ሜቴክ ከጥናት ውጭ አሮጌ 5 አውሮፕላኖችንና 2 መርከቦችን ገዝቶ መንግስት ላይ ጉዳት አድርሷል

Home Forums Semonegna Stories ሜቴክ ከጥናት ውጭ አሮጌ 5 አውሮፕላኖችንና 2 መርከቦችን ገዝቶ መንግስት ላይ ጉዳት አድርሷል

Viewing 2 posts - 1 through 2 (of 2 total)
  • Author
    Posts
  • #8485
    Semonegna
    Keymaster

    ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ሜቴክ ከተቋቋመበት ተልዕኮ ውጭ አገልገሎት መስጠት የማይቸሉ ሁለት መርከቦችና አምስት አውሮፕላኖችን ገዝቶ በመንግስት ላይ ከ24 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት ደርሷል።

    አዲስ አበባ (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)– የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ከተቋቋመበት ተልዕኮ ውጭ አሮጌ ሁለት መርከቦችና አምስት አውሮፕላኖችን ያለአዋጭነት ጥናት ገዝቶ በመንግስት ላይ ጉዳት ማድረሱን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቀ።

    ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ አቶ ብርሀኑ ጸጋዬ ህዳር 3 ቀን 2011 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት፥ ሜቴክ ከተቋቋመበት ተልዕኮ ውጭ አገልገሎት መስጠት የማይቸሉ ሁለት መርከቦችና አምስት አውሮፕላኖችን ገዝቶ በመንግስት ላይ ጉዳት አድርሷል።

    ተቋሙ የተቋቋመበት የራሱ ደንብና መመሪያ ያለው ነው፤ ነገር ግን ከተልዕኮው ውጭ የሆኑ ያለምንም አዋጭነት ጥናት ትልልቅ ግዥዎችን ፈጽሟል ያሉት ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ፥ የግዥዎችን አይነትና የነበረውን ሂደት ዘርዝረው አስረድተዋል።

    ሜቴክ እና የመርከቦች ግዥ

    ቀድሞ የመርከብ ድርጅት ይባል የነበረው የአሁኑ የየባህር ትራንዚትና ሎጅስቲክ ድርጅት አባይ እና አንድነት የሚባሉ ከ28 ዓመት ባለይ ያገለገሉ መርከቦች ነበሩት። እነዚህ መርከቦች በባለሙያ በማስጠናት ከዚህ በላይ መርከቦቹ አገልገሎት ላይ መቆየት የለባቸውም፤ ከቆዩ ከገቢያቸው ወጪያቸው ይበልጣል ስለተባለ እንዲሸጡ የሥራ አመራር ቦርዱ ይወስናል። በዚህ መነሻነት ገዥ ተፈልጎ አንድ የውጭ ድርጅት በሶስት ነጥብ ሶስት ሚሊዮን ዶላር አንዷን መርከብ ለመግዛት ቀረበ።

    ነገር ግን ለውጭ ድርጅት ከሚሸጥ ሜቴክ ቆራርጦ ብረቱን ይጠቀምበት በሚል ድርጅቱ ባቀረበው ዋጋ መሰረት በሶስት ነጥብ 276 ቢሊዮን ብር ሜቴክ እንዲገዛው ይደረጋል። ይሁን እንጂ ሜቴክ መርከቦቹን ቆራርጦ ብረቱን መጠቀም ትቶ መርከቦቹ አዋጭ አይደሉም የሚል ጥናት እያለ ወደ ንግድ ሥራ አስገብቷቸዋል።

