ጂንካ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ተገንብተው በ2010 ዓ.ም. ወደ ሥራ ከገቡት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ምንም እንኳን ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆንም የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት በርካታ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል።
ዩኒቨርሲቲው በማኅበረሰብ-አቀፍ አገልግሎት (community-based service) በደቡብ ኦሞ ዞን ውስጥ ለሚገኙ 18 ሁለተኛ ደረጃ እና አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በጥቅሉ ለ19 ትምህርት ቤቶች 510 ኮምፒዩተሮችን ከአንድ ደርጅት እንዲሁም በውጭ ሀገር ከሚኖር አንድ የአካባቢው ተወላጅ ጋር በመተባበር ለእያንዳንዳቸው ሃያ አምስት፣ ሃያ አምስት ኮምቲዩተሮችን ለትምህርት ቤቶቹ የሰጠ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕ/ር ገብሬ ይንቲሶ ገልጸዋል።
Read more: bit.ly/2PKUi2R