ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በሕክምና እና ኪነ-ሕንፃ ዘርፍ ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

Home Forums Semonegna Stories ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በሕክምና እና ኪነ-ሕንፃ ዘርፍ ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

Viewing 3 posts - 1 through 3 (of 3 total)
  • Author
    Posts
  • #10192
    Semonegna
    Keymaster

    በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ እና በሞናኮ ኢንስቲትዩት (Institut de Paléontologie Humaine, Fondation Prince Albert Ier de Monaco) መካከል በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ።
    —–

    ስምምነቱን የድሬዳዋ ከንቲባና የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ኢብራሂም ኡስማን እና የኢንስቲትዩቱ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ሄነሪ ዲ ሉምሌይ (Henry de Lumley) ፈርመዋል ።

    ስምምነቱ ለዩኒቨርስቲው መምህራንና ተማሪዎች የሁለተኛና የሦስተኛ ዲግሪ የትምህርት ዕድልና አጫጭር ስልጠናዎችን የሚያስገኝ ነው ተብሏል።

    በተጨማሪም ስምምነቱ የምርምር ሥራዎችን በጋራ ለመሥራት ዕድል የሚፈጥር ሲሆን በዋናነት በጂኦሎጂና በቅድመ ታሪክ ጥናት ላይ ያተኮረ እንደሚሆን በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል ።

    ከንቲባ ኢብራሂም ኡስማን የስምምነቱ መፈረም በድሬዳዋና በአካባቢው ቅድመ ታሪክ ላይ ጥናትና ምርምር ለማድረግ እድል ከመፍጠሩም ባሻገር ዩኒቨርሲቲውን በሰው ሀይል ለማጠናከር ትልቅ እገዛ ይኖረዋል ሲሉ በፊርማ ስነስርአቱ ወቅት ተናግረዋል።

    ምንጭ፦ የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት

    #10195
    Semonegna
    Keymaster

    የድሬዳዋ ከንቲባ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ
    —–

    የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኢብራሂም ዑስማን ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ ለከተማ አስተዳደሩ ያቀረቡት ጥያቄ በምክር ቤቱ ተቀባይነት አገኘ።

    የኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶሕዴፓ) አባል የሆኑት አቶ ኢብራሂም ለሦስት ዓመታት ከመንፈቅ በከንቲባነት ያገለገሉ ሲሆን፣ በተደጋጋሚ በሚደረጉ ሠልፎች ተቃውሞ ይቀርብባቸው ነበር።

    ምክር ቤቱ በምትካቸው አቶ መሐዲ ዲሬን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ በማድረግ ሹሟል።

    ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ

    #10510
    Anonymous
    Inactive

    የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ለሰላማዊ የመማር ማስተማር ሒደት ትኩረት መስጠቱን አስታወቀ
    —–

    የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሒደቱን ለማስቀጠልና መልካም ስነ-ምግባር የተላበሰ ምሁር ላማፍራት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

    በተለያየ አጋጣሚ ሰላምን ሊያውክ የሚችል የስነ-ምግባር ችግር በታየባቸው ተማሪዎች ላይም አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን ጨምሮ ገልጿል።

    የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶክትር ኡጁሉ ኡኮክ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት መደበኛውን የመማር ማስተማር ሒደት ሰላማዊ ለማድረግ ሁሉንም ያሳተፈ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው።

    በግቢው የሚካሔደው የትምህርት አሰጣጥ ውጤታማ እንዲሆንም የማሪዎችን ስነምግባር ከመከታተል ጀምሮ አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

    በቅርቡም በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ተገቢ ያልሆነ ተግባር የተፈጸመ በማስመሰል ተማሪዎችን ለሁከት ለማነሰሳት ሲሰሩ የተደረሰባቸው 30 ተማሪዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል።።

    “ከነዚህ ውስጥም 13ቱ የስንብት፣ 10 ተማሪዎች ከአንድ እስከ ሁለት ዓመት ከዩኒቨርሲቲው የታገዱ ሲሆን ሰባት ተማሪዎች ላይ ደግሞ የመጨረሻ የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ እርምጃ ተወሰዷል” ብለዋል።

    ዩኒቨርሲተው እርምጃውን ለመውሰድ የተገደደው የተቋሙን ስርዓትና ደህንነት ለማከበር መሆኑን ተናግረዋል።

    ተማሪዎች የተወሰደባቸው እርምጃ ተገቢ አደለም በሚል ቅሬታ ማቅረባቸውንና ጉዳያቸውም በቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ እንደገና እየታየላቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል።

    “በቀጣይም የዩኒቨርሲቲውን ህግና ደንብ የሚጥስ ተማሪ ከተገኘ ተመሳሳይ እርምጃ የመውሰዱ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል” ብለዋል።

    የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በ2006 ዓ.ም. የተቋቋመ ሲሆን ይዞታው ያልታጠረ በመሆኑ ለጸጥታ ችግር የተጋለጠ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት ይገልጻሉ።

    ምንጭ፦ ኢዜአ

Viewing 3 posts - 1 through 3 (of 3 total)
  • You must be logged in to reply to this topic.