Home › Forums › Semonegna Stories › 5ኛው ሀገር አቀፍ የግዕዝ ጉባዔ ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቀቀ
Tagged: መቀሌ ዩኒቨርሲቲ, መቱ ዩኒቨርሲቲ, ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ, ብዙነሽ መሠረት, አዲግራት ዩኒቨርሲቲ, የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር
- This topic has 1 reply, 1 voice, and was last updated 5 years, 6 months ago by Anonymous.
-
AuthorPosts
-
June 16, 2019 at 2:19 am #11103AnonymousInactive
አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መፃሕፍት ኤጀንሲ፣ ከትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመቀናጀት “ግዕዝ እና ሥነ-ፈውስ” በሚል ቃል የተዘጋጀው 5ኛው ሀገር አቀፍ የግዕዝ ጉባዔ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ አዲሐቂ ካምፓስ ሲካሄድ ቆይቶ ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ሰኔ 2 ቀን 2011ዓ.ም. ተጠናቋል።
በጉባዔው መክፈቻው ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ክብርት ወ/ሮ ብዙነሽ መሠረት የባህል ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ያስተላለፉት መልዕክት “አገራችን ከ80 በላይ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ብዝሃ-ባህል ያለን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ሀገር መሆናችን እንደአፍሪካ አህጉር መልካም አጋጣሚዎች ቢኖረንም ያሉንን ባህላዊ እሴቶችና ሀገር በቀል ዕውቀቶችን አስተዋውቀን በሚገባ አልተጠቀምንባቸውም። የራሳችን የሆነ ፊደልና የግዕዝ ቋንቋ ያለን ሲሆን፣ እነዚህ ልዩ ጥበቃና እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸው በጥናትና ምርምር እየተደገፈ በመሰነድ ለትውልድ ማስተላለፍ የሁላችን ኃላፊነት ሆኖ ይገኛል ካሉ በኋላ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ላለፉት አራት ዓመታት ተመሳሳይ የጥናትና ምርምር መድረኮች የተካሄዱበት አግባብና ውጤታማነት ሲገመግም ጉባዔዎች በተባባሪ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ በጋራ የሚካሄዱ መሆናቸው እንደ ጥሩ ጅምር የሚወሰድ ነው ብለዋል።
አክለው ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ጉባዔያቱ በቋንቋው ጥናት ዙሪያ ያሉ ጠቃሚ ልምዶች፣ በቋንቋው ጥናት አስፈላጊነት በቂ ግንዛቤ ያገኘንባቸው ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል። የዘንድሮው የመቀሌ ጉባዔ ለየት የሚያደርገው ከግዕዝ ወጣ ብሎ በሥነ-ፈውስ ላይ ትኩረት ማድረጉ ጭምር መሆኑ ነው። የግእዝ ቋንቋ በሥነ-ፈውስ ደረጃ ምን ይላል የሚለው ጥያቄ መልስ የሚሰጥባቸው፣ አቅጣጫና መፍትሄ የሚቀርብባቸው ጥናታዊ ጽሑፎች በጉባዔው የሁለት ቀን ውሎ ይቀርባሉ ተብሎ ታሳቢ ተደርጓል።ሥነ-ፈውስ ኅሊናዊ፣ ሥነ-ፈውስ ሥጋዊ፣ ሥነ-ፈውስ መድኃኒታዊ፣ ሥነ-ፈውስ መንፈሳዊ፣ እያልን ብዙ ነጥቦችን ማንሣት እንችላለን። ሰው በጎ አስተሳሰብ እንዲኖረው፣ ለአገር፣ ለወገን፣ እንዲኖር ጤናማና ያልተዛባ አእምሮ እንዲኖረው ያስፈልጋል። ሁሉን ጎጂ አድርጎ የሚመለከት አእምሮዊ ህልውናዊ እንደሚያስፈልገው አምናለሁ። በዚህ ጉባዔ የስነ-ፈውስ ደረጃ ምንድነው የሚለውን ጥያቄ መልስ የሚሰጡ አማራጮችን በስፋት መዳሰስና በጉባዔው ማጠቃለያም የተሳታፊዎች ንቁ ተሳትፎና ውይይት ለቋንቋው ልማት ለምናካሂደው ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች ሊያግዙ የሚችሉ ምክረ-ሀሳቦች እንደሚመጡ ያለኝ ተስፋ ላቅ ያለ ነው በማለት መልዕክታቸውን በማስተላለፍ ጉባዔው በይፋ አስጀምረዋል።
5ኛው ሀገር አቀፍ የግዕዝ ጉባዔ በተያዘለት መርሃ-ግብሮች መሠረት በግእዝ ላይ የተደረጉ የተለያዩ የጥናትና ምርምር ስራዎች ቀርበው ገለፃና ውይይት ተደርጎባቸዋል። እነዚህም ግዕዝና ሥነ-ፈውስ በመጋቤ ምስጢር ፍሬስብሃት ዱባሌ (ከኢ.ኦ.ተ. ቤተ ክርስቲያን)፣ ግዕዝና ለፈውስ የሚደረስ ጸሎት በዶ/ር አባ ዳንኤል አሰፋ (ከፍራንቺስኮ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ)፣ ግዕዝና የባህል መድሃኒት በመጋቤ ምስጢር ስማቸው ንጋቱ (ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ)፣ ዘይትረከቡ በውስጠ ልሳነ ግዕዝ ሕቡኣነ ስመ እግዚአብሔር ዘይህቡ ፈውሰ ድኅነት በአቶ ሃፍተ ንጉስ (ከአዲግራት ዩኒቨርሲቲ)፣ ግዕዝ (The General Features of the Geez Magical Texts) በአቶ ጉኡሽ ሰለሞን (ከአዲግራት ዩኒቨርሲቲ)፣ ጸበልና ማየ ጸሎት በግዕዝ ባህል ወፊዚክስ በዶ/ር ሀጎስ አብርሃ (ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ) ይገኙበታል።
ምንጭ፦ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር/ ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
June 27, 2019 at 5:02 pm #11207AnonymousInactiveየመቱ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብና ተመራቂ ተማሪዎች የተራቆቱ ቦታዎች ላይ ችግኝ ተከሉ
—–የመቱ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብና ተመራቂ ተማሪዎች የተራቆቱ ቦታዎች ላይ ችግኝ ተክለዋል።
የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና ተመራቂ ተማሪዎች ችግኞቹን የተከሉት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የአካባቢ ጥበቃ እንቅስቃሴ ምክንያት በማድረግ ነው።
ይህ የችግኝ ተከላ የተካሄደው በመቱ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ግቢ ውስጥ ሲሆን፣ በዚህ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ የዩኒቨርሲተው የበላይ አመራሮች፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና የ2011 ዓ.ም. የዩኒቨርሲቲው ተመራቂ ተማሪዎች ናቸው።
በተያያዘ ዜና በመቱ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ድጋፍ ስድስት ለሚሆኑ አባወራዎች የመኖሪያ ቤት እተሰራላቸው መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል።
ቤቱ የሚሰራላቸውም በሚኖሩበት ቀበሌ በኩል የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸውና ምንም ገቢ የሌላቸው መሆናቸው የተረጋገጠ ነው ተብሏል።ምንጭ:- EBC
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.