Home › Forums › Semonegna Stories › ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ቅድመ ዝግጅት እያደረገች ነው
Tagged: ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር, የዓለም ንግድ ድርጅት
- This topic has 0 replies, 1 voice, and was last updated 5 years, 10 months ago by Semonegna.
-
AuthorPosts
-
February 24, 2019 at 1:01 am #9864SemonegnaKeymaster
ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ከየካቲት 10 ቀን 2003 (እ.ኤ.አ.) ጀምሮ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችንና አባል ለመሆን ብቁ የሚያድርጓትን የማሻሻያ እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች።
አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የሚያስችላትን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየሠራች መሆኑን ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የባለ ብዙ ዘርፍ የንግድ ግንኙነትና ድርድር ዳይሬክተር አቶ ሙሴ ምንዳዬ የዓለም ባንክ የንግድና ክልላዊ ትብብር ዳይሬክተር ጋር ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደትን እና የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና ስምምነትን ለማጽደቅ እያደረገች ባለው እንቅስቃሴ ዙሪያ በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በተወያዩበት ወቅት ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እና በድርድሩ ሂደት የሚገጥሟትን ችግሮች ተቋቁማ ወደ ድርጅቱ እንድትቀላቀል ለማድረግ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
◌ ምንም እንኳን ኢትዮጵያ በተከታታይ የኢኮኖሚ እድገት ብታስመዘግብም የግል ዘርፉ በኢኮኖሚው ውስት ያለው ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ነው
አቶ ሙሴ አያይዘው በአሁኑ ወቅት መንግስት በተለይም በአገልግሎት ንግድ ሰጭ ተቋማት ላይ እየሠራቸው ያሉት የማሻሻል (ሪፎርም) ሥራዎች እና የቴሌኮም ድርጅትን የቁጥጥር/ርጉላቶሬ/ መስሪያ ቤት የተለያዩ ዘርፎች ለግሉ ሴክተር ለማስተላለፍ በሚኒስትሮች ምክር ቤት መጽደቁ ሀገሪቷ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የምታደርገውን ድርድር ሊያግዝ የሚችል መልካም አጋጣሚ ነው ያሉ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ በ2011 ዓ.ም. 4ኛውን የሥራ ቡድን ስብሰባ ለማካሄድ የተለያዩ ዶክመንቶችን የማዘጋጀት ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል።
በዓለም ባንክ የማክሮ፣ ንግድና ኢንቨስትመንት ዳይሬክተር ወ/ሮ ካሮሊን ፍረንድ (Caroline Freund) በበኩላቸው ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በዓለም የንግድ ድርጅት ድርድር እና በአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ዙሪያ የሚሠራቸው ሥራዎች መልካም መሆናቸውን ገልጸው ወደፊት ለሚደረጉ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድርኮች እንዲሁም ዘመናዊና ደረጃውን የጠበቀ ቢሮና መሠረተ- ልማት እንዲኖር ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።
እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን 1995 በ124 አገራት የአባልነት ፊርማ የተመሠረተውን የዓለም ንግድ ድርጅት (World Trade Organization)፣ በአሁኑ ሰዓት ዋና መቀመጫውን ጄኔቭ ከተማ፣ ስዊዘርላን አድርጎ 164 አገራትንም በአባልነት አቅፏል።ኢትዮጵያም የዚህ ድርጅት አባል ለመሆን ከየካቲት 10 ቀን 2003 (እ.ኤ.አ.) ጀምሮ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችንና አባል ለመሆን ብቁ የሚያድርጓትን የማሻሻያ እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች።
ምንጭ፦ በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
——
ሌሎች ዜናዎች፦- “ብሔራዊ የግብር ገቢ ንቅናቄ” በጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት በይፋ ተጀመረ
- ባለፉት 6 ወራት ለኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 484 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡ ተገለጸ
- አንበሳ የከተማ አውቶቡስ በአንዳንድ አካባቢዎች አገልግሎቱን በማቋረጡ ተገልጋዮች ለችግር ተዳርገዋል
- የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ መቋቋሙን ተከትሎ ወደ ተግባር ለመግባት የመዋቅርና የሕግ ማዕቀፍ ሥራን አጠናቀቀ
- ሀገር በቀል የመድኃኒት አምራቾች መሠረታዊ ችግሮች በጥናት ሊለዩ ይገባል ― የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.