ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ – አዲስ አበባን እንደስሟ አድርጎ ለትውልድ ለማሸጋገር የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል

Home Forums Semonegna Stories ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ – አዲስ አበባን እንደስሟ አድርጎ ለትውልድ ለማሸጋገር የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል

Viewing 1 post (of 1 total)
  • Author
    Posts
  • #9923
    Semonegna
    Keymaster

    አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ አድርጎ ለትውልድ ለማሸጋገር የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተናገሩ።

    የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) እንደዘገብው፥ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የአዲስ አበባን የወንዞችና ወንዝ ዳርቻዎች ማልማት አዲስ ፕሮጀክትን በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት “በተራሮች ከፍታ ላይ የምትገኘው አዲስ አበባ እንደ ስሟ አዲስ ሆና ለትውልድ የምትሸጋገር ውብ ከተማ ማድረግ ይገባል” ብለዋል።

    በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) መሪነት በከተማ አስተዳደሩ አስተባባሪነትና በከተማዋ ነዋሪዎችና በወጣቶች ትብብር ለትውልድ የሚሸጋገር ድንቅ ከተማ መገንባታችንን እንቀጥላለንም ነው ያሉት ኢንጂነር ታከለ። ፕሮጀክቱ ለትውልድ የሚተላለፍ የትውልድ አሻራ ያለበትና ሁላችንም የጋራ እሴቶቻችንን የምናስተላልፍበት በመሆኑ ልንደሰት ይገባል በማለት አጽንዖት ሰጥተዋል።

    ፕሮጀክቱ ከተማዋ እንደስሟ እንድትኖር ወንዞችና የወንዞች ዳርቻዎች ሁሉ የቆሻሻ መናኸሪያ ሳይሆኑ የሰው ልጅ በተለይም ደግሞ ወጣቶች ቁጭ ብለው በመነጋገር ሀሳብ የሚቀያየሩበትና ለቀጣይ ትውልድ የተሻለች የጋራ ሀገር ለመገንባት የሚያስችል መሆኑንም አብራርተዋል።

    ፕሮጀክቱ ከእንጦጦ ተራራ ተነስቶ ፒያሳን አካሎ እስከ ብሔራዊ ቤተመንግስት የሚዘልቅ እንዲሁም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል እስከ ብሔራዊ ቤተመንግስት ገራዥ የሚያልፍ ሆኖ እንደማሳያ የሚጀመር ነው ብለዋል።

    በከተማዋ የተያዘው የልማት የወደፊት ስሌት (strategy) ሕዝቦቿ ከልማቱ ጋር የሚያድጉና የሚበለፅጉ እንዲሆኑ የሚያስችል እንጂ አንዱን የህንፃ ባለቤት በማድረግ ሌላውን ለማፈናቀል የሚሠራ አለመሆኑንም ተናግርዋል ኢንጂነር ታከለ ኡማ።

    የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ በበኩላቸው ከተማዋ ብዙ ታላላቅ ቅርሶች ያሏት፣ አብያተ መንግስት፣ ቤተ እምነቶችና እንደመርካቶ ያሉ የታላላቅ ገበያዎች መገኛ ናት ብለዋል። ከዚህም ባሻገር የኢትዮጵያ ምርጥ ሕዝቦች በፍቅር በአንድነት በደም ተሳስረው የሚኖሩባት ከተማ መሆኗንም አስረድተዋል ኃላፊው።

    ራሳችን ተንፍሰንና ተዝናንተን ቁጭ ብለን የምንወያይበት እነጂ የተጣበበ የአስተሳሰብ መንገድ እንዳይኖረን ሰፋ ያለ የስፍራ አጠቃቀምን የሚያሳዩ የቱሪስት መዳረሻዎች የሉንም ያሉት ኃላፊው፤ ፕሮጀክቱ ለልጆቻችን ልናተርፍላቸው የሚገባ የመዝናኛ፣ የመነጋገሪያና የመናፈሻ ቦታ እንዳለውም ተናግረዋል። ከዚህም ባሻገር ልጆቻችን ሌሎች ሰዎችን ጋብዘው የሚጠቀሙበት የቱሪስት መዳረሻ እንደሚሆንም ተናግረዋል።

    ምንጭ፦ ኢዜአ / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

    ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ


Viewing 1 post (of 1 total)
  • You must be logged in to reply to this topic.