    ወደ ንግድ ሥራ ከማስገባቱም በፊት መስከረም 15 ቀን 2005 ዓ.ም. የሜቴክ ሥራ አመራር ቦርድ ተሰብስቦ መርከቦቹ ጅቡቲ ወደብ ላይ ለረጅም ጊዜ ከቆዩና ተጨማሪ ወጭ ካስወጡ በኋላ ለጥገና ወደ ዱባይ ተልከዋል። ለጥገናውክ ከኮርፖሬሽኑ 513 ሚሊዮን 837 ሺህ ብር ወጪ ተደርጎ መርከቦቹ እንዲጠገኑ ተደርጓል። ጥገናውን የሚያከናውኑ ሰዎችን የሚያፈላልጉ ተብለው የተመረጡትም ሜቴክ ውስጥ ያሉ የድልለላ ሥራ የሚሠሩ ከተቋሙ ኃላፊዎች ጋር የስጋ ዝምድና ያላቸው ግለሰቦች ናቸው።

    በመጨረሻም መርከቦቹ ተጠግነው ወጥተዋል ተብለው ወደ ንግድ ገብተዋል። ነገር ግን የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ አድረገው መንቀሳቀስ ስለማይችሉ ለጥገና ብለው የተንቀሳቀሱበትን ፈቃድ የዘው ከኢራን ወደ ሞቃዲሾ በማድረግ እሰከ 500 ሺህ ዶላር አካባቢ ይሠራሉ። ይህ ገንዘብ ግን ወደሜቴክ ያልገባበት ሁኔታ አለ። ሥራውም ቢሆን ሕገ-ወጥ ነው። በመጨረሻ መርከቧ ሥራ መሥራት እንደማትችልና ፈቃድ እንደማታገኝ ሲታወቅና ተቃውሞ ሲያጋጥማቸው መርከቧ በሁለት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ብረ ተሽጣለች።

    ሜቴክ እና የአውሮፕላን ግዥ

    ይሄ ግዥ የተፈጸመበት ዓላማ በራሱ ችግር የለበትም። “አገራዊ ፐሮጀክቶችን በአውሮፕላን ታግዞ ለመከታተል” በሚል ያለምንም ጨረታ ከአንድ የእሥራኤል ኩባንያ በ11 ሚሊዮን 732 ሺህ 520 ብር ነው ግዥው የተፈጸመው። ነገር ግን ወደ ንግድ መግባት አለብን ተብሎ ፈቃድ በማውጣት ለመሥራት ተሞክሮ አልተሳካም።

    አውሮፕላኖቹ ከ50 ዓመት በላይ ያገለገሉ፣ የሚጠቀሙት ነዳጅ እጅግ ውድ፣ የቴክኒክ ችግርም ያለባቸውና ጥቅም ላይ ሊውሉ የማይቸሉ ናቸው ተብለው አራቱ ተቀምጠዋል። አንደኛው ግን እስካሁን የት እንዳለ አልታወቀም።

    በአጠቃላይም በሁለቱ ግዝዎች በመንግስት ላይ ከ24 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት ደርሷል።

    ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

    ሜቴክ

    #8493
    Semonegna
    Keymaster

    ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በቁጥጥር ስር ውለው ወደ አዲስ አበባ እየመጡ ነው
    ****************************************************

    የቀድሞ የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በቁጥጥር ስር ዋሉ።

    ከኮርፖሬሽኑ አሰራር ጋር በተያያዘ በወንጀል ተጠርጣሪ የሆኑት የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በምዕራባዊ ትግራይ በኩል ባታር በተሰኘው አካባቢ ነው በህብረተሰቡ እና በመከላከያ ኃይል ትብብር የተያዙት።

    በአሁኑ ሰዓትም ወደ አዲስ አበባ ተይዘው እየመጡ ነው።

    በትናንትናው እለት የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ከፍተኛ የገንዘብ ምዝበራ በመፈፀማቸው የተጠረጠሩ 27 ከፍተኛ የሜቴክ አመራሮች እና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ማስታወቁን ሪፖርተራችን አብዲ ከማል ከስፍራው ዘግቧል።

Viewing 2 posts - 1 through 2 (of 2 total)
  • You must be logged in to reply to this topic.