

Home Forums Semonegna Stories ሀገር በቀል የመድኃኒት አምራቾች መሠረታዊ ችግሮች በጥናት ሊለዩ ይገባል ― የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ

Viewing 2 posts - 1 through 2 (of 2 total)
  • Author
    Posts
  • #9806
    Anonymous
    Inactive

    በሕክምና ባለሙያዎች የሚታዘዙላቸውን መድኃኒት ለመጠቀም የዋጋ ልዩነት እየተፈታተናቸው መሆኑን ነዋሪዎቹ ገለጹ
    —–

    በሕክምና ባለሙያዎች የሚታዘዙላቸውን መድኃኒት ለመጠቀም የዋጋ ልዩነት እየተፈታተናቸው መሆኑን የትግራይ ደቡባዊ ዞን ሦስት ከተሞች ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

    የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ በበኩሉ በጤና ተቋማት የሚታየውን የመድኃኒት አያያዝና አጠቃቀም ሥርዓት ለማሻሻል እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡

    ከከተሞቹ ነዋሪዎች አንዳንዶቹ ለኢ ዜ አ እንዳስታወቁት በመንግሥት ሆስፒታሎች በተመጣጣኝ ዋጋ ይቀርቡላቸው የነበሩትን መድኃኒት ባለማግኘታቸው ከአቅማቸው በላይ ወጪ በማድረግ ለመግዛት ተገደዋል።

    በአላማጣ ሆስፒታል በ200 ብር ይቀርብላቸው የነበረውን የስኳር በሽታ መድኃኒት ከግል መድኃኒት ቤት በ400 ብር በመግዛት እየተጠቀሙ መሆናቸውን የከተማው ነዋሪ አቶ መኮንን ይሄይስ ይገልጻሉ፡፡

    የሚጥል በሽታ መድኃኒት በ150 ብር ይገዙ እንደነበር የሚናገሩት የመሆኒ ከተማ ነዋሪው አቶ ገብሩ ስዩም ከግል መድኃኒት መደብር በ350 መቶ ብር ገዝቼ እየተጠቀምኩ ነው ይላሉ።ዋጋውም ወርኃዊ ገቢያቸው እየተፈታተነ መጥቷል ይላሉ፡፡

    ከኮረም ሆስፒታል በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኙት የነበረው የስኳር በሽታ መድኃኒት በ200 ብር ጭማሪ በመግዛት ላይ መሆናቸውን የሚናገሩት ደግሞ የኮረም ከተማ ነዋሪ ሼክ ኢብራሂም ሰዒድ ናቸው፡፡

    ለመድኃኒቱ በወር የሚያወጡት 450 ብር ወጪውን መቋቋም እንዳላስቻላቸው ተናግረዋል፡፡

    የአላማጣ አጠቃላይ ሆሰፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ሓዱሽ ኃይሉ ከክልሉ ጤና ቢሮ ለሆስፒታሉ የሚላከው መድኃኒት መቀነስ ለእጥረቱ ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

    የማይጨው ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ኪዱ ተክሉ ሆስፒታሉ ከቢሮው የሚላክለት መድኃኒት መጠን እያነሰ በመምጣቱ የተገልጋዩን ፍላጎት ማሟላት እንዳልቻለ ተናግረዋል፡፡

    ሆስፒታሉ በውስጥ ገቢው ተጠቅሞ እጥረቱን ለማቃለል ቢጥርም፤ ተፈላጊው መድኃኒት በአገር ውስጥ ገበያ ለማግኘት ችግር እንደሚያጋጥም አስታውቀዋል፡፡

    ሙሉውን ኢዜአ ላይ ያንብቡ

    #10320
    Semonegna
    Keymaster

    የሕክምና መሣሪያዎችን በሀገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ
    —–

    አዲስ አበባ (ሰሞነኛ)– የሕክምና መሣሪያዎችን በሀገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችል ስምምነት መጋቢት 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ተፈረመ።
    ስምምነቱ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር፣ በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ፥ በጤና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን መካከል ነው የተፈረመው።
    ስምምነቱ በሀገሪቱ ያለውን የሕክምና መሳሪዎችን ፍላጎት ለማሟላትና ለግዢ የሚወጣውን የውጪ ምንዛሪ ለመቀነስ ያስችላል።

    ምንጭ፦ የጤና ሚኒስቴር / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

Viewing 2 posts - 1 through 2 (of 2 total)
  • You must be logged in to reply to this topic.