Home › Forums › Semonegna Stories › የስኳር ፕሮጀክት፣ ኢንቨስትመንትና ህገወጥ አደን በማጎ እና ኦሞ ብሔራዊ ፓርኮች ላይ የፈጠሩት የህልውና አደጋ
- This topic has 0 replies, 1 voice, and was last updated 5 years, 9 months ago by Semonegna.
-
AuthorPosts
-
February 7, 2019 at 8:22 am #9550SemonegnaKeymaster
አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን በማጎ እና ኦሞ ብሔራዊ ፓርኮች ላይ ያሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመፍታት በጥር 28 ቀን የተጀመረው ውይይት መድረክ ጥር 29 ቀን 2011 ዓ.ም. ከቀኑ 7:00 ሰዓት ላይ ተጠናቋል።
በውይይቱ ወቅት ፓርኮቹ ከሚያዋስኗቸው ዞኖችና ወረዳዎች የተወከሉ የአካባቢው ሽማግሌዎች እና የጽህፈት ቤት ኃላፊዎች በስፋት ሐሳባቸውን አንሸራሽረዋል።
ኦሞ ኩራዝ የስኳር ፋብሪካ፣ አርብቶ አደሩ እና የጥበቃ ቦታዎቹ በተቀናጀ መልኩ ችግሩን ለመፍታት መሥራት እንደሚኖርባቸው ተገልጧል። የመንገድ፣ መብራት፣ ትምህርት፣ ውሃ እና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን በቀጠናው በማስፋፋት የአካባቢውን ማኅበረሰብ ልማት ተጠቃሚነት በማስፋት በፓርኩ ላይ የሚደርስ ጫና መቀነስ እንደሚገባው የአካባቢው ኗሪዎች አሳወቀዋል።
◌ ቪዲዮ፦ የአሜሪካ መንግስት ለታሪካዊው የአባ ጅፋር ቤተ መንግስት እድሳት የሚሆን 335,000 ዶላር ልገሳ አደረገ
የአገር ሽማግሌዎች እንደገለጡት፤ ላለፉት ሀምሳ ዓመታት ከፓርኮቹ ጋር በሰመረ መልኩ ኖረናል። ፓርኩ ዛሬ የመጣ ጉዳይ አይደለም የፓርኩ ህልውና የእኛ ህልውና እንደሆነ እንገነዘባለን። የስኳር ፕሮጀክቱም ቢሆን በተቀናጀ እና በተጠና መልኩ ከተተገበረ ጠቀሜታ እንዳለው እናምናለን ብለዋል። ሆኖም ግን የቅንጅት አሠራር ላይ በተለይም የፓርክ አስተዳደር እና ስኳር ፕሮጀክት በሚጠበቀው ልክ ባለመቀናጀታቸው ችግሮች መፈጠራቸውን እና ሁኔታውም በዚህ መልኩ የሚቀጥል ከሆነ አደጋው የከፋ እንደሚሆን አስረድተዋል።
ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተዋረድ ኃላፊነቱን መወጣት ይኖርበታል። ከፌዴራል እስከ ቀበሌ ድረስ የሚጠበቅባቸውን መወጣት አለባቸው ሲሉ በአካባቢው ኗሪዎች በኩል የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል። ተሳታፊዎቹ አጽንኦት ሰጥተው የገለጡት ጉዳይ፤ በየመድኩ የሚደረጉ ይህንን መሰል ውይይቶች የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ ፋይዳቸው የላቀ ቢሆንም በሚፈለገው ልክ ወደ ሥራ መውረድ ካልተቻለ በራሱ መድረክ ውጤታማ አያደርገንም የሚለው ዋናው ነው።
በዚህ ጉዳይ ዙሪያ በርካታ ድረኮች መካሔዳቸውን በመጠቆም ከውሳኔው በኋላ ወደ መሬት ሊወርድ እንደሚገባ አሳስበዋል። ከዱር እንስሳት ቲንክ ታንክ ቡድን እና ከሌሎች ተቋማት የመጡ ባለሙያዎችም ከሁለቱ ፓርኮች ባሻገር የታማ ጥብቅ ስፍራ (Tama Wildlife Reserve) ከፍተኛ የብዝሃ ሕይወት ሀብት ያለው በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶት ጥበቃ ሊደረግለት እንደሚገባ ገልጠዋል።
በማጎ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ በቅርብ ጊዜ የተከሰተውን የጥበቃና ቁጥጥር ሠራተኛ ግድያም አስመልክቶ የሚመለከታቸው አካላት ህገወጦችን ለፍርድ ማቅረብ እንደሚኖርባቸው ተመልከቷል።
በተጨማሪም በውይይቱ የተደረሰበትን ውሳኔ ተከታትሎ በማስፈጸም ውጤታማ መሆን እንደሚኖርበት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል። በቀጣይም በመስክ ሥራዎች የተገኙ ውጤቶች ላይ በተከታታይ ግምገማ ማካሄድ እንዳለበት ተገልጧል።
በመጨረሻም ስኳር ኮርፖሬሽን ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እና ከክልሉ ጋር በስፋት ተወያይተው የጋራ መግባባት ላይ መድረስ እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል። መድረኩ የውይይቱን አጠቃላይ ሐሳብ የያዘ ባለስምንት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተቋጭቷል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን (EWCA) / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.