Home › Forums › Semonegna Stories › ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ የመጣው የማኅበረሰብ አገልግሎቱ
Tagged: Wachemo University, ሀብታሙ አበበ, ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ
- This topic has 2 replies, 2 voices, and was last updated 5 years, 10 months ago by Anonymous.
-
AuthorPosts
-
February 4, 2019 at 7:37 am #9471SemonegnaKeymaster
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ የሚያከናውናቸው ምርምሮች በመጠጥ ውሃ፣ በግብርናና በትምህርት መስኮች ላይ እንደሚያተኩሩና የሕዝቡን መሠረታዊ ችግሮች ይፈታሉ ተብለው እንደሚጠበቁ፤ በሥራ ፈጠራ፣ በማጠናከሪያ ትምህርት በግብርናው መስኮች በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ሐዋሳ (ኢዜአ)– ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ አገልግሎቱን በማጠናከር ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሠራ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንቱ ገለጹ። ዩኒቨርሲቲው ዘንድሮ በሚያከናውናቸው ምርምሮችና በማኅበራዊ አገልግሎት ዙሪያ ከኅብረተሰቡ ተወካዮች ጋር ተወያይቷል።
የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሀብታሙ አበበ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው አገልግሎቱን በማጎልበት ኅብረተሰቡን በጥናትና ምርምር ሥራዎቹ ተጠቃሚ እንዲሆን ይሠራል።
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ የሚያከናውናቸው ምርምሮች በመጠጥ ውሃ፣ በግብርናና በትምህርት መስኮች ላይ እንደሚያተኩሩና የሕዝቡን መሠረታዊ ችግሮች ይፈታሉ ተብለው እንደሚጠበቁም ገልጸዋል። በሥራ ፈጠራ፣ በማጠናከሪያ ትምህርት በግብርናው መስኮች በመሥራት ላይ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።
◌ VIDEO: After mandatory preparations, Selale University accepts incoming students
ይሁን እንጂ ይህን የሚያከናውነው የማኅበረሰብ አገልግሎት እምብዛም ስለማይታወቅ ከኅብረተሰቡ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር መድረኩ መዘጋጀቱን ዶ/ር ሀብታሙ አመልክተዋል።
የሐዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አያሌው ዝና በዩኒቨርሲቲው የማኅበረሰብ አገልግሎት ላይ በቂ ግንዛቤ ባለመፈጠሩ ከማኅበረሰቡና ከዞኑ አስተዳደር ክፍተት መፍጠሩን በዚህም አገልግሎቱን ለማገዝ ሳይቻል መቆየቱን ይናገራሉ። ዩኒቨርሲቲው የሆሳዕና ከተማ በማስተር ፕላን እንድትመራ ለሚያከናውነው ሥራ በሚቀጥለው በጀት ዓመት 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
የአምብቾ ጎዴ ቀበሌ አባገዳ በቀለ ጅራ እንዳሉት በዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ አገልግሎት ከዚህ በፊት ተወያይተውም ሆነ ተሳትፈው እንደማያውቁ ገልጸው፣ ዘንድሮ የተጀመረው ውይይት ችግሮቻቸውን ለማሳወቅና ለመመካከር አስችሎናል ብለዋል።
መንግሥታዊ ካልሆነ ድርጅት የመጡት አቶ ዳኛቸው ዓለሙ በበኩላቸው ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከተመሠረተበት ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ የሚያከናውናቸው የማኅበረሰብ አገልግሎት ሥራዎች አመርቂ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በዩኒቨርሲቲው የሲቪል ምህንድስና ትምህርት ክፍል መምህር አቶ ታምራት ፍቅሬ የሆሳዕና ከተማ ዕድገት ማስተር ፕላኗን በጠበቀ መልኩ ለማከናወን ፕሮጀክት መቀረጹን ተናግረዋል። ፕሮጀክቱ በከተማዋ የሚካሄደው ሕገ ወጥ ግንባታን ለመቆጣጠር እንደሚያስችልም እምነታቸውን ገልጸዋል።
የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ስርጸት ጉዳዮች ተጠባባቂ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጸደቀ ላምቦሬ ዩኒቨርሲቲው ለሐዲያ ዞን አርሶ አደሮች የተሻሻለና ከፍተኛ ምርት የሚሰጥ የስንዴ ዘር፣ ለደጋማ አካባቢዎች ደግሞ የአፕል ችግኞች እንዲሁም ቡና በማቅረብ ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑ ተናግረዋል።
አርሶ አደር መልሰው ሐሲቦ ከስድስት ዓመታት በፊት በዩኒቨርሲቲው የቀረበላቸውን አፕል በማልማት ተጠቃሚ መሆናቸውን ይናገራሉ። በዓመት ሁለት ጊዜ ምርቱን በመሰብሰብ እስከ አራት ሺህ ብር እንደሚያገኙ ገልጸዋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
February 4, 2019 at 8:08 am #9477AnonymousInactiveየዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ ለአቅመ-ደካሞች ቤት ሠራ!
