Home › Forums › Semonegna Stories › የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ራሷን ንግሥተ ነገሥት ብላ በምትጠራው ግለሰብ ላይ ምርመራ አጠናክሮ መቀጠሉን አስታወቀ
- This topic has 1 reply, 1 voice, and was last updated 4 years, 7 months ago by Anonymous.
-
AuthorPosts
-
May 2, 2020 at 3:55 am #14333AnonymousInactive
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ራሷን ንግሥተ ነገሥት ብላ በምትጠራው ግለሰብ (እህተ ማርያም) ላይ ምርመራ አጠናክሮ መቀጠሉን አስታወቀ
ሚያዝያ 21 ቀን 2012 ዓ.ም. ማምሻውን እህተ ማርያም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተላልፋ በቁጥጥር ስር ስትውል አብረው ፖሊስ ጣቢያ ድረስ የመጡ 30 የሚጠጉ ተከታዮቿ ግርግር ሊፈጥሩ ቢሞክሩም ፖሊስ መክሮ ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል።
በጥላሁን ካሣ (ኢብኮ) |
አዲስ አበባ – የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ራሷን “ንግሥተ ነገሥት ዘ–ኢትዮጲያ” ብላ በምትጠራው እና የአራት ልጆች እናት በሆነችው እህተ ማርያም ላይ ምርመራ አጠናክሮ መቀጠሉን አስታወቀ። ፖሊስ ግለሰቧን በቁጥጥር ስር ያዋላት ሚያዝያ 21 ቀን 2012 ዓ.ም. (የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የወታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመጣሷ ምክንያት) ነበር።
ከሁለት ዓመት በፊት ባሏ በሞት የተለያት የ43 ዓመቷ እህተ ማርያም በሚል መጠሪያ የምትታወቀው ሴት ስለ ማንነቷ ለፖሊስ ስትገልጽ፥ ትክክለኛ መጠሪያ ስሟ ትዕግሥት ፍትህአወቀ አበበ መሆኑንና መኖሪያዋ አዲስ አበባ ውስጥ ኮልፌ መብራት ኃይል አካባቢ እንደሆነ ተናግራለች።
ግለሰቧ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጣስ በመኖሪያ ቤቷ በሃይማኖት እና በምገባ ስም እስከ መቶ የሚደርሱ ሰዎችን ሰብስባ በመገኘቷ በቁጥጥር መዋሏ ይታወቃል።
በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ ልዩ ወንጀሎች ምርመራ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር በድሉ ግርማ፥ ተጠርጣሪዋ እህተ ማርያም በማኅበራዊ ድረ ገጽ ኮሮናቫይረስ የለም ተሳሳሙ፣ ተቃቀፉ፣ ተጨባበጡ በማለት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመፃረር የዜጎችን ሕይወት ለአደጋ አጋልጣለች በሚል መጠርጠሯን ገልጸዋል። አክለውም ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ የተጠረጠረችበት ወንጀል ጉዳይ እየታየ መሆኑንም ተናግረዋል።
ተጠርጣሪዋ በ2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ መሀል ላይ የሚገኘውን ኮከብ ቀድዳ አውጥታ በማቃጠሏ መቀጣቷም ተጠቅሷል። ግለሰቧ ከሰማይ ታዝዣለሁ (የማደርገውን ሁሉ የማደርገው ከሰማይ በሚመጣልኝ መልእክት ነው) በማለት ማረሚያ ቤት ድረስ በማቅናት ታራሚዎችን ልታስወጣ ስትሞክር እጅ ከፍንጅ ተይዛ መቀጣቷንም ኢንስፔክተሩ ገልጸዋል።
ሚያዝያ 21 ቀን 2012 ዓ.ም. ማምሻውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተላልፋ በቁጥጥር ስር ስትውል አብረው ፖሊስ ጣቢያ ድረስ የመጡ 30 የሚጠጉ ተከታዮቿ ግርግር ሊፈጥሩ ቢሞክሩም ፖሊስ መክሮ ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ማድረጉንም አመልክተዋል። ከእርሷ ጋር በግብረ አበርነት የተጠረጠሩ ሁለት ሴቶች ግን ምርመራ እየተካሔደባቸው መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር በድሉ ግርማ ተናግረዋል።
