የወላይታ ልማት ማህበር የተፋጠነ ትምህርት ፕሮጀክት ለመምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ

Home Forums Semonegna Stories የወላይታ ልማት ማህበር የተፋጠነ ትምህርት ፕሮጀክት ለመምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ

Viewing 1 post (of 1 total)
  • Author
    Posts
  • #9596
    Semonegna
    Keymaster

    ወላይታ ሶዶ (ሰሞነኛ)– የወላይታ ልማት ማህበር ለሰው ሀብት ልማት ልዩ የትኩረት ሰጥቶ በሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት የህብረተሰቡን ኑሮ ለማሻሻል በትምህርትና ስልጠና በዕውቀትና ክህሎት የበለጸጉ ዜጎችን ማፍራት ዓላማው አድርጎ የራሱን ጉልህ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

    ለዚህም ዓለማ የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት በማቋቋም፣ በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ በማድረግ፣ በትምህርት ጥራት ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት፣ የቅድመ መደበኛ ትምህርት በማስፋፋትና ዕድሜያቸው ለትምህርት ደርሶ በድህነት ምክንያት በትምህርት ገበታ ላይ መገኘት ያልቻሉ ልጆችን ወደ ትምህርት ቤት በማስገባት ሙሉ የትምህርት ቁሳቁሶችን በማሟላት ከእኩዮቻቸው ጋር እኩል ለማድረግ በአንድ ዓመት ከአንደኛ ክፍል እስከ ሦስተኛ ክፍል በማስተማር በዓመቱ መጨረሻ በየወረዳው ትምህርት ጽ/ቤቶች የሚዘጋጀውን ፈተና ተፈትነው ሲያልፉ ወደ መደበኛው አራተኛ ክፍል ተዛውረው ትምህርታቸውን የሚቀጥሉበት ወደ አራተኛ ክፍል በማዛወር የተፋጠነ ትምህርት ለአፍሪካ በተሰኘ ፕሮጀክት እየተገበረ ይገኛል።

    ቪዲዮ፦ ደቡብ ግሎባል ባንክ ባለፈው የበጀት ዓመት ከታክስ በፊት ሚሊዮን ብር ማትረፉን አስታወቀ

    የወላይታ ልማት ማህበር በሰው ሀብት ልማት ዘርፍ ከሚተገብራቸው ፕሮጀክቶች አንዱ ጀኔቫ ግሎባል ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የሚያከናውነው የተፋጠነ ትምህርት ፕሮጀክት ነው። ይህ ፕሮጀክት ከ2013 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በወላይታ ዞን ውስጥ ከ13,500 በላይ በድህነት ምክንያት ወደ ትምህርት ቤት መግባት ያልቻሉ ህጻናትን ተጠቃሚ አድርጓል።

    ፕሮጀክቱ ከትናንትናው ዕለት ጥር 29 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ለፕሮጀክቱ አመቻች የአንደኛ ደረጃ መምህራን፣ ከዳሞት ሶሬ ወረዳ ለተወጣጡ መምህራንና ርዕሰ መምህራን በተግባር ተኮር የመማር ማስተማር ስነዘዴ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ሲሆን ስልጠናው አስከ የካቲት 2 ቀን 2011 ዓ.ም.. እንደሚቆይ በልማት ማህበሩ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ቆርጋ ላምቤቦ ገልጸዋል።

    ፕሮጀክቱ በተያዘው በጀት ዓመት በዳሞት ሶሬ ወረዳ አስር ትምህርት ቤቶች በ3 ሚሊዮን ብር በ30 የመማሪያ ክፍሎች ለ900 ህጻናት ሙሉ የትምህርት ቁሳቁሶችን በማሟላት አመርቂ ሥራ እየሠራ ይገኛል።

    ከዚህ ጎን ለጎን የእነዚህን ተማሪዎች እናቶች በራስ አገዝ ማህበራት በማደራጀት በመረጡት የገቢ ማስገኛ ሥራዎች ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ በየሳምንቱ ገንዘብ በማስቆጠብና ከራሱ መጠነኛ ድጎማ በማድረግ ገቢያቸውን እንዲያሻሽሉና ወደ ፊት ልጆቻቸው ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ በማድረግ፣ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች አቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠትና የህጻን ለህጻን ትምህርትን በማጎልበት እንደሚሠራ ከፕሮግራም ኦፕሬሽን ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

    ምንጭ፦ የወላይታ ልማት ማህበር / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

    የወላይታ ልማት ማህበር


Viewing 1 post (of 1 total)
  • You must be logged in to reply to this topic.