የሣይንስና ከፍተኛ ት/ት ሚኒስተር ባስቀመጠው “አንድ ቀን ለሕዝቤ” መርሃ-ግብር መሰረት ፣ ዛሬ በ25/05/2011 ዓ.ም. “የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የዱራሜ ካምፓስ ለሕዝቤ” በሚል መሪ ቃል ለሁለት የደሃ ደሃ ቤተሠቦች ማለትም ለአቶ አማን መሐመድ ከቀርጭቾ ቀበሌ እና ለአቶ አባቶ መኬቦ ከ ጠዛ አጋራ ቤት መልሶ የመገንባት ስራ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የዱራሜ ካምፓስ በጎ ፈቃደኛ አስተዳደር ሠራተኞች፣ መምህራን ፣ ተማሪዎችና ሌሎች የግቢው ማህበረሰብ አባላት ተሰርቷል።
ከቤቱ በተጨማሪ ፣ለእያንዳንዳቸው አባወራዎች ስፓንጅ ፍራሽና ብርድልብስ ተበርክቶላቸዋል።
በመጨረሻም፣የቤቱ ባለቤቶችና በቦታው የነበሩ ጎረቤቶቻቸው አስተያየታቸውን ተጠይቀዋል። የተሰማቸውን ሲገልፁም÷ ” ይህ በጎ ተግባር መቀጠል አለበት፣ አቅመ-ደካሞችን ከመርዳቱም በላይ ማህበረሰቡ ስለ ተቋሙ መልካም አመለካከት ከመቼውም በላቀ ሁኔታ እንዲኖረው ያደርጋል፤ ተቋሙንም እንደ ዐይኑ ብሌን እንዲጠብቅ የባለቤትነት ስሜት ያሳድርበታል” ብለዋል።
ምንጭ፦ ከዩኒቨርሲቲው ፌስቡክ ገጽ
February 9, 2019 at 9:01 am #9602AnonymousInactiveዋቸሞ ዩኒቨረሲቲ ዘሬ ቅዳሜ የካቲት 02-2011 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው ታሪክ የመጀመሪያ የሆኑትን የህክምና ዶክተሮች አሰመረቀ፡፡
—–ክብርት ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሳይነስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፣ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ. ድሌቦ ፣የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የሴኔት አባላት፣ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ስራ ሃላፊዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ የዩኒቨርሲቲው ማህበረስብ እና ውድ የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ታሪክ የመጀማሪያ የሆኑትን የህክምና ዶክተሬት ተማሪዎችን በደማው ሁኔታ አስመረቀ፡፡
በህ/ጤ/ሳይ/ኮሌጅ፤
– በቅድመ-ምረቀ በ3 ት/ት መሽኮች በህክምና ዶክተሬት ወንድ 26 ሴት 8 (ድምር 24)፣ በህ/ሰብ ጤና ወንድ 37 ሴት 15 (ድምር 52)፣ በሰርጂካል ነርስ ስፔሻሊቲ ወንድ 11 ሴት 7 (ድምር 18)፣ እና በድህረ ምረቃ በህብረተሰብ ጤና ወንድ 2 ሴት 1 (ድምር 3) በአጠቃላይ ወንድ 76 ሴት 31 (በድምሩ 96) ተማሪዎች፣
– በግ/ሳ/ኮሌጅ በቅድመ ምረቃ በክረምት መረሃ ግብር በ2 ትምህርት መስኮች በተፈጥሮ ሀብት አያያዝና በዕጽዋት ሳይንስ ወንድ85 ሴት 8 (በድምሩ 93) ተማሪዎች፣
– ቢዚነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በድህረ ምረቃ በአካውንቲንግና ፋናንስ በመደበኛ መርሃ ግብ 4 ተማሪዎች፣በአጠቃላይ በውድመ ምረቃ እና በድህረ ምረቃ በመደበኛ እና በክረምት መርሃ ግብር ሰለጠኑ ወንድ 165 ሴት 39 በድምሩ 204 ተማሪዎችን አሰመርቋል፡፡
በምረቃውም በሁላቱም ጾታ አመረቂ ውቴት የመጡ ተማሪዎች የተሸለሙ ሲሆን ከ ሴቶች ዶ/ር ጋዲሴ ሰስፋ ከወንዶች ዶ/ር ዋክሹም ፌጠነ የሰርትፍኬት እና የብር ሽልማት ተሸለመዋል፡፡ ዶ/ር ዋክሹም ፌጠነ በአጠቀላይ የሜዳሊያ ተሸላሚ ነው፡፡
ምንጭ፦ ከዩኒቨርሲቲው ፌስቡክ ገጽ
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.