የጊዳቦ ግድብ ሥራ ፕሮጀክት በዚህ ወር ይመረቃል

Home Forums Semonegna Stories የጊዳቦ ግድብ ሥራ ፕሮጀክት በዚህ ወር ይመረቃል

Viewing 2 posts - 1 through 2 (of 2 total)
  • Author
    Posts
  • #9484
    Anonymous
    Inactive

    የጊዳቦ ግድብና መስኖ ልማት ፕሮጀክት ተመረቀ
    —–
    ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የጊዳቦ ግድብና መስኖ ልማት ፕሮጀክትን መርቀው ከፈቱ።

    በ2002 ዓ.ም ግንባታው የተጀመረው የጊዳቦ ግድብና መስኖ ልማት ፕሮጀክት በሁለት ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል ቢባልም ከተባለለት ስድስት ዓመት ዘግይቶ ዛሬ ተመርቋል።

    ከአዲስ አበባ በ365 ኪሎ ሜትር ርቀት፣ ከዲላ ከተማ አቅራቢያ ጊዳቦ በተሰኘ የደቡብና የኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ቦታ ላይ ነው ግድቡ የተገነባው።

    በሁለት ዓመታት ውስጥ ግንባታው እንደሚጠናቀቅ ታቅዶና በ258 ሚሊዮን ብር በጀት የተጀመረው የጊዳቦ ግድብና መስኖ ልማት ፕሮጀክት በ1 ነጥብ 26 ቢሊዮን ብር ተጠናቋል።

    ግድቡ ከ63 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በላይ ውኃ የመያዝ አቅም ሲኖረው 13 ነጥብ 5 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ ለማልማት ያስችላልም ተብሏል።

    በግድቡ ግራና ቀኝ ዋና ዋና የውኃ ቦዮች መገንባታቸውና በአሁኑ ወቅትም ከ1 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ያካለለ ውኃ በግድቡ መጠራቀሙም ታውቋል።

    በምርቃቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ስለሺ በቀለን ጨምሮ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ፣ የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ፣ የሁለቱ አጎራባች ክልሎች ነዋሪዎች፣ አባ ገዳዎችና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

    የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት

    #9593
    Anonymous
    Inactive

    ጠ/ሚ አብይ አሕመድ የጊዳቦ መስኖ ግድብ ፕሮጀክትን መረቁ
    —–

    የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የጊዳቦ የመስኖ ግድብ ፕሮጀክትን በዛሬው ዕለት መርቀው ከፈቱ፡፡

    በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳና የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሚሊዮን ማቴዎስ ተገኝተዋል::

    ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የጊዳቦ ግድብ ፕሮጀክት የምእራብ ጉጂና ሲዳማ ዞን ህዝቦችን ያቀራረበ መሆኑን አንስተዋል:: የኢትዮጵያ መንግስት ለግብርናና የመስኖ ፕሮጀክቶችን ለማልማት በሰጠው ትኩረት መሰረትም በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ማህበረሰቦችን የሚያቀራርቡ ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች እንደሚቀረፁ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል::

    በመጨረሻም ሁሉም ኢትዮጵያውያን ከመጠየቅ አልፈው የተገኙ ድሎች ላይበመንተራስ ለአገራቸው እድገት የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል::

    የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት መረጃ እንደሚያመለክተው በኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች የሚገኘው ይህ ግድብ 25.8 ሜትር ከፍታና 335 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ከ62.5 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ ውሃ የመያዝ አቅም አለው::

    ግድቡ ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል፡፡

    ዋልታ

Viewing 2 posts - 1 through 2 (of 2 total)
  • You must be logged in to reply to this topic.