Home › Forums › Semonegna Stories › ከመጣንበት መንገድ በላይ የሚቀረን ይከብዳል!! (ለኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች)
Tagged: መቐለ 70 እንድርታ, የኢትዮጵያ ቡና, የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን, ፕሪምየር ሊግ
- This topic has 1 reply, 2 voices, and was last updated 5 years, 6 months ago by Anonymous.
-
AuthorPosts
-
June 15, 2019 at 2:44 am #11090SemonegnaKeymaster
እኛ ያሰባሰበን እግር ኳስ ነው፤ የሚያዝናናን እግር ኳስ ነው፤ የታገልነው ለእግር ኳስ ፍትህ ነው፤ ሌላ ዓላማ የለንም፤ እግር ኳስ ቋንቋችን ነው፤ ከዚህ ቋንቋ ውጪ መናገረ የማይችል ከኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች መሀል ባይገኝ ይመረጣል፤ ምክንያቱም መግባቢያችን እግር ኳስ እና እግር ኳስ ብቻ ነው።
ከመጣንበት መንገድ በላይ የሚቀረን ይከብዳል!! (ለኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች)
ከሊቅ እስከ ደቂቁ፣ ከመምህሩ እስከ ደቀመዝሙሩ፣ ከሹፌሩ እስከ ረዳቱ፣ ከገጠሩ እስከ ከተማው፣ ከገበሬው እስከ ሠራተኛው፣ ከአስተማሪው እስከ ተማሪው፣ ከፖለቲከኛው እስከ አክቲቪስቱ፣ ከመሪው እስከ ተመሪው… የኢትዮጵያን ሕዝብ በአንድ ቃል ሲያነጋግር የነበረው 8 ውሳኔዎች የተለዋወጡበት በቀሽም ደራሲ ተደርሶ በቀሽም ተዋንያን ሲተወን የነበረው ተከታታይ ድራማ በመጨረሻም እውነትን ይዞ እስከ መጨረሻው ሲታገል የነበረው በሕዝባዊው ክለብ ኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት የመጀመሪያው ምዕራፍ ተጠናቋል።
ኢትዮጵያ ቡና ምንም ዓይነት ጥፋት ሳይገኝበት ‘ከመቐለ ሰብዓ እንደርታ ጋር በዝግ ተጫወት’ የሚለውን ቀልድ መሰል መራር ፍርድ ከመላው ደጋፊው ጋር በመሆን እና ሌሎች ለእውነት የቆሙ በርካታ አጋሮቹን አብሮ በማሰለፍ በምርቃና እየወሰኑ፣ በሞቅታ የሚሽረውን ከእግር ኳስ ዕውቀት ነጻ የሆነው የፌዴሬሸኑን [የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን] አድልዎ የተሞላበትን ዝርክርክ አሠራር በአደባባይ አጋልጠን ውሳኔውን በማስቀልበሳችን ደስተኛ ብንሆንም ደስታችን ሙሉ የሚሆነው የማክሰኞውን ጨዋታ በድል ተወጥተን በፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት ኢትየጵያ ቡና ብቻ ከፍ በማድረግ ደስታችንን ሙሉ በማድረግ ተወስኖብን የነበረው ፍርድ ምን ያህል ከእምነት የራቀ ፍርደ ገምድል ውሳኔ መሆኑን ማሳየት ይኖርብናል።
● SEMONEGNA on Social Media: Facebook | Twitter | Instagram | Pinterest | Video | Forum
ውድ ደጋፊዎቻችን፥ ታግለን ካሸነፍነው እና ከመጣንበት መንገድ በላይ የሚቀረን መንገድ ከባድ እንደሆነ በማሰብ ሁሉንም በጥንቃቄ መከወን ይኖርብናል። በዚህ ጨዋታ ላይ ፌዴሬሽኑ የአደባባይ ውርደቱን ለማካካሰ እና የቅጣት ዶሴውን ለመምዘዝ ጥቂት ስህተት ብቻ ከእኛ እንደሚጠበቅ ለማወቅ ነብይ መሆን አያስፈልግም። የመጣንበትን መንገድ መመርመር ብቻ በቂ ነው። ስለዚህ ምዕራፍ ሁሉቱን በድል ለመወጣት ሁሉም ደጋፊ እንደቀድሞ በህብረት በመሆን ዘጠና ደቂቃ ስለ ክለባችኝ ኢትዮጵያ ቡና ብቻ በመዘመር በፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት ይህን ምዕራፍ መዝጋት ይኖርብናል።
በኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ስም እንዲሁም በቡኒው እና ቢጫው መለያ ስር ተደብቆ የተለየ ዓላማውን ለማራመድ ወደ ካንቦሎጆ የሚመጣ ሰው ካለ ኢትዮጵያ ቡና ማለት ለዚህ ደጋፊ ምን እንደሆነ ያልተረዳ ነውና ጥንቃቄ እንዲያደርግ እንመክራለን።
እኛ ያሰባሰበን እግር ኳስ ነው፤ የሚያዝናናን እግር ኳስ ነው፤ የታገልነው ለእግር ኳስ ፍትህ ነው፤ ሌላ ዓላማ የለንም፤ እግር ኳስ ቋንቋችን ነው፤ ከዚህ ቋንቋ ውጪ መናገረ የማይችል ከኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች መሀል ባይገኝ ይመረጣል፤ ምክንያቱም መግባቢያችን እግር ኳስ እና እግር ኳስ ብቻ ነው።
June 18, 2019 at 6:56 pm #11132AnonymousInactiveኢትዮጵያ ቡና ከመቐለ 70 እንደርታ ባዶ ለባዶ ተለያዩ
—–አዲስ አበባ – በኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪምየር ሊግ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ኢትዮጵያ ቡና እና መቐለ 70 እንደርታ ሰኔ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. ያደረጉት ጨዋታ ባዶ ለባዶ ተጠናቋል። በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ የተደረገው 27ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ያለምንም ግብ በሰላም ተጠናቋል።
መቐለ 70 እንደርታ ዛሬ ያለምንም ግብ አቻ መለያየቱን ተከትሎ ሊጉን በ52 ነጥብ እየመራ ከለው ፋሲል ከነማን ተከትሎ በ50 ነጥብ በሁለተኛ ደረጃ ተቀምጧል። በ34 ነጥብ በሊጉ 11ኛ ደረጃ ተቀምጦ የነበረው ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ ነጥቡን ወደ 35 በማሳደግ በሊጉ ያለዉን ደረጃ ወደ 9ኛ ከፍ ማድረግ ችሏል።
የፕሪምየር ሊጉ 28ኛ ሳምንት ቀጣይ መርሃ ግብር የፊታችን ቅዳሜና እሁድ የሚቀጥል ሲሆን ቅዳሜ ጅማ አባጅፋር ከኢትዮጵያ ቡና፣ ሀዋሳ ከተማ ከመከለከያ፣ ስሁል ሽሬ ከደደቢት፣ ባህር ዳር ከተማ ከወላይታ ድቻ ጋር ይጫወታሉ።
እሁድ ሰኔ 16 ቀን 2011 ዓ.ም. የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ፋሲል ከነማ ከሜዳው ዉጭ ከአዳማ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ ሲዳማ ቡና ከድሬደዋ፣ መቐለ 70 እንደርታ በጥሎ ማለፉ ከደቡብ ፖሊስ ጋር እንደሚጫወቱ ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.