Home › Forums › Semonegna Stories › የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 20 የካቢኔ አባላትን ሹመት አጸደቀ – ሴቶችና ወንዶች የካቢኔውን ስልጣን እኩል ተካፍለውታል
Tagged: ሰሞነኛ ኢትዮጵያ, አብይ አህመድ የካቢኔ ሹመት, የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
- This topic has 1 reply, 2 voices, and was last updated 6 years, 3 months ago by Anonymous.
-
AuthorPosts
-
October 16, 2018 at 8:52 am #8100SemonegnaKeymaster
አዲሱ የካቢኔ አባላት ሹመት የቀረበው የአስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል የቀረበውን አዲስ ረቂቅ አዋጅ በምክር ቤቱ መፅደቁን ተከትሎ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል።
አዲስ አበባ – የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ20 አዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመት ውስጥ 50 በመቶ ሴቶች ሆነው እንዲያገለግሉ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የቀረበውን ሹመት ጥቅምት 6 ቀን 2011 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ አፀደቀ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባውን እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከሚሾሙት 20 ካቢኔዎች ውስጥ 10 ሴቶች ሆነው በተሰጣቸው ኃላፊነት እንዲያገለግሉ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
አዲሱ የካቢኔ አባላት ሹመት የቀረበው የአስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል የቀረበውን አዲስ ረቂቅ አዋጅ በምክር ቤቱ መፅደቁን ተከትሎ ነው።
በዚህም መሠረት የሹመቱ ዋና መስፈርት ብቃት፣ የትምህርት ዝግጅትና ለውጥን የመምራት አቅም መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከሚሾሙት ካቢኔዎች 50 በመቶ (በቁጥር፥ ወይም ከ20ዎቹ 10 ሴት) ካቢኔዎች መሆናቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
ይህም በኢትዮጵያ ምናልባትም በአፍሪካ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑም በምክር ቤቱ ተገልጿል።
በዚህ በተደረገው የካቢኔ ሹመት ለውጥ ውስጥ ከዚህ በፊት “የፐብሊክ ሰርቪስ እና ሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር” ተብሎ ይጠራ የነበረው ሚኒስቴር ተለውጦ አሁን “ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን” (Civil Service Commission) በሚል እንደተተካ ታውቋል። ከዚህ በተጨማሪ ሶስት ኮሚሽኖችም በአዲስ መልክ ተካተዋል፤ እነዚህም (1) የሥራ ፈጠራ ኮሚሽን (Job Creation Commission)፣ የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን (Environment, Forestry and Climate Change Commission) እና የፕላንና እድገት ኮሚሽን (Plan and Development Commission) ናቸው።
አዲስ በተዋቀረው ካቢኔ ውስጥ የተሰየሙት ባለስልጣናትና የተሰየሙበት ስልጣን ዝርዝር
- ዶ/ር ሂሩት ካሳው ― የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር
- ዶ/ር ሂሩት ወልደማርያም ― የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
- ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ― የሰላም ሚኒስቴር
- ዶ/ር ሳሙኤል ሆርቃ ― የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር
- ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ― የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር
- አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ ― ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ
- አቶ አህመድ ሺዴ ― የገንዘብ ሚኒስቴር
- ዶ/ር አሚን አማን ሐጎስ ― የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር
- ወ/ሮ አዳነች አበበ ― የገቢዎች ሚኒስቴር
- ኢ/ር አይሻ መሀመድ ሙሳ ― የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር
- አቶ ኡመር ሁሴን ― የግብርና ሚኒስቴር
- ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ― የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር
- ወ/ሮ የዓለምፀጋይ አስፋው — የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር
- ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ― የትራንስፖርት ሚኒስቴር
- አቶ ጃንጥራር አባይ ― የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር
- ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ ― የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
- ዶ/ር ጥላዬ ጌጤ ― አምባዬ የትምህርት ሚኒስቴር
- ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ― የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
- ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረ-እግዚአብሔር ― የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
- ዶ/ር ፍፁም አሰፋ ― የፕላን ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር
ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
October 17, 2018 at 10:21 am #8120AnonymousInactiveጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለፌደራል የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጡ
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለፌደራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጡ።በዚሁ መሠረት፤
1. አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ― በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ
2. አቶ መለስ ዓለሙ ― በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ምክትል ዋና አስተባባሪ
3. አቶ ተመስገን ጥሩነህ ― የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር
4. አቶ ደሴ ዳልኬ ― በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የግብርና እና የመስኖ አማካሪ በመሆን ከጥቅምት 7 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ተሹመዋል።
የተሰጠው ሹመት የትምህርት ዝግጅትና የፖለቲካ አመራር ብቃትን ከግምት ያስገባ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። -
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.