Home › Forums › Semonegna Stories › ኦርቢስ በራሪው የአይን ሆስፒታል አዲስ አበባ ውስጥ ስልጠና እየሰጠ ነው
Tagged: ኦርቢስ ኢንተርናሽናል, ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር
- This topic has 0 replies, 1 voice, and was last updated 6 years, 3 months ago by Semonegna.
-
AuthorPosts
-
October 3, 2018 at 7:36 pm #7870SemonegnaKeymaster
አዲስ አበባ (ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር)– ኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የ20ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን እያከበረ ሲሆን ይህን ተከትሎም ኦርቢስ በራሪው የአይን ሆስፒታል በቦሌ ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ የስልጠና አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ከበደ ወርቁ በመክፈቻ ስነ ሥርዓቱ ላይ በመገኘት እንደተናገሩት ሀገሪቱ በአይን ህክምና ዙሪያ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እያከናወነች ትገኛለች። ለነዚህ ሥራዎች መሳካትም በርካታ በአይን ህክምና ዙሪያ የሚሠሩ አጋር አካላት ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር በትብብር እየሠሩ መሆናቸውን የተናገሩት ዶ/ር ከበደ ወርቁ በተለይም ኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ሊታከም የሚችል አይነ-ስውርነትን አስቀድሞ በመከላከል ረገድ፣ የዘርፉን ባለሞያዎች በዕዉቀት እና በክህሎት በማብቃት፣ በአይን ህክምና ዙሪያ የሚሠሩ የትምህርት ተቋማትን አቅም በመገንባት፣ ለአይን የሚደረጉ ጥንቃቄዎችን አስመልክቶ ግንዛቤ በመፍጠር እንዲሁም በዘርፉ የሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች ላይ በመሥራት እና የተለያዩ ግብአቶችን በማቀረብ ላለፉት ሀያ አመታት ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው አመስግነዋል።
በቀጣይም ኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በአይን ህክምና ዙሪያ ለሚያከናውናቸው ስራዎች በትብብር እንደሚሰራ እና ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። በዕለቱም ዶ/ር ከበደ ወርቁ በቦሌ ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ በመገኘት ኦርቢት በራሪውን የአይን ሆስፒታል ወይም የአውሮፕላን ውስጥ የአይን ሆስፒታል ጎብኝተዋል።
በኢትዮጵያ የኦርቢስ ዳይሬክተር ዶ/ር አለማየሁ ሲሳይ በበኩላቸው ስለበራሪው የአይን ሆስፒታል እንደተናገሩት ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህክምና ትምህርት ክፍል ጋር በመተባበር ለአምስተኛ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ሲሆን አውሮፕላኑ በረቂቅ ቴክኖሎጂ የበለጸገ የማስተማሪያ ተቋም በመሆን ያገለግላል።
በዚህም ለዶክተሮች፣ ለነርሶች እና ለህክምና ቴክኒሺያኖች ስልጠና ከመስጠት በተጨማሪ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር በመተባበር የአይን ህክምና ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርስ እገዛ ያደርጋል ብለዋል። በራሪው የአይን ሆስፒታል በውስጡ እጅግ ዘመናዊ የቀዶ ጥገና፣ የመማሪያና የማገገሚያ ክፍሎች ያሉት እንደሆነ የተናገሩት ዳይሬክተሩ፥ የበጎ ፈቃደኛ ሀኪሞች ስልጠናን በአውሮፕላን ወስጥ እና በአካባቢው ከሚገኙ ሆስፒታሎች ጋር በመተባበር ይሰጣልም ብለዋል።
በራሪው የአይን ሆስፒታል ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ ከከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህክምና ትምህርት ክፍል ጋር በመተባበር ለአምስተኛ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ እንደመጣም ገልጸዋል። ለሚቀጥሉት 15 ቀናትም በራሪው ሆስፒታል በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚቆይ ለማወቅ ተችሏል።
ኦርቢስ ኢንተርናሽናል መንግስታዊ ያልሆነና የበጎ አድራጊ ዓለማቀፋዊ ድርጅት ሲሆን ዋነኛ ተግባሩም ዓይነ ስውርነትን መከላከልና የዓይን ህክምናን መስጠት ነው። ኦርቢስ ኢንተርናሽናል እ.ኤ.አ በ1960ዎቹ አሜሪካዊ የዓይን ህክምና ባለሙያ ዶ/ር ዴቪድ ፓተን (Dr. David Paton) ጽንሰ ሀሳቡን ጀምሮት በድርጅት ደረጃ የተቋቋመው ደግሞ እ.ኤ.አ በ1982 ዓ.ም ሲሆን ዋና መቀመጫውን ኒው ዮርክ ከተማ (ኒው ዮርክ፣ አሜሪካ) አድርጎ ከ90 በላይ ሀገራት ይሠራል።
ምንጭ፦ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.