Home › Forums › Semonegna Stories › ሕገ-ወጥ የገንዘብ እና የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመከላከል ተጨማሪ 36 አዳዲስ ኬላዎች ተቋቁመዋል – የገቢዎች ሚኒስቴር
Tagged: አዲሱ ይርጋ, የገቢዎች ሚኒስቴር, የጦር መሣሪያ
- This topic has 1 reply, 2 voices, and was last updated 5 years, 8 months ago by Anonymous.
-
AuthorPosts
-
April 20, 2019 at 11:22 pm #10701SemonegnaKeymaster
የገቢዎች ሚኒስቴር የተጠናከረ የጉምሩክ ስርዓት እና የተጠናከረ ኬላ ፍተሻ ቁጥጥር ስርዓት መዘርጋቱን ተከትሎ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚያዙ ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያዎችና የተለያዩ አገራት ገንዘቦችም (የገንዘብ ኖቶችም) ጨምረዋል
አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – ለሕገ-ወጥ የገንዘብ እና የጦር መሣሪያ ዝውውር ስጋት ናቸው የተባሉ ቦታዎችን በመለየት ተጨማሪ 36 አዳዲስ የጉምሩክ ኬላዎች መቋቋማቸውን የኢፌዴሪ የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።
አዳዲስ ኬላዎችን በመክፈት እንዲሁም ቦታቸው ትክክል ያልነበሩ ነባር ኬላዎችን ወደ ትክክለኛ ቦታ በመቀየር ሕገ-ወጥ የገንዘብና የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመከላከል ከምንጊዜውም በላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አዲሱ ይርጋ ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ተናግረዋል።
ችግሩን ለመከላከል በተደረው ጥናት በኬላዎች ላይ 1 ሺህ 400 የፖሊስ ኃይል እንደሚያስፈልግ በተጨማሪ ተገልጿል።
ጥናቱን ተከትሎ ተጠሪነቱ ለፌደራል ፖሊስ፣ ስምሪቱ በጉምሩክ ኮሚሽን የሆነ ጥሩ ሥነ ምግባር የተላበሰ፣ ለቦታው የሚመጥን የጉምሩክ ተቆጣጣሪ ፖሊስ እንዲቋቋምና ወደ ሥራ እንዲገባ መደረጉን ዳይሬክተሩ አቶ አዲሱ ይርጋ ገልጸዋል።
የተጠናከረ የጉምሩክ ስርዓት እና የተጠናከረ ኬላ ፍተሻ ቁጥጥር ስርዓት መዘርጋቱን ተከትሎ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚያዙ ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያዎችና ገንዘቦችም ጨምረዋል ነው የተባለው።
የፌዴራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ጀላል አብዲ በበኩላቸው ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ የራሳቸውን ገንዘብ ለማግኘት በሚንቀሳቀሱ ሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ከተለያዩ አገራት (በተለይም ከጎረቤት አገራት) ወደ አገር ውስጥ ይገባል ብለዋል።
የጦር መሣሪያዎቹን መዳረሻ ለማወቅ ጥናት የሚጠይቅ ቢሆንም ከሁኔታ ግምገማ በመነሳት በአገር ውስጥ ጸጥታና የደህንነት ስጋት ያለ በመሆኑ ማንኛውም ሰው ራሱን እና ንብረቱን ለመጠበቅ የጦር መሣሪያ ፍላጎት እንደ አንድ ምክንያት ሊወሰድ ይችላል ብለዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የተለያየ ዓላማና ግብ ያላቸው የታጠቁ ቡድኖችም የጦር መሣሪያ መዳረሻ ሊሆኑ እንደሚችሉም ጠቁመዋል ዳይሬክተሩ።
የዘርፉን ችግር ለመቅረፍ የጦር መሣሪያ ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ውይይት እየተደረገበት መሆኑ ይታዋሳል።
ምንጭ፦ ኢቢሲ/ ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
——
ሌሎች ዜናዎች፦- በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አማካኝነት የተሠራው ባለሞተር ማረሻ ተመረቀ
- አለርት ሆስፒታል ውስጥ ዘመናዊ የሕፃናት ሆስፒታል እና የአደጋ ሕክምና ማዕከል ይገነባሉ
- ዩኒቨርሲቲዎች በሦስት መስኮች ተደልድለው እንዲያስተምሩ የሚያስችል ጥናት እየተጠናቀቀ ነው
- የወልድያ ዩኒቨርሲቲ እና ጎተንበርግ ዩኒቨርሲቲ በትብብር የቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ የትምህርት መስክ ሊጀምሩ ነው
- ሀገር በቀል የመድኃኒት አምራቾች መሠረታዊ ችግሮች በጥናት ሊለዩ ይገባል ― የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ
April 21, 2019 at 12:10 am #10705AnonymousInactive37 ማዳበሪያ (ጆንያ) የካናቢስ ዕፅ ያቤሎ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ ሚያዝያ 8 ቀን 2011 ዓ.ም በዕለቱ ተረኛ ፈታሾች ተያዘ
—–37 ማዳበሪያ (ጆንያ) የካናቢስ ዕፅ ያቤሎ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ ሚያዝያ 8 ቀን 2011 ዓ.ም በዕለቱ ተረኛ ፈታሾች ተያዘ። አደንዛዥ ዕፁ ኮድ3-57519 ኢት የሰሌዳ ቁጥር ባለው የግንባታ ጠጠር በጫነ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ሲጓጓዝ ነበር።
አሽከርካሪው ለጊዜው በማምለጡ ክትትል እየተደረገበት ይገኛል።
ሚያዝያ 8 ቀን 2011 ዓ.ም የተያዘው ካናቢስ ክብደቱ 1280 ኪ.ግ ይመዝናል።
በአንድ ሳምንት ውስጥ ሞያሌ አካባቢ በድምሩ 2720 ኪ.ግ ተይዟል። ትውልዱ አደንዛዥ ዕፅ ከሚያስከትለው አደጋ ለመከላከል እና የሀገር ሰላምና ደህንነት ከሚያውኩ የኮንትሮባንድ ምርቶች ለመጠበቅ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ እንደ አዲስ ተደራጅተው ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው።
ምንጭ፦ የገቢዎች ሚኒስቴር
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.