Home › Forums › Semonegna Stories › ሰባት ዩኒቨርሲቲዎች፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና STEMpower ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ
Tagged: STEMpower, Study in India, ሂሩት ወልደማርያም, ሳሙኤል ክፍሌ, ቅድስት ገብረአምላክ, ነጻ የትምህርት ዕድል, አፈወርቅ ካሱ, የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
- This topic has 1 reply, 1 voice, and was last updated 5 years, 8 months ago by Semonegna.
-
AuthorPosts
-
February 23, 2019 at 11:28 pm #9860SemonegnaKeymaster
አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – STEMpower የተሰኘ መቀመጫውን USA (ሳሌም፥ ማሳቹሴትስ፣ አሜሪካ) ያደረገ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሒሳብ ትምህርቶችን በዩኒቨርሲቲዎች እየረዳ የሚገኝ ሲሆን በአገራችን 13 ማዕከላትን ከፍቶ በትብብር እየሠራና እየረዳ ይገኛል።
ድርጅቱ የድጋፍ አድማሱን በማስፋት በኢትዮጵያ ተጨማሪ 10 ማዕከላትን (ሰባት ማዕከላትን በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች፣ ሶስቱን በተለያዩ ከተሞች እ.አ.አ. በ2019) ለመክፈት ከኢፌዴሪ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲሁም ከሰባቱ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የትብብር ስምምነት የካቲት 14 ቀን 2011ዓ.ም. ተፈራርመዋል።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ሂሩት ወልደማርያም (ፕ/ር) STEMpower ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርቶችን ለማበልጸግ እያደረገ ያለውን ትብብር በማመስገን፥ ዩኒቨርሲቲዎችም ዕድሉን በመጠቀም በአግባቡ ማዕከላቱን ማሳለጥ እንደሚጠበቅባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
◌ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማስተማሪያ ክፍሎቹ ውስጥ ዲጂታል ሰሌዳዎችን መጠቀም ጀመረ።
የሳንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አፈወርቅ ካሱ (ፕ/ር) በበኩላቸው ለሰባቱ ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች (አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ፣ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ እና ወሎ ዩኒቨርሲቲ) ማዕከሉን በመጠቀም በአካባቢዎቻቸው ያሉትን የማኅበረሰብ ችግሮች መፍታት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የSTEMpower አስተባባሪ ዳይሬክተርና ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ቅድስት ገብረአምላክ፥ “STEMpower ከየት ወዴት?” በሚል ርዕስ ከድርጅቱ አመሠራረት ጀምሮ ዓላማውን፣ አሁን ያለበት ሁኔታ እና የወደፊት ዕቅድ አጭር ማብራሪያ ለተሳታፊዎቹ አቅርበዋል። ለወደፊትም ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር በስፋት እንደሚሠሩ ፣ በ2040 የበለጸገች ኢትዮጵያን ማየት እንደሆነ ገልጸዋል።
አገራችን ኢትዮጵያ የራሷን የሆነ ጥንታዊ ታሪክና ባህል ያላት አገር እንደመሆኗ ድርጅቱ በማኅበራዊ ሳይንስ ላይም ትኩረት እንዲያደርግ ከተሳታፊዎቹ አስተያየት ተሰንዝሯል።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ማዕከሎቹ በከፍተኛ ትምህርት እና በሳይንስ ትምህርቶች አከባቢ የሚስተዋሉትን ችግሮች በመቅረፍ የአገሪቱን ብልጽግና ከማረጋገጥ ረገድ መልካም ሁኔታ እንደሚፈጥሩ ገልጸዋል።
ምንጭ፦ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
——
ሌሎች ዜናዎች፦- ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በሕክምና እና ኪነ-ሕንፃ ዘርፍ ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ
- ሁለተኛው SolveIT ሀገር አቀፍ የፈጠራ ውድድር (የኢዲስ አበባ ከተማን) በይፋ ተጀመረ ― የአሜሪካ ኢምባሲ
- በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነው የቀጠና/ወረዳ ጤና መረጃ ስርዓት አካዳሚ (DHIS2) በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተከፈተ
- የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዘላቂ የሆነ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር በአንድነት ለመሥራት ቃል ገቡ
- የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት እና ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር አብሮ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ
March 16, 2019 at 3:15 am #10254SemonegnaKeymasterየህንድ መንግስት በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት ለ3,500 ኢትዮጵያውያን ነጻ የትምህርት ዕድል ይሰጣል
—–የህንድ መንግስት እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር በ2019 ብቻ ለ3ሺህ500 ያህል ኢትዮጵያውያን ነጻ የትምህርት ዕድል ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታወቀ።
‘ስተዲ ኢን ኢንዲያ’ (Study in India) በተሰኘው ተቋም አማካኝነት የሚሰጠው የትምህርት ዕድል የአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠናን ያካተተ እንደሚሆን ታውቋል።
የህንድ መንግስት በሚሰጠው ነጻ የትምህርት ዕድል ከመላው አፍሪካ ተጠቃሚ የሚሆኑ ዜጎች ቁጥር ከ20 ሺህ የሚልቅ እንደሆነ ‘ስተዲ ኢን ኢንዲያ’ አስታውቋል።
ትምህርትና ስልጠና የሚሰጥባቸው መስኮች በርካታ ሲሆኑ የህክምና ዘርፍን የማያካትት መሆኑ ተገልጿል።
በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኑራግ ስሪቫስታቫ እንደገለጹት፤ የህንድ መንግስት ለአፍሪካ አገሮች እየሰጠውን ያለው የአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠና አጠናክሮ የማስቀጠል ፍላጎት አለው።
አክለውም ተቋሙ አጫጭር ስልጠናዎችን በማዘጋጀትና ነጻ የትምህርት እድል ሲሰጥ የቆየ መሆኑን ገልጸው አሁን ደግሞ በፊት ይሰጠው የነበረውን ቁጥር በማስፋትና ረጅም ስልጠናዎችንም ለመስጠት ማሰቡን ገልጸዋል።
38 ሺ ኮሌጆችና 800 ዩኒቨርሲቲዎች ያሏት ህንድ በትምህርት ተቋማት ብዛትና የትምህርት እድሎችንም በማመቻቸት ረገድ ትታወቃለች።
ምንጭ፦ ኢዜአ
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.