Home › Forums › Semonegna Stories › 28ኛው ዓመታዊ ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባዔ በትግራይ ብሔራዊ ክልል መቐለ ከተማ ተካሔደ
Tagged: መቐለ, የትምህርት ሚኒስቴር, የትምህርት ጉባዔ
- This topic has 0 replies, 1 voice, and was last updated 6 years ago by
Semonegna.
-
AuthorPosts
-
March 22, 2019 at 8:16 am #10357
Semonegna
Keymasterዓመታዊው የትምህርት ጉባዔ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ ዝግጅት ተጠናቆ ለመንግስት ውሳኔ በሚቀርብበት፣ 5ኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት መርሃ ግብር የሦስት ዓመት አፈጻጸም የሚዳሰስበት፣ ለቀጣይ ሥራ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ተለይተው አቅጣጫ የሚቀመጥበት ነበር።
አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የሚያዘጋጀው 28ኛው ዓመታዊ ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባዔ በትግራይ ብሔራዊ ክልል መቐለ ከተማ ተካሔደ። በየዓመቱ ሚካሄደው እና ከመጋቢት 12 እስከ 13 ቀን 2011 ዓ.ም. በቆየው 28ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባዔ በተለያዩ የትምህርት ዘርፍ ጉዳዮች ላይ በመምከር ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
በመድረኩ ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፣ ከሁሉም ክልሎችና ከተለያዩ ከተማዎች አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የተውጣጡ የትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች እና ባለ ድርሻ አካላት እንዲሁም የትምህርት ልማት አጋር አካላት በሀገር አቀፉ የትምህርት ጉባዔ ተሳታፊ ሆነዋል።
● SEMONEGNA on Social Media: Facebook | Twitter | Instagram | Pinterest
ዓመታዊ ጉባዔው የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ ዝግጅት ተጠናቆ ለመንግስት ውሳኔ በሚቀርብበት፣ 5ኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት መርሃ ግብር የሦስት ዓመት አፈጻጸም የሚዳሰስበት፣ ለቀጣይ ሥራ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ተለይተው አቅጣጫ የሚቀመጥበት ሁነኛ ጉባዔ እንደነበር የትምህርት ሚኒስቴር ዘግቧል።
በተጨማሪም በአፈፃጸም ሂደት የተገኙ ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ለአብነት የትምህርት ጥራትና የትምህርት ቤቶች ደረጃ ምደባ ቀርበው በተሳታፊዎች ውይይት እንደተደረገባቸው ታውቋል።
የዘንድሮውን ትምህርት ጉባዔን ለየት የሚያደርገው ሀገር አቀፍ የተማሪዎች ስፓርት ጨዋታ ጋር አቀናጅቶ እንዲካሄድ መደረጉ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዘግቧል።
The 28th National Education conference is being held in Mekelle. Major agendas are; the new Education Road Map strategic issues, ESDP V performance evaluation and 2018 National Learning Assessment study findings and future actions to be taken in the remaining two years. pic.twitter.com/h6XTlcTWTv
— Tilaye Gete Ambaye (PhD) (@DrGete) March 22, 2019
ምንጭ፦ የትምህርት ሚኒስቴር / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
——
ሌሎች ዜናዎች፦- የዓለም የውሃ ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በአዲስ አበባ ከተማ ተከበረ።
- በኢትዮጵያ ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት ተግባራዊ የሚሆን አገራዊ የጤና ደህንነት የትግበራ ዕቅድ ይፋ ሆነ
- ሀገር በቀል የመድኃኒት አምራቾች መሠረታዊ ችግሮች በጥናት ሊለዩ ይገባል ― የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ
- ሰባት ዩኒቨርሲቲዎች፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና STEMpower ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ
- ለዩኒቨርሲቲ መምህራን ጥናትና ምርምር ማድረግ አስገዳጅ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ፤ ፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ ይጀመራል
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.