ግለሰቧ ለፖሊስ በሰጠችው የእምነት ክህደት ቃል ርትዕት ተዋሕዶ የተሰኘ ሃይማኖት ለማስተዳደር ከሰማይ እንደተላከች እና ራሷም ንግሥተ ነገሥት ዘኢትዮጵያ መሆኗን ተናግራለች።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ)/ ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
May 16, 2020 at 3:09 am #14522AnonymousInactiveየአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እህተ ማርያም በሌሎች ወንጀሎችም በመጠርጠሯ ምርመራውን እያጠናከረ መሆኑን ገለጸ
አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ራሷን ንግሥተ ነገሥት (እህተ ማርያም) እያለች በምትጠራው ትዕግሥት ፍትህአወቅ ላይ የአስቸኳይ አዋጁን ከመጣስ በተጨማሪ በሌሎች ወንጀሎችም በመጠርጠሯ ምርመራውን እያጠናከረ መሆኑን ገለጸ።
በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ ልዩ ወንጀል ዲቪዥን ምርመራ ኃላፊ ኢንስፔክተር በድሉ ግርማ ትዕግሥት ፍትህአወቅ (እህተ ማርያም) ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነቴንና ቀኖናዬን አቃላለች መገልገያ አልባሳቴን ያለ አግባብ ጥቅም ላይ አውላለች በሚል ያቀረበችው ክስም በምርመራው እየታየ እንደሆነ ገልጸዋል።
ግለሰቧ ሃይማኖትም ሆነ ማኅበር ለመመሥረት ከኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢፌዲሪ) የሰላም ሚኒስቴር ተገቢውን ፈቃድ ሳታገኝ ርትዕት ተዋሕዶ የሚል ሃይማኖት መሥርታ ተከታዮቿን አላግባብ እየሰበሰበች የነበረበት ሂደትም እየተመረመረ ነው ተብሏል።
ተጠርጣሪዋ የትዳር አጋሯ በትራፊክ አደጋ እንደሞተ ብትገልጽም የሟች ቤተሰቦች ይህ ስለመሆኑ ምንም ማስረጃ ባለመኖሩ ተጨማሪ ምርመራ ይደረግልን ማለታቸውም ምርመራው የሚያተኩርበት ሌላ ጭብጥ መሆኑንም ኢንስፔክተሩ ገልጸዋል።
በተጠርጣሪዋ ቤት የተገኘው አስከሬንም ለምርመራ ወደ ሆስፒታል መላኩንም ኢንስፔክተር በድሉ ገልጸዋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን/ ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
—–
ሌሎች ዜናዎች፦- የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ራሷን ንግሥተ ነገሥት ብላ በምትጠራው ግለሰብ (እህተ ማርያም) ላይ ምርመራ አጠናክሮ መቀጠሉን አስታወቀ
- በመላው ዓለም የተስፋፋውን የኮሮና ወረርሽኝ ለመግታት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ
- የኢትዮጵያ የለውጥ ሂደት፣ የቀጣዩ ምርጫ አገራዊ ፋይዳ እና የተደቀኑ አደጋዎች ― ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ (ኢዜማ) ያስተላለፉት መልዕክት
- ኢትዮጵያ ውስጥ የኮቪድ-19 (ኮሮና ቫይረስ) ስርጭትን እና ለመከለከል የሚደረገውን ጥረት ወቅታዊ መረጃ
- ዓለምን እጅግ ያሰጋው የኖቬል ኮሮና ቫይረስ የተጠቂዎች ቁጥር እጅግ አሻቅቧል፤ ቻይና ውስጥ በአንድ ቀን ብቻ 57 በበሽታው የተጠቁ ሰዎች ሞተዋል። የተለያዩ ሀገራት ዜጎቻቸውን ከዉሃን ከተማ ማስወጣት ጀምረዋል
- የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የተቋቋመው “ሰው ነኝ ሌሎችንም እረዳለሁ” የተባለው ኮሚቴ፣ በመንግሥት የተቋቋመው የአማካሪ ምክር ቤት እና ኢትዮጵያ ውስጥ በሽታው የተገኘባቸው ሰዎች ያሉበት ሁኔታ
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.