ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ጥር 6 ቀን ለኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች በሰጡት ገለጻ አስካሁን ባለው ሂደት ኢትዮጵያዊያን ዳያስፖራዎች በቀረበላቸው ሀገራዊ ጥሪ አማካኝነት በዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በኩል 1 ነጥበ 9 ሚሊዮን ዶላር አዋጥተዋል።
አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – በዳያስፖራ ትረስት ፈንድ አንድ ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ዶላር መሰብሰቡን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ጥር 6 ቀን 2011 ዓ.ም. አስታወቁ። እስካሁን ባለው ሂደት በትረስት ፈንዱ አማካኝነት 12 ሺህ 9 መቶ ዳያስፖራዎች መዋጮ አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የ2011 ዓ.ም. አገራዊ በጀትን በአስጸደቁበት ወቅት ኢትዮጵያዊ ዳያስፖራ ሁሉ በአገሩ ልማት ላይ እንዲሳተፍ በቀን የ1 ዶላር መዋጮ መጠየቃቸው ይታወሳል። ይሁን እንጂ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ዳያስፖራው ለጠቅላይ ሚነስትሩ የሰጠው ምላሽ አጥጋቢ እንዳልሆነ ሲነገር ቆይቷል።
◌ Commercial Bank of Ethiopia to start diaspora mortgage loan to ease Ethiopians’ home ownership
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ጥር 6 ቀን ለኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች በሰጡት ገለጻ አስካሁን ባለው ሂደት ዳያስፖራው በቀረበለት ፈንድ አማካኝነት 1 ነጥበ 9 ሚሊዮን ዶላር አዋጥቷል።
በመዋጮውም 12 ሺህ 900 ዳያስፖራዎች እንደተሳተፉ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ከዚህም ውስጥ 10 ሺህ 300 የሚሆኑት በአሜሪካ የሚኖሩ ናቸው። 1ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላሩ ከእነዚህ በአሜሪካ ከሚኖሩ ዳያስፖራዎች መሰብሰቡን አክለዋል።
በአሜሪካ ካሉ ግዛቶች መካከል ሜሪላንድና ካሊፎርኒያ እንደቅደም ተከተል ከፍተኛ መዋጮ የተገኘባቸው አካባቢዎች መሆናቸውንም ገልጸዋል።
በዓለም ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዳያስፖራዎች ቢኖሩም መዋጮው እምብዛም ያልሆነበት ምክንያት መተማመኑ ባለመፈጠሩ መሆኑንም ጠቅላይ ሚንስትሩ አስገንዝበዋል።
◌ The case of Ethiopian diaspora, their interest to invest in Ethiopia and bureaucratic bottlenecks
የሚዋጣውን ነገር በሚታይ ነገር ላይ በማዋል መተማመንን ለመፍጠር እንደሚሠራ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በፈንዱ የተሰበሰበው ገንዘብ ግን 10 ሚሊዮን ዶላር አስኪደርስ ጥቅም ላይ እንደማይውል ገልጸዋል።
ይህ የሚሆነውም በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች መካካል ፍትሃዊ ክፍፍልን ለመፍጠር መሆኑንም ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያውያን ዳያስፖራ ትርስት ፈንድ የተቋቋመው በነሀሴ ወር 2011 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋና ሰብሳቢነት ሲሆን፥ በዋነኝነት በተለያዩ የአርሜሪካ ግዛቶች የሚኖሩ 15 ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በአማካሪ ካንስል አባልነት ያቀፈ ቡድን በበላይነት ይከታተለዋል።
◌ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ድረ-ገጽ: EDTF
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
——
ተመሳሳይ ዜናዎች፦