አገራዊ የጤና ደህንነት የትግበራ ዕቅድ ይፋ ሆነ

Home Forums Semonegna Stories አገራዊ የጤና ደህንነት የትግበራ ዕቅድ ይፋ ሆነ

Viewing 1 post (of 1 total)
  • Author
    Posts
  • #10277
    Semonegna
    Keymaster

    በኢትዮጵያ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ተግባራዊ የሚሆን አገራዊ የጤና ደህንነት የትግበራ ዕቅድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና የልማት አጋሮች በተገኙበት ዛሬ ይፋ ሆነ።

    አዲስ አበባ (ሰሞነኛ)– የጤና ደህንነት የትግበራ ዕቅድ አንዲት አገር በዓለም አቀፍ የጤና ህግጋት ላይ የተጠቀሱትን መሠረታዊ የሕብረተሰብ ጤና ስጋቶችንና አደጋዎችን ለመከላከል፣ አስቀድሞ ለመለየትና ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል አቅም ለማጠናከር የተቀመጡ ግቦችን እንድታሟላ የሚያስችል ዕቅድ ሲሆን በሃገሪቱ ሙሉ ባለቤትነት የሚቀረጽ የትግበራ ዕቅድ ነው።

    ማንኛውም የዓለም አቀፍ የጤና ሕግጋት ፈራሚ አገር ይህንን ዕቅድ እንደሚያዘጋጅ ሁሉ ኢትዮጵያም የዚህ ስምምነት ፈራሚ እንደመሆኗ በተደጋጋሚ የሚገጥሟትን የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን ለመቋቋም የሚያስፈልጓትን አቅም ለመገንባት ዕቅዱን ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኗል።

    የትግበራ ዕቅዱን በአዲስ አበባ በይፋ መጀመሩን ያበሰሩት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር  አቶመቀ መኮንን፥ ስለ አንድ አገር ሰላምና ደህንነት ስንናገር የሕዝቦቻችንን የጤና ደህንነት ጭምር አያይዘን እንደምንናገር መገንዘብ እንደሚገባ ጠቁመው፥ አገራዊ ዕቅዱ ወቅታዊና እንደአገር የሚያጋጥሙንን ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ አደጋዎችን ቀድሞ ለመከላከልና ብዙ ጉዳት ሳያደርሱ ምላሽ ለመስጠት ያስችለናል ብለዋል።

    ◌ SEMONEGNA on Social Media: FacebookTwitterInstagramPinterest

    የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን በበኩላቸው ሃገሪቱ እ.ኤ.አ በ2016 የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ከአፍሪካ ቢሮ በመጡ ገምጋሚዎች የጤና ደህንነቷ ያለበትን ደረጃ ማስመዘኗን ገልጸው፥ ከግምገማው በተገኙ ግብረ መልሶች እና በሃገሪቱ ከተከሰቱ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ምላሽ አሰጣጣችን የተግባር ልምድ በመውሰድ አገራዊ የጤና ትግበራ ዕቅድ አዘጋጅታለች ብለዋል።

    የትግበራ ዕቅዱን ለመፈጸም በጀት ስለሚጠይቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ያለንን ሃብት አቀናጅተን በመጠቀም ለዕቅዱ መሳካት የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይገባናል ያሉት ደግሞ የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ዶ/ር ፓሚላ ሙቱሪ ናቸው።

    የኢትዮጵይ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ በበኩላቸው፥ እንደ ኩፍኝና ቢጫ ወባን የመሳሰሉ ወረርሽኞችን ለመከላከልና በዓለም ደረጃ ለሚከሰቱ እንደ ኢቦላ እና ዚካ ቫይረስ ያሉ ወረርሽኞችን ለመከላከል አገራዊ የጤና ደህንነት የትግበራ ዕቅድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።

    ለዕቅዱ ትግበራ 368 ሚሊዮን 764 ሺህ 777 ዶላር የሚያስፈልግ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 77 በመቶ የሚሆነው የክትባት ሽፋንን ለማሳደግ የሚውል ይሆናል።

    አገራዊ የጤና ደህንነት የትግበራ ዕቅዱ ለአምስት ዓመት ማለትም ከ2011/12 እስከ 2016/17 ዓ.ም ድረስ የሚተገበር ይሆናል።

    ምንጭ፦ የጤና ሚኒስቴር / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

    አገራዊ የጤና ደህንነት


Viewing 1 post (of 1 total)
  • You must be logged in to reply to this topic.