የአስረኛ ክፍል አጠቃላይ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና እንደሚቀርና የሁለተኛ ደረጃ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ይሆናል

Home Forums Semonegna Stories የአስረኛ ክፍል አጠቃላይ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና እንደሚቀርና የሁለተኛ ደረጃ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ይሆናል

Viewing 1 post (of 1 total)
  • Author
    Posts
  • #11712
    Anonymous
    Inactive

    በኢትዮጵያ የትምህርትና ስልጠና ሥርዓት አወቃቀር ላይ በሚደረገው ለውጥ ከ1ኛ-6ኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ፤ 7ኛ እና 8ኛ ክፍል መለስተኛ እንዲሁም ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እንደሚሰጥ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

    አዲስ አባባ (ዶይቼ ቬለ ሬድዮ) – ከመጪው የትምህርት ዓመት (2012 ዓ.ም.) ጀምሮ የአስረኛ ክፍል አጠቃላይ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና እንደሚቀር የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌጤ ተናገሩ።

    በአዲሱ የኢትዮጵያ የትምህርት ፍኖተ-ካርታ መሠረት ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ በሚሆነው አሠራር ለስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ክልላዊ ፈተና ይሰጣል ተብሏል። የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጥላዬ ነሐሴ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በትምህርት ፍኖተ-ካርታ ላይ ረዘም ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

    ሚኒስትሩ አጠቃላይ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ተብሎ የሚጠራው እና አስረኛ ክፍልን ለሚያጠናቅቁ ተማሪዎች ይሰጥ የነበረው አገር አቀፍ ፈተና ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ እንደማይኖር መናገራቸውን የአዲስ አበባው የዶይቼ ቬለ ሬድዮ ወኪል ዘግቧል።

    ከ1993 ዓ.ም. ጀምሮ ይሰጥ በነበረው አጠቃላይ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በአብዛኛው ተማሪዎች ዘጠኝ የትምህርት ዓይነቶች ሲፈተኑ ቆይተዋል። በአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አማካኝነት የሚሰጠውን ይኸን ፈተና ያለፉ ተማሪዎች ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ወደ መሰናዶ ትምህርት (preparatory) ይሻገራሉ።

    በኢትዮጵያ የትምህርትና ስልጠና ሥርዓት አወቃቀር ላይ በሚደረገው ለውጥ ከ1ኛ-6ኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ፤ 7ኛ እና 8ኛ ክፍል መለስተኛ እንዲሁም ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ይሰጣል።

    በዚህም መሠረት መጀመሪያ ደረጃ አንደኛ ሳይክል (ከ1ኛ ክፍል እስከ 4ኛ ክፍል)፣ መጀመሪያ ደረጃ ሁለተኛ ሳይክል (ከ5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል)፣ ሁለተኛ ደረጃ አንደኛ ሳይክል (9ኛ እና 10ኛ ክፍል) እና ሁለተኛ ደረጃ መሰናዶ ትምህርት (11ኛ እና 12ኛ ክፍል) ተብሎ ሥራ ላይ የነበረው አወቃቀር ይቀየራል።

    በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት በክልላዊ መንግሥታት የሚሰጥ የስድስተኛ ክፍል ፈተና እንደሚኖር ሚኒስትሩ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት «መጀመሪያ ደረጃ ሁለተኛ ሳይክል» ተብሎ በሚጠራው ምዕራፍ መጨረሻ ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች በክልሎች የሚሰጠው የሚሰጠው ፈተና ሀገር አቀፍ ይሆናል ተብሏል።

    ምንጭ፦ ዶይቼ ቬለ ሬድዮ

    የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት


Viewing 1 post (of 1 total)
  • You must be logged in to reply to this